Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

እስራኤላውያን የኢትዮጵያን መንግስት ለምን ወቀሱ? | ግራኝ አህመድ ከእስማኤላውያን ጋር በጣም በመቀራረቡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2019

ከዓመት በፊት በታህሳስ ቅዱስ ሚካኤል ዕለት፤

ይህን የታህሳስ ፲፪ ፥ ፪ሺ፲ ዓ.ም፡ ዕለትን በደንብ እናስታውስ።” የሚለውን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር። ይህን ባቀረብኩ በአምስት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግሥት ተካሄደ። አዎ አሁንም ያን ዕለት በደንብ እናስታውስ!

እግዚአብሔር አምላካችን፤“በልጆቼ ላይ በደል የሚፈጽሙ ሰዎች፡ ዕምነት የሌላቸው ወይም እግዚአብሔርን ያልተቀበሉት ኃይሎች ለጥፋት ይላኩባቸዋል” ብሎ እንዳስተማረን፡ ኮሎኔል ጋዳፊ እና ከርሱ ጋር ለዘመናት አብረው ሲንደላቀቁ የቆዩት ሊቢያውያንም ለዚህ ክፉ ጊዜ በመድረስ፡ “ጨነቀኝ ጠበበኝ”ለማለት የበቁት፡ በተለይ፡ ኮሎኔሉ በክርስቲያኖች አምላክና በመንፈስ ቅዱስ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ትዕቢት የተሞላባቸውን ስድቦች ለመሠንዘር በመቃጣቱ፡ እንዲሁም የሊቢያው ሕብረተሰብ፡ በተለይ በሃገረ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ለዘመናት ሲፈጽመው ከነበረው ዲያብሎሳዊ አድራጎቱ የተነሳ ነው።

የኢትዮጵያና እስራኤል ግኑኝነት እንዲሻክርና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም እ...1973 .ም ላይ ከእስራኤል እንዲርቁ ብሎም ወደ አረቦች እንዲጠጉና በመጨረሻም እንዲወድቁ ተደርገዋል ይህም የሆነው ኢትዮጵያ በ አፍሪቃ አንድነት ድርጅት ዘንድ ፀረ–እስራኤል የሆነ አቋም እንድትይዝ የጋዳፊዋ ሊቢያ በርሷ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ በመቻሏ ነበር። ልክ ከዚህ ጊዜ በኋላ ነበር ኢትዮጵያችን በጣም አስከፊ በሆነ መልክ እንድትራቆትና እንድትደቅ ሁለት የተዋሕዶ ትውልድ በተከታታይ እንዲጠፋ የተደረገው።

ወንድሞቻችንን በባርነት ከሚሸጡት፣ እህቶቻችንን ከፎቅ እየወረወሩ ከሚገድሉት አርቦች ጋር በማበር የኢትዮጵያን የድጋፍ ድምጽ በተባበሩት መንግሥታት አሁንም እየሰጠን ነው።

የሚያሳዝነው እስራኤልን አለመደገፋችን ሳይሆን አረቦችን መደገፋችን ነው!

አገራችን ከእነዚህ ፍየል አገራት ጋር ማበር አልነበረባትም። ያልተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ ስለሚካሄደው የባርነት ንግድና በእስላም አገሮች በበየቀኑ የሚታየው የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ መውገዝ ነበረበት እንጂ ኢምባሲ ተዛወረ አልተዛወረ እንደ ትልቅ ነገር ተቆጥሮ የተለየ ሤራ መጠንሰስ አልነበረበትም። ትናንት በ ጎላን ከፍታዎች ጉዳይ እንዳየነው አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ጥብቅብቅ ያለቸው ሎቢ የሚያደረጉ አይሁድ አሜሪካውያን ተጽዕኖ ማሳደር ስለሚችሉ ብቻ ሳይሆን፣ በዋናነት በረከቱን እንዳታጣ በመፍራቷ ነው።

በመታየት ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ብልሕነት የጎደለው አሠራር እና ተግባር የሚያስቆጣ ነው፤ እንኳን እኛን እስራኤልንም እያስቆጣ እንደሆነ አሁን እያየነው ነው። እስራኤላውያን ለክፉም ሆነ ለበጎ በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ልዩ የሆነ አትኩሮት ነው ያላቸው።

/ር አህመድ እስራኤልን አንዴም አልጎበኛትም፤ እስራኤላውያን ፖለቲከኞችንም ተቀብሎ አላነጋገረም፤ አረቦችን ግን በየሳምንቱ እየጋበዘ በመኪናው ሳይቀር ያንሸራሽራቸዋል፤ አገሮቻቸውንም በየወሩ ይጎበኝላቸዋል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ አይታወቀም። ሰውዬው ሃገራችንን ለመቅሰፍት እያዘጋጀልን እንደሆነ እንረዳው።

ልክ በ ካታሉኒያ (ስፔይን) + ቫሎኒያ (ቤልጂም) + ባቫሪያ (ጀርመን) + ክሮአስያ (ዩጎዝላቪያ) + ስኮትላንድ (ብሪታኒያ) + ቱርክ + ዩክሬየን (ሩሲያ) + ኩቤክ (ካናዳ)እንደምናየው፡ ኦሮሚያ በተባለው ክልልም የአመጸኞቹ አለቃ ሰይጣን ከእርሱ መሰለፉን የመረጡትን ከሃዲዎች በተዋሕዶ ልጆች ላይ ያምጹ ዘንድ በመቀስቀስ ላይ ነው

ብልሕ እና ፈሪሀ እግዚአብሔር የሆኑትን መሪዎች ለሃገራችን ቶሎ ይስጥልን!

__________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: