ግን ወላዲተ አምላክ ይህን ትበጥሰዋለች ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ይጠብቀናል…
ወገኖች፡ እኅታችንን በደንብ አዳምጧት፤ እየተሠራብን ስላለው ጉድ ሳትፈሩ አዳምጡ፤ ስለዚህ ጉዳይ የማታውቁ መጀመሪያ ሊያስደንግጣችሁ ይችላል፤ ግን ሃቅ ስለሆነ መጋፈጥ ግድ ነው። ኢትዮጵያውያኖችን መቆጣጠር፣ ዘራቸውን ማግኘትና ወደ አውሬነት መቀየር በሳይንሱም በመንፈሳዊውም ዓለም በጣም የሚታገሉለት ሥራ ነው። ሕዝባችን በአካሉም በመንፈሱም በጣም ጥንታዊ የሆነና ከአምላክ በኩል የሆነ ተፈጥሮአዊ መሠረት አለው፤ ይህን መሠረት ዲያብሎስ ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ ይዋጋዋል፤ ልጆቹም አሁን ቴክኖሎጂን እይተጠቀሙ ጥቃቱን በማጧጧፍ ላይ ናቸው። ከሰው ልጅ ጋር የተደባለቁ እንሽላሊቶች በእኛም ውስጥ ሰርገው በመግባት ላይ ናቸው፤ አገራችንን በመምራት ላይ ያሉት የእነዚህ እንሽላሊት ዲቃላዎች ታዛዦች ናቸው። እኔ በግሌ ላለፉት ሃያ ዓመታት በቅርብ እንዳያቸው እግዚአብሔር መርቶኛል፤ ስለዚህ ጉዳይ በጦማሬ ደጋግሜ አቅርቤዋለሁ፤ ወደፊትም አቀርበዋለሁ። ወገኖች፤ እጅግ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ወደ “ህክምና” ቦታዎች አንሂድ።
አንድ ምሳሌ፦ ከጥቂት አመታት በፊት ጸንሳ የነበረችውን፥ የሦስት ወር እርጉዝ ነበረች፥ የአክስቴን ልጅ ለማየት ወደ ቺካጎ ከተማ አመራሁ። አንድ ቀን “የምርመራ ውጤት ለመቀበል ወደ ዶክተሬ አብረን እንሂድ” አለችኝና ወደ ኢትዮጵያዊቷ የሴቶች ሃኪሟ አብረን ሄድን። ገብታ ስትወጣ ተደነጋግጣ እና እንባ በእንባ ሆና አየኋት። ተረጋግተን እንዳለን፡ “ዶክተሬ ልጅሽ ጤናማ ሆኖ አይወለድምና ማስወረደ አለብሽ ብላ ነገረችኝ” አለችኝ። ይህ ውሸት እንደሆነ የእግዚአብሔር መልአክ ወዲያው ነገረኝ። እያጽናናሁ ነገሮችን ማጣራት ጀመርኩ፤ መጀመሪያ በህክምናው በኩል ዶክተሯ ዋሽታታለች፤ በግል በኩል ደግሞ ዶክተሯ እራሷ በሽተኛ የሆነ እና የተኮላሸ ልጅ እንደምታሳድግና ደስተኛ ያልሆነች ግለሰብ እንደሆነች ደረስኩበት፤ ቺካጎ አካባቢ ያላችሁ ታውቋት ይሆናል። ታሪኩን ላሳጥረው፤ የአክስቴ ልጅ ዶክተሯን እንድተተዋት ከአሳምንኳት በኋላ በእናታችን በቅድስት ማርያም ምሕረት ቆንጆና ጤናማ ልጅ ወልዳ በደስታ አሳድገዋለች፤ በቅርቡም አሥረኛ ዓመቱን አክብሯል።