Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April, 2019

የኢትዮጵያ አለኝታ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ሃገራችን ቅጥሯ ተደፈረ፣ አላዊያን እጅግ በረቱብን፣ ደማችን በከንቱ ፈሰሰ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2019

የትናንቶቹ አባቶቻችን አንተን መከታ አድርገው፣ ታቦትክን ይዘው ድል አደረጉ፤ ጠላትም ይፈር የሞቱንም እዳ ከእጅህ ይቀበሉ፤ ና ቶሎ ና፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ገበዝ።

እንኳን አደረሰን! የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግብጽ ኢማም | የስፊንክስ ሃውልት እና የጊዛ ፒራሚዶች መፍረስ አለባቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2019

እንደ ኢማሙ ከሆነ እነዚህን የግብጽ ታሪካዊ ቦታዎች አፈራርሶ ማጥፋት የሃሰተኛው ነብይ መሀመድ ፍላጎት ነው፤ ስለዚህ እነዚህ “የጣዖት ሐውልቶች” በቅርቡ ክግብጽ ምድር መጥፋት አለባቸው።

ግብጽ ስትረጋጋ ኢትዮጵያ ትናወጣለች፤ ኢትዮጵያ ስትረጋጋ ግብጽ ትናወጣለች!

ምነው ባደረገው! ፍየሏ ግብጽ እንደገና መበጣበጥ አለባት አለዚያ በጓ ኢትዮጵያ ሰላም አይኖራትም። “ቤኒሻንጉል” ተብሎ በሚጠራው ሌላው ሰው ሰራሽ አፓርታይዳዊ ክልል በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ጽንፈኛ ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍየሏ ግብጽ ጋር የተያያዘ ነው። ገና ከመሠረቱ ይህ ቤኒ ሻንጉል የተባለው ክልል ሲቋቋም ይህን መሰል ችግር እንደሚፈጠር አስቀድመው በማወቅ ነው። ከሃያ ሰባት ዓመታት በፊት ሉሲፈራውያኑ የክልሎችን ካርታ ለህዋሃት እና ኦነግ መንግስት ሲያስረክቧቸው አሁን በአገራችን እየታየ ያለው ቀውስ እንደሚመጣ ሰለሚያውቁ ነው። ይህ አሁን ግልጽ ነው!

የሕዳሴ ግድቡ ሆን ተብሎ ቤኒ ሻንጉል በተባለው ክልል እንዲገነባ መደረጉ አንድ ቀን፡ በጎቹን ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ከክልሉ መንጥረው ካስወጡ በኋላ በቀላሉ ሊቆጣጠሯቸው የሚችሏቸውንና የአረብ መጋረጃ በመልበስ ላይ የሚገኘውን “የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብን” ወደ ሱዳን በመጠቅለል በግብጽና አረቦች እጅ ለማስገባት በመሻት ነው።

ኦሮሚያ በተባለው ክልል ደሀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሮ ግሮ ያጠራቀመውን ገንዘብ የዋቄዮ አላህ ልጆች እንደሚዘርፉት፤ በቤኒ ሻንጉልም ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን አሰባሰበው እየገነቡት ያሉትን የሕዳሴውን ግድብ እነ ግብጽ ለመውረስ በመዘጋጀት ላይ ናቸው። ለፍየሏ ግብጽ የጊዮንን ውሃ ለዘመናት በነጻ መጠጣት ብቻ በቂ ስላልሆን፣ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ደም መጠጣት፣ ኩላሊቶቻቸውን መስረቅ ብቻ በቂ ስላልሆነ፡ አሁን ኢትዮጵያውያን ላባቸውን አንጠፍጥፈው ባጠራቀሙት ገንዘብ የገነቡትን ግድብም በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ ተነሳስተዋል።

ልክ በደርግ ጊዜ የሉሲፈራውያኑ ተቋም ሲ አይ ኤ የኢትዮጵያን ሠራዊት ብትንትኑን ለማውጣት የጦር መሪዎችን እንዲያስወግድና እንዲገድል ኮሎኔል መንግስቱን እንዳዘዙት፤ በሕማማት ሳምንት ሆን ተብሎ (የቤኒ ሻንጉሉ ዕልቂት ታቅዷልና)ከኢትዮጵያ ሹልክ በማለት ወደ ቻይና ሄዶ የነበረውን ኮሎኔል አብዮት አህመድንም በተመሳሳይ መልክ ሠራዊታችንን እንዲያዳክም፣ ልምዱ ያላቸውን የጦር መሪዎችን እንዲያባርርና በምትካቸው ሴቶችን/እንደ ሴት የሆኑትንና በቀላሉ እጅ የሚሰጡትን ፀረኢትዮጵያውያንን እንዲያስቀምጥ ተደርጓል። ደርግ ሥልጣን ላይ ሲወጣና አሁን በአገራችን እየታየ ያለው ሁኔታ በጣም ተመሳሳይ ነው። ግብጽ በአሁን ሰዓት ወደ ቤኒ ሻንጉል በቀናት ውስጥ ሰተት ብላ በመግባት የሕዳሴውን ግድብ መቆጣጠር ትችላለች።

ይህ እንዳይሆን ግን ግብጽ እራሷ መናወጥ እና መጥፋት አለባት፤ ስለዚህ የኢማሙ ሃሳብ ጥሩ ነው፤ ፒራሚዶቹን ቶሎ አፈራርሷቸው እላለሁ!

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፱፥]

ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።

ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።

የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቍሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ።

ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።

ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።

በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም።

ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።

የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ።

ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች።

፲፩ የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሰነፎች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው ድንቍርና ሆነች። ፈርዖንን። እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?

፲፪ አሁንሳ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብጽ ላይ ያሰበውን ይወቁ።

፲፫ የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፤ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብጽን አሳቱ።

፲፬ እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል፤ ሰካር በትፋቱ እንዲስት እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ አሳቱ።

፲፭ ራስ ወይም ጅራት የሰሌን ቅርንጫፍ ወይም እንግጫ ቢሆን ሊሠራ የሚችል ሥራ ለግብጽ አይሆንላትም።

፲፮ በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ መንቀሳቀስ የተነሣ ይሸበራሉ ይፈሩማል።

፲፯ የይሁዳም ምድር ግብጽን የምታስደነግጥ ትሆናለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመከረባት ምክር የተነሣ ወሬዋን የሚሰማ ሁሉ ይፈራል።

፲፰ በዚያ ቀን በግብጽ ምድር በከነዓን ቋንቋ የሚናገሩ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም የሚምሉ አምስት ከተሞች ይሆናሉ፤ ከነዚህም አንዲቱ የጥፋት ከተማ ተብላ ትጠራለች።

፲፱ በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔር ዓምድ ይሆናል።

ይህም ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በግብጽ ምድር ምልክትና ምስክር ይሆናል፤ ከሚያስጨንቁአቸው የተነሣ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉና፥ እርሱም መድኃኒትንና ኃያልን ሰድዶ ያድናቸዋልና።

፳፩ በዚያም ቀን እግዚአብሔር በግብጽ የታወቀ ይሆናል፥ ግብጽAውያንም እግዚአብሔርን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በቍርባን ያመልካሉ፥ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ ይፈጽሙትማል።

፳፪ እግዚአብሔርም ግብጽን ይመታታል፤ ይመታታል ይፈውሳታልም፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ እርሱም ይለመናቸዋል ይፈውሳቸውማል።

፳፫ በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ ግብጽ፥ ግብጻዊውም ወደ አሦር ይገባል፤ ግብጻውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ።

፳፬፤፳፭ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሕዝቤ ግብጽ፥ የእጄም ሥራ አሦር፥ ርስቴም እስራኤል የተባረከ ይሁን ብሎ ይባርካቸዋልና በዚያ ቀን እስራኤል ለግብጽና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፥ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል።

_______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ክርስቲያኖች የተሰውባት ስሪ ላንካ የእስልምና ልብስን በሕግ አገደች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2019

ባለፈው ሳምንት፡ የካቶሊኮች ፋሲካ ዕለት፡ በተለያዩ የስሪ ላንካ ከተሞች እስከ ሦስት መቶ የሚጠጉ ክርስቲያኖችን ሙስሊሞች በመግደላቸው ነው አሁን ስሪ ላንካ ሙሉ የፊት ገጽታን የሚሸፍን ሂጃብ‘ ‘ቡርካእና ኒቃብለማገድ የተገደደችው። ከአጥፍቶ ጠፊዎቹ መካከል ብዙ ሴቶች ይገኙበት እንደነበር ተገልጿል።

ልክ እንደ ኢትዮጵያ አገራችን በስሪ ላንካ ሴቶች እነዚህን አስቀያሚ ልብሶች መልበስ የጀመሩት ከ ሰላሳ ዓመታት በፊት ነበር። በኢራቅና ኩዌት መካከል የመጀመሪያ ገልፍ ጦርነት ሲጀምር ማለት ነው።

በዘመናችን ዓለም አቀፉ የጂሃድ እንቅስቃሴ የጀመረው በዚህ ወቅት ነበር። በአገራችን ግብጽ፣ ኢራቅ እና ሶሪያ የኤርትራን፣ ሱዳንን እና ሶማሊያን ጂሃዲስቶች በመርዳት ኢትዮጵያን ይበታትኑ ዘንድ ሁለተኛው ደረጃ ላይ አደረሷቸው፤ የመጀመሪያው፤ በፈረንሳይ አነሳሽነት ጂቡቲን አስመልክቶ ተካሂዷል፤ አሁን ደግሞ ሶማሌ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ እና አማራ ነን የሚሉትን ወገኖቻችን (Useful Idiots/ጠቃሚ ሞኞች) በብሔር እንዲደራጁና ለጦርነት እንዲነሳሱ በመቆስቆስ ኢትዮጵያን ለመጨረሻ ጊዜ እራሳቸው ይበታትንሏቸው ዘንድ እንደ አሻንጉሊት ሲጠቀሙባቸው ይታያሉ።

ግን ለጊዜው ነው፤ እያንዳንዱ ከሃዲ አሁኑኑ ስህተቱን ካላረመ እና ንስሐ ገብቶ ቶሎ ካልተመለስ ገሃነም እሳት ነው የሚጠበቀው! እየታየ ያለው ክህደት እና ንቀት የተሞላበት ተግባር እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ ወንጀል ነውና።

_______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጌታችን ትንሣኤ፣ የድኅነታችን ብሥራት ነው | እንኳን አደረሰን!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2019

ሰማያት (ሰማያውያን መላእክት) የደስታ በዓልን ያደርጋሉ፤ ደመናት (ቅዱሳን) የደስታን በዓል ያደርጋሉ፡፡ ምድር (ምድራውያን ሰዎችም) በክርስቶስ ደም ታጥባ (ታጥበው) የፋሲካን በዓል ታደርጋለች (ያደርጋሉ)፡፡ ያከብራሉ (ታከብራለች)፡፡ ዛሬ በሰማያት (በመላእክት ዘንድ) ታላቅ ደስታ ኾነ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ የፋሲካን የነጻነት በዓል ታደርጋለች፡፡ የትንሣኤያችን በኵር ክርስቶስ ከሙታን ሰዎች ዂሉ ተለይቶ ቀድሞ ተነሣ፤” (ድጓ ዘፋሲካ)፡”

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | 1 Comment »

አስደናቂ ዕይታ | በደመናዎች መሃል የገባው የፀሐይ ብርሃን መስቀል ሠርቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2019

ፍኖተ መስቀል – የመስቀል መንገድ

ፍኖተ መስቀል ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጲላጦስ ዐደባባይ አንሥቶ መስቀሉን ተሸክሞ እስከተሰቀለበት ተራራ ቀራንዮ ድረስ የተጓዘበት መንገድ ማለት ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሙስ ማታ እንደተያዘ ሌሊቱን ሁሉ መከራ ሲቀበል አድሮ ዓርብ ጧት የአይሁድ ሽማግሌዎችና አለቆች ተሰብስበው ወደ ሹሙ ወደ ጲላጦስ ቤት ይዘውት ሔዱ፡፡ ከዚያም ይህ ሰው ከሕጋችን ጋር የማይስማማ ትምህርት ሕዝቡን ያስተምራልና እንደ ሕጋችን ሞት ይገባዋል፡፡ ንጉሥ ነኝ፣ እያለም ያታልላል በማለት በሹሙ ፊት ቀርበው ከሰሱት፡፡ ጲላጦስ ግን ብዙ ቢዋሹበትና ቢከሱት አላመናቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም መርምሮ በደል አላገኘበትምና ሊያድነው አስቦ ነበር፡፡ ግን ሊያድነው አልተቻለውም፡፡

ጲላጦስ ጌታችንን ሲመረምር ለብቻው አቁሞ መጠየቅ የሮማውያን ልማድ ነበርና አዳራሽ አስገብቶ ለብቻው የተከሰሰበትን ነገር ጠየቀው፡፡ አይሁድ ግን በዓለ ፋሲካ ደርሶባቸው ነበርና ስለ በዓሉ ክብር ሲሉ ወደ ፍርድ ቤት አልገቡም፡፡ ከውጪ ተሰብስበው እርስ በእርሳቸው እንደፈቃዳቸውና እንደምኞታቸው ጌታን ለመስቀል ያስቡ ነበር፡፡

ጲላጦስም ጌታን ለብቻው በጥያቄ ከመረመረው በኋላ ከአዳራሹ ወደ ውጭ ብቅ ብሎ በዚህ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ወይም ምክንያት አላገኘሁበትም ያውላችሁ አላቸው፡፡ እነሱም ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏልና ሞት ይገባዋል፡፡ ስቀለው፣ ስቀለው እያሉ መለሱለት፡፡ እሱም እንደገና ለብቻው ጠይቆና መርምሮ የሚሞትበት በደል ስላላገኘበት ከአዳራሹ ወደ ውጭ ወጣና ውኃ አስመጥቶ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ፡፡ ከዚህም ሰው ደም ንጹሕ ነኝ ሞት አልፈርድበትም እያለ ሐቁን መሰከረ፡፡

አይሁድ ግን ይህ ሰው ንጉሥ ሳይሆን ንጉሥ ነኝ ብሏል፤ ንጉሥ ነኝ የሚል ሁሉ የቄሳር ተቃዋሚ ጠላት ነው፡፡ የቄሳር ወደረኛ መሆኑን እኛ እየመሰከርን አንተ ግን የቄሳር ሹም ሆነህ ብትለቀው አንተ ታውቃለህ እያሉ ጲላጦስን አስፈራርተውታል፡፡ ጲላጦስም ይህን ሲሰማ በራሱ ላይ ክስ እንዳይመጣበት ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ጌታችንን ወታደሮቹ ተቀብለው ወደ ሌላ አዳራሽ አስገቡት፡፡ ልብሱን ገፍፈው፣ ሌላ ቀይ ልብስ አልብሰው፣ የሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፍተው፣ ዘንግ በእጁ አስይዘው፣ ሎቱ ስብሐት ንጉሥ ከሆንህ ለአንተ ስግደት ይገባል፡፡ ልብሰ መንግሥት ያምርብህ ይሆን? ክርስቶስ ከሆንህ ትንቢት ንገረንእያሉ ፊቱን ሸፍነው ራስ ራሱን በዘንግ እየመቱ ተሳለቁበት፡፡

ከያለበሱትንም ልብስ ገፍፈው የቀድሞ ልብሱን አልብሰው፣ መስቀሉን አሸክመው ወደሚሰቀልበት ቦታ ወደ ቀራንዮ ሲወስዱት የተነሡበት ቦታ ገበታ /ገበጣ/ ተብሎ ይጠራል፡፡ ከዚህ ቦታ ተነሥቶም መስቀሉን ተሸክሞ መከራውን ታግሶ እስከ ቀራንዮ የተጓዘበት ፍኖተ መስቀል ይባላል፡፡

___________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

ድንቅ ተዓምር በጠፈር | ዝነኛው ቴሌስኮፕ በ፴፩ ሚሊየን የብርሃን ዓመት እርቀት ላይ ክቡር መስቀሉን አገኘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2019

የአሜሪካ የህዋ ምርምር ተቋም፡ ናሳ/ NASAንብረት የሆነው ሃብል ቴሌስኮፕ/ Hubble Telescope በ፴፩ ሚሊየን የብርሃን አመት እርቀት ላይ እኛ ከዚህ ሆነን ማየት የማንችለውን ነገር በጥለቂ ጋላክሲ ለማየት ችሏል። ይህ በጣም አስገራሚ የሆነ ነገር የተከሰተበት ቦታ በጣም ከመራቁ የተነሳ ርቀቱ በእኛ ኪሎሜትር አይለካሙ፤ በብርሃን ፍጥነት እንጅ፤ ስለዚህ የብርሃን ዓመት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። 1 ብርሃን ዓመት = 10 ትሪሊየን ኪሎሜትር – ወይንም 10 ሚሊየን ሚሊየን ኪሎሜትር።

ምድር ላይ፤ በቅርቡ ስፔን ላይ ከሃዘን ጋር እንዳየነው፤ መቶ ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የነበረውን ሕፃን ለሁለት ሳምንታት ያህል ቆፍረው ማውጣት አልቻሉም፤ ግን ወደ ሌላ ዓለማት ርቀው በመሄድ ብዙ ሲደክሙ ይታያሉ፤ ምን እንደሚፈልጉ እንኳን የሚያውቁት አይመስለኝም።

ተመልከቱ! አምላካችን ኢየሱስ ግን በሁሉም ቦታ መኖሩን ያሳያቸዋል፤ እኔ ነኝ ጸጋው፣ ምሕረቱ፣ ሰላሙ ፣ እውነቱ፣ ቸርነቱ፣ ፍቅሩ በማለት ምድር ላይ የሰጠንን ክቡር መስቀሉን ከሁሉም ዓለሞች ሆኖ ያሳያቸዋል። አሁንስ ምን ይሉ ይሆን? ይህ ተዓምር በተለይ በፋሲካ ዋዜማ መታየቱ አይስገርማቸውምን? ለማመን በግትርነት ሌላ ምልክት ማየቱን ይሹ ይሆን?

ያዘን እናት የንባ ባሕር

ቁማ ነበር እመስቀል ሥር

ተቸንክራ በፍቅር፡፡

ቅድስት እናት ለዘላለም

በልቤ ውስጥ እንዲታተም

የልጅሽ የየሱስ ሕማም፡፡

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ያስለቅሳል! ግን፡ ዓርብ ስቅለት ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 25, 2019

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት

ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል

. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)››

. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››፤

. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፤

. እመቤታችንን ‹‹ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩንም ‹‹እናትህ እነኋት›› በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤

. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ››

. ‹‹ተጠማሁ››፤

. ‹‹ዅሉ ተፈጸመ›› (ማቴ. ፳፯፥፵፭፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲)፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ጸሎተ ሐሙስ | “ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው” | ወገኔ ሆይ! የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 24, 2019

  • ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ

በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸሙ ተግባራት

በዕለተ ሐሙስ ከተፈጸሙ ዐበይት ተግባራት አንዱ መድኃኒታችን ክርስቶስ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፤›› ብሎ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ ነው (ማቴ. ፳፮፥፳፮፳፰)፡፡ እንደዚሁም ይህ ዕለት ሰፊ ጸሎት የተደረገበት የጸሎት ቀን ነው፡፡ ጌታችን ሐሙስ ዕለት ወዙ እንደ ውኃና እንደ ደም ወርዶ መሬቱን ጭቃ እስኪያደርገው ድረስ መላልሶ ስለ ጸለየ ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን የጸለየበትን ቦታም ወንጌላውያኑ በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፤ ማቴዎስና ማርቆስ – ‹ዐፀደ ወይን›፣ ‹ጌቴሴማኒ›፤ ሉቃስ – ‹ደብረ ዘይት›፤ ዮሐንስ – ‹ማዕዶተ ቄድሮስ›፣ ‹ፈለገ አርዝ›፣ ‹ዐፀደ ሐምል› በማለት ሰይመውታል (ማቴ.፳፮፥፴፮፤ ማር.፲፬፥፴፪፤ ሉቃ. ፳፩፥፴፯፤ ፳፪፥፴፱፤ ዮሐ. ፲፰፥፩)፡፡

በተጨማሪም ይህ ዕለት (ሐሙስ) ያለ እርሱ ፈቃድ ሊይዙት እንደማይችሉ ለማስረዳት ጌታችን በመለኮታዊ ኃይሉ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ካደረጋቸው በኋላ በይቅርታው ብዛት መልሶ በማስነሣት በፈቃዱ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው (ዮሐ. ፲፰፥፭)፡፡ በዕለተ ሐሙስ ከተከናወኑ ዐበይት ተግባራት መካከል ሠራዔ ሕግ፣ ፈጻሜ ሕግ የኾነው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕገ ኦሪትን እየፈጸመ አድጓልና በኦሪት ሥርዓት የሚፈጸመውን የመጨረሻውን በግዐ ፋሲካ (የፋሲካ በግ) ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መመገቡ አንደኛው ነው፡፡ ይሁዳ እንደሚያስይዘው ለሐዋርያት በምልክት ማስረዳቱ ሁለተኛው ሲኾን (ዮሐ. ፲፫፥፳፩)፤ እንደ አገልጋይ ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ደግሞ ሦስተኛው ነው፡፡

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዲያብሎስ ጂሃድ በፋሲካ | መሀመዳውያኑ በግብጽ እና ናይጄሪያ ክርስቲያን ሕፃናት ላይ እየዘመቱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 24, 2019

በደቡብ ግብጽ የአንድ ሺህ ሦስት መቶ ኮፕት ክርስቲያኖች መኖሪያ በሆነችው በ ናጋ አልጋፊር መንደር የሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የተገኙትን ሦስት መቶ የሚሆኑ ሕፃናትን ጎረቤቶቻቸው የሆኑት ሙስሊሞች ግር ብለው ለጥቃት በመምጣት ስላስፈራሯቸው ቤተክርስቲያናቸው ያው በፋሲካ ዋዜም እንዲዘጋ ተደርጓል። ለመንደሩ ያለው ቤተክርስቲያን አንድ ብቻ ነው።

በናይጄሪያ ደግሞ፤ በካቶሊኮች ፋሲካ ዕለት፡ ጎምቤ በምትባለዋ ከተማ አንድ ሙስሊም ፖሊስ በዓሉን ለማክበር መንገድ ላይ ወጥተው የነበሩትን ሕፃናት በመኪና በመግጨት አሥሩን ሲገድል፤ ሰላሳ የሚሆኑትን አቁስሏል። በድርጊት የተናደዱት የሕፃናቱ ዘመዶች ሙስሊሙን ፖሊስ ተከታተለው በመያዝ ቀጥቅጠው ገድለውታል።

በሌላ በኩል ባለፈው ረቡዕ በመካከለኛ ናይጄሪያ ሙስሊም ፉላኒ እረኞች፡ ለ አንድ ህፃን የቀብር ሥነ ሥርዓት የወጡትን አስራ ሰባት ክርስቲያኖችን ጨፍጭፈው ገድለዋቸዋል

ባለፈው ዓመት የፋሲካ በዓል ላይም ፉላኒ ሙስሊሞች አሥራ ዘጠኝ ክርስቲያኖችን መግደላቸው ይታወሳል።

ሜዲያዎች ይህን ዜና አግባብ ባለው መልክ አላቀረቡልንም፤ የመሀመድ አርበኞች በአገራችንም ተመሳሳይ ዲያብሎሳዊ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው፤ እግዚአብሔር ያልታሰበ ነገር ወይም እሳቱን ያውርድባቸው፤ እነዚህ ሰይጣኖች፤ ባጭር ይቅሩ!


10 Killed, 30 Injured In Nigeria After Policeman Ploughs Car Into Children


Ten people have died and 30 left wounded after a policeman ploughed his car into a group of children during Easter proceedings under way in Nigeria late on Sunday, AFP reported.

According to police sources who spoke to AFP, the angry bystanders killed the policeman, who was off-duty at the time the incident took place.

State police spokesperson Mary Mallum told AFP that the policeman as well as a parliamentary member were among the dead.

Witnesses who spoke to AFP said the driver got into an argument regarding the proceedings blocking the road and purposefully rammed his car into the crowd, RTE writes.

“The driver of the car had a heated argument with the children before they made way for him to pass, only for him, in a fit of rage, to turn and drive into them,” said Isaac Kwadang, head of the Boys Brigade in Gombe.

Various reports state that according to Mallum, the injured children have been taken to hospital and the investigation is ongoing.

Other recent Easter Sunday attacks include a series of eight bombings in Sri Lanka which left at least 322 people dead and more than 300 injured, the Associated Press previously reported.

Police have arrested 40 suspects, including the driver of a van allegedly used by the suicide bombers and the owner of a house where some of them lived.

The attacks took place at three churches attended by worshippers during Easter Sunday services as well as three luxury hotels. At least 39 foreigners were killed.

Source


CHURCH CLOSED IN EGYPT AFTER MUSLIM MOB FRIGHTENS CHILDREN IN SUNDAY SCHOOL


Another worship building shuttered over ‘sectarian tensions.’

A Coptic church in Upper Egypt is closed after a throng of angry Muslims attacked it this month, beating a priest and another Copt as more than 200 fearful children who had gathered for Bible lessons looked on, according to advocacy groups.

One of the injured Copts, Asaad Bakheet Rezek, told Coptic TV (CTV) that a Muslim about 17 years old beat one of the priests with a club as security forces led him from the Anba Karas Church building in Naga al-Ghafir, Sohag Governorate in southern Egypt.

The priest, identified as Father Basilious, sustained a minor head injury as security forces escorted him and another priest into an armored vehicle after the chanting mob tried to enter the building, Rezek said, adding that the children were terrified by the club- and knife-wielding crowds as they shouted, cursed and pelted the building with rocks.

The village mayor had gone to the church premises the previous day, angry at construction underway for a fourth floor to a building annex, according to advocacy groups Coptic Solidarity and the Egyptian Initiative for Personal Rights (EIPR).

The mayor accused the Christians of “treason” for the add-on. He started shouting to neighbors to take action against the church and left, later submitting a notice at the city council complaining about the construction, according to the groups. The city council immediately arrived, stopped the work and confiscated building materials, including the cement and the reinforced steel.

The next day at 4 p.m., dozens of angry demonstrators tried to enter the church premises but were unable to get through a steel door. Carrying clubs and knives, they started shouting, cursing and pelting the building with rocks, according to Coptic Solidarity.

Additional forces arrived, and Father Basilious was struck as he and another priest were escorted off the premises. Parents and church leaders were not able to move the 200 children away from the angry, chanting villagers until security forces dispersed the crowds. Though police witnessed the beating of the priest, no arrests were made.

Both Father Basilious and Father Bakhoum were taken for questioning into the evening hours.

Police issued an indefinite closure order, pending investigations, and froze all activities of the 10-year-old church, including the its daycare and the Sunday School.

The church, which held worship services every Wednesday, Friday and Sunday, was the only one serving a Christian population of about 1,300 in Naga al-Ghafir village

Source

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቃሊቲ ገብርኤል አጠገብ ሁለት አዳዲስና ድንቅ የሆኑ ዓብያተክርስቲያናት በህልሜ ታዩኝ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2019

ህልሜ ይህን ይመስላል፦

በቃሊት በኩል ሳልፍ መጀመሪያ የታየኝ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ቀለማት የተከበበው ጥንታዊው እና ክቡ የቤተክርስቲያን ህንጻ ነው። “ይህን ቤተክርስቲያን እንዴት እስካሁን አላውቀውም?” በማለት እራሴን በመጠየቅ ዘወር ስል ሌላ ቤተክርስቲያን ታየኝ፤ በቦታው ያለውን የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ህንፃ ይመስላል፤ ነገር ግን እርሱም አዲስ ሆነበኝ እንዴት እስካሁን አላየሁትም? በማለት ተገርሜ በቤተክርስቲያኑ ግዙፍነትና ውበት እጅግ በይበልጥ ተደነቅኩ። “ካሜራ ይዤ መምጣት አለበኝ” እንዳልኩ ህልሙ አለቀ።

ይህን ቪዲዮ ሳዘጋጅ ባለፈው ዓመት ልክ በሁዳዴ ፆም መግቢያ፣ ረቡዕ፣ የካቲት ፯፣ ፪ሺ፲ ዓ.ም ላይ በቃልቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ድንገተኛ የእሳት አደጋ መድረሱን አስታወስኩ።

ይህ ህልም የታየኝ በአቡነ አረጋዊ ዕለት እና (የቆሼን አደጋ አስመልክቶ ቪዲዮዎች አቅርቤ ነበር)በሁዳዴ ፆም ማብቂያ ላይ ነውምን ሊሆን ይችላል? ቅዳሜ የቅዱስ ገብርኤል ዕለት ነውሁሉም ለበጎ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ!

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: