እንሳቅ? እናልቅስ? ወይስ እየሳቅን እናልቅስ?
ዴንማርክ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ጋር ተጣብቃለች። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በዴንማርኳ አዓርሁስ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ አገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ላይ ከ ሃያ ዓመት በታች እድሜ ያላቸው ሯጮች ብቻ መሳተፍ ነበረባቸው። ነገር ግን በዚህ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት፡ ጌትነት የትዋለ እና ድንቅዓለም አየለ፡ እድሜያቸው አሥራ ስምንት ነው ተብለው እንዲሳተፉ ተደርጓል፤ የተመለከተ ሁሉ ግን ሁለቱም አረጋውያን መሆናቸውን በማየቱ አሁን የአውሮፓውያን ማሕበረሰባዊ ሜዲያ መሳለቂያ ሆነዋል። በተለይ የስፔይኑ የስፖርት ጋዜጣ፡ “አስ/AS” ሰፊ የሆነ ዘገባ በዚህ ጉዳይ ላይ አቅርቧል። ሯጮቹ አሥራ አንደኛ እና ሃያ አንደኛ ወጥተዋል። እውነትም ጌትነት የትዋለ፤ ለመሆኑ ድንቅዓለምስ የትዋለ? የፊልም ባለሙያዎች እስኪ“የትዋለ እና ድንቅዓለም”በማለት ድራማ ስሩላቸው!
ውድድሩን ተከታትለው አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ያሸነፉት ጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ሚልከሳ መንገሻ እና ታደሰ ወርቁ ናቸው።