እንኳን አደረሰን!
የመንበረ ጸባዖት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን በ፲፰፹፫ / 1883 ዓ.ም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተመሠረተ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ የ፻፳፰/ 128 ዓመት ዕድሜ ባለቤት ነው።
የቅዱስ በዓለወልድ /መካነ ሥላሴ/ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተው በ፲፰፹፫ / 1883 ዓ.ም በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አማካይነት ሲሆን ለምሥረታው የተነሳሱበትም ዋናው ምክንያት አንድ ባሕታዊ መነኩሴ “ከቤተ መንግሥትዎ በስተቀኝ ባለው ከፍታ ቦታ ላይ ሦስት ነጫጭ ርግቦች መጥተው ሲያርፉ በራዕይ አይቻለሁና (መካነ ሥላሴ) የሚል ጽሕፈት ያለበት ጽላት አስፈልገው በማምጣት እንዲተክሉ እግዚአብሔር አዟልና እንዲተከል ይሁን።” ስለተባሉ በዚሁ መነሻነት መካነ ሥላሴ የሚል ጽሕፈት ያለበት ጽላት ሲያስፈልጉ ቆይተው ከአዲስ ዓለም በላይ ፉየታ ከሚባለው ቦታ እንዳለ በጥቆማ ስለደረሱበት ለቦታው ሌላ ጽላት ተፈልጎለት በንጉሡ ትእዛዝ በአለቃ ወልደ ያሬድ ኤላሪዮን አስመጭነት በወቅቱ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት በነበሩት በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ እጅ ከተረከቡ በኋላ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ንጉሠ ሸዋ በተባሉ በ25ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው በነገሡ በአንደኛው ዓመት ታህሣሥ ፳፪ / 22 ቀን ፲፰፹፫ / 1883 ዓ/ም የአዛዥ ዘአማኑኤል እልፍኝ ተባርኮ በዚሁ ቅዱስ ሥፍራ በመቃኞ /በመቃረቢያ/ ቆይቶ ይህ አሁን ለዕድሳት የበቃው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለ12 ዓመታት በግንባታ ላይ ከቆየ በኋላ በ ፲፰፺፭ / 1895 ዓ/ም በመጠናቀቁ መስከረም ፯ / 7 ቀን ፲፰፺፭ / 1895 ዓ/ም ታቦተ ሕጉ ከነበረበት መቃረቢያ ወጥቶ በዓለ ንግሥ ተደርጎለት አዲስ ወደ ታነፀው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል።
በዚሁ አጋጣሚ ሳይጠቀስ የማይታለፈው ዐቢይ ጉዳይ ደግሞ ቀደም ሲል ጽላቱ ከግራኝ መሐመድ ወረራ በፊት ወረኢሉ ደሴ የነበረ ሲሆን በግራኝ ወረራ ምክንያት ካህናቱ አሽሽተው ወግዳ ወስደው አኑረው ለብዙ ዘመናት ከቆየ በኋላ የራስ ጎበና ባለቤት ወ/ሮ አየለች ከወሎ ወግዳ አስመጥተው አዲስ ዓለም በላይ ፉየታ ከተባለው ቦታ ላይ አስተክለው እንደነበርና ታሪኩ እንደሚያስረዳው በአፄ ምኒልክ ትዕዛዝ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በዚሁ ቦታ ላይ የተተከለ ሲሆን መካነ ሥላሴ የሚለው የደብሩ ስያሜም የተሰጠው ከጽላቱ ላይ ከተገኘው ጽሕፈት በመነሳት እንደሆነ ከታሪኩ ለመረዳት ተችሏል።
የድንግል እናታችን ልጅ ስሞቹ ፦ ቃል፣ ወልድ፣ አማኑኤል፣ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ፣ መድኃኔ አለም። ሲሆኑ ትርጓመያቸውም፦
#ቃል ማለት፦ አንደቤት መናገርያ ማለት ስሆን ከ3ቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር #ወልድ በህልውነት/በመሆን ግብሩ የ #አብ እና የ #መንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ስሆን የእግዚአብሔር ቃል ይባላል። ራእይ 19፥13 “በደም የታለሰ ልብስም ለብሶአል ስሙንም “ቃል እግዚአብሔር” አሉት። ቍላስ.1፥16 “በእርሱ ቃልነት እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአልና….”
#ወልድ ማለት፦ ከ3ቱ አካላት ፩(1)ዱ ወልድ ስሆን ልጅ ማለት ነው የ #ወልድ አካላዊ ግብሩ መወለድ ማለት ነው የ #አብ የባሕርይ ልጅ ስለሆነ እግዚአብሔር ወልድ ይባላል። ገላ.4፥4,, ዮሐ.ወ 5፥16,, ማቴ 3፥17…
#አማኑኤል ማለት፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። ማቴ 1፥23። ይህን በት.ኢሳ 7፥14 ላይ ስሙን እናገኛለን። ይህ ማለት ከድንግል በተዋህደው ተዋህዶ አምላክ ሰው ሆነ ዮሐ.1፥14 …….. 1ኛ ቆሮ 15፥21 አዳምን የመጀመርያው ሰው ይላል ክርስቶስን ደግሞ ሁለተኛው ሰው ይለዋል።
#ኢየሱስ ማለት፦ መድሃኒት ማለት ነው ይህን መጽሐፍ ቅዱስም ይናገራል ሉቃስ 2፥11 “እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኃል” እንዳለ መልአኩ ለእረኞች….
#ክርስቶስ ማለት፦ “ቅቡ /የተቀባ” ማለት ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና በመሰሎቿ አብያተ ቤተክርስትያናት “የተዋሃደ” ተብሎ ይተረጉማል።
#መድኃኒአለም ማለት፦ የአለም መድኃኑት ማለት ነው። በእርሱ አለም ስለዳነ (በሞቱ አለምን ስላዳነ) መድኃኒአለም የአለም መድሃኒት እንለዋለን። ሉቃስ 2፥11 ላይ እኔሆ ለሕዝብ ሁሉ የምሆን መድኃኒት እንዳላለ ሉቃስ፤ ዮሐ.ወ 1፥29 ላይ መጥምቁ ዮሐንስ “እነሆ የአለምን ኃጢአት የምያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” እንዳለው እንደገና በሮሜ 5፥12-21 ስናነብ በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ሞት ወደ አለም እንደመጣ ሁሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም አለም እንደዳነ ይናገራል…………..እኛ ኦርቶዶክሳዊያን በነዚህ ስሞች አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችንን እናከብረዋለን እንጠራዋለን እናመልከዋለን ። “ኢየሱስ ብቻ ስሙ ነው ሌሎችን ከየት አመጣችሁ ለምን ባለወልድ አማኑኤል መድሃኒአለም እያላቹ ትጠሩታላችሁ ኢየሱስ ማለት ብቻ እንጅ” የምሉ ወገኖቻችን አሉና እነዚህን ስሞችን እኛ ኦርቶዶክሶች ፈጥረንለት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሱ እራሱ እንደምጠራው መገናዘብ ይገባናል።
ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይድረሰው የእኛ ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ። ክብር ለወለደችው ለድንግል!!!
_________
Like this:
Like Loading...