“ሀጊያ ሶፊያ” ወይም “ቅድስት ጥበብ” በሚለው የመድኃኔዓለም ስሙ የተሰየመው ይህ የእግዚአብሔር ወልድ ቤተ ክርስቲያን በቁስጥንጥንያ መንበር ታላቁ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን እጅግ አስደናቂ የሕንጻ ጥበብ የታየበትና የብዙ ቅዱሳን አጽም ያረፈት ታላቅ ካቴድራል ነበረ። በኦርቶዶክሳዊያንና በዓለም የክርስትና ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሥፍራ ያለውና በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የዓለም ቅርሶች አንዱ የሆነው ይህ ቤተ ክርስቲያን በ1453 ዓ ም ቁስጥንጥንያ፡ ያሁና ኢስታምቡል፡ በኦቶማን ቱርክ እጅ ስትወድቅ በሱልጣን መሀመድ ዳግማዊ ትእዛዝ ወደ መስጊድነት ተቀይሯል። ከ1935 ዓ ም እስከ ዛሬም ድረስ ደግሞ ወደ ቤተ–መዘክርነት ተቀይሮ የቀደመ ታሪኩ ብቻ እየተነገረ ለጎብኚ ክፍት ሆኖ ይገኛል። አሁን እብዱ የቱርክ ፕሬዚደንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሙስሊም ወንድሞቹ ግፊት ይህን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን መስጊድ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው አውስቷል።
የክርስቲያን ሃገራትን በመውረር እስካሁን ድርስ ይዛ የቆየችው የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ መጥፊያዋ ተቃርቧል፤ ቁስጥንጥንያንም ለግሪኮችና አርመኖች በቅርቡ ትመልስ ዘንድ ትገደዳልች፤ ስልዚህ በጣም ያቁነጠንጣታል ያለው። እንደ እኛዎቹ ሁሉንም ነገር “ኬኛ” ትላለች። አውሮፓ የእኔ ነው፣ ሰሜን አፍሪቃ የእኔ ነው ትላለች። እንዲያውም “አሜሪካን እኛ ቱርኮች ነን ያገኘነው” በማለት እብዱ ኤርዶጋን በቅርቡ ቀለባብዶ ነበር። “ኬኛ” የመሀመዳውያን መንፍስ እንደሆነ እያየን ነው?
የሀጊያ ሶፊያ ቤተክርስቲያን ወደ ቀደመ ክብሩ መመለስ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኦርቶዶክስ ምእመናን ታላቅ ደስታ የሚሆን ነው። በዓለም ዙሪያ ብዙ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በሀጊያ ሶፊያ ቤተክርስቲያን ሕንጻ አምሳል መሠራታቸውም ለቤተክርስቲያኑ የሠጡትን ትልቅ ሥፍራ የሚያስረዳ ነው። ሀጊያ ሶፊያን መስለው ከተሠሩ ቤተክርስቲያኖች መካከል በግብጽ ካይሮ የሚገኘው የዘይቱን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጵያ የሚገኘው የርእሰ አድባራት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ይጠቀሳሉ። በቱርክ እና ግብጽ የሚገኙት ሙስሊሞችም አብዛኛዎቹን መስጊዶቻቸውን ከዚህ ድንቅ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ኮርጀው ነው የሠሯቸው።
ቀድሞ ቁስጥንጥንያ ዛሬ ደግሞ ኢስትንቡል በመባል የምትታወቀው የግሪኮችና አርመኖች ከተማ ስሟን ያገኘችው „εἰς τὴν πόλιν“ „is tim boli (n)„ ከሚለው የግሪክኛ ቃል ነው። “ከተማው” ወይም “በከተማው” ማለት ነው፤ ለቁስጥንጥንያ። የኦርቶዶክስ ጠላት የሆኑት ቱርኮች ግሪክ ኦርቶዶክሶችን የጎዱ ስለመሰላቸው ነበር ቁስጥንጥንያን ኢስታንቡል ብለው የሰየሙት። ልከ በአገራችንም ከሃዲዎቹ የዋቄዮ አላህ ልጆች ኦርቶድክስ ኢትዮጵያን ያሸነፉ መስሎ ስለታያቸው አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” ብለው ለመጥራት ይታገላሉ፤ ግን ፊንፊኔ የአማርኛ ቃል መሆኑን አላወቁም ነበር።