Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 19th, 2019

አዲስ አበባን ከጠላቶቿ የሚጠብቃት አንጋፋ መስቀል በእንጦጦ ተራሮች ላይ ሊሠራ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 19, 2019

እንኳን ለበአለ መስቀል አደረሰን!

ክቡር መስቀሉ የሚሠራው በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ጫፍ ላይ ነው። ከዚህ ተራራ ጫፍ ሆኖ በመላው አዲስ አበባን አካባቢዋ ሊታይ ይችላል፤ ማታ ላይም በደንብ እንዲታይ መብራት ይኖረዋል።

ይህ የተቀደሰ ሥራ ከሁሉም ሥራዎች ቀድሞ በፍጥነት መከናወን ይኖርበታል እላለሁ። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት “እንጦጦ ማርያም ጫፍ ላይ አንድ ትልቅ መስቀል መተከል አለበት” እያልኩ ብዙ አባቶችን በየጊዜው ስወተውት ነበር፤ አሁን ህልሜ ዕውን ሆነ።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ወደ ገዳማቸው መርተውኝ ይህን የመስቀል ሥራ ንድፍ ሳይ፡ ባጋጣሚው፡ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተገርሜም ተደስቼም ነበር። እስከ አሁንም ድረስ ብዙ ነገሮች ይታዩኛል፤ ለምሳሌ፡ በአንድ በኩል ቤተ ክህነት ኃላፊነቱን ወስዳ ቶሎ ማሠራት አለባት እላለሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባውያን፥ ውጭ ካለነው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ባጭር ጊዜ ውስጥ – እንዲያውም ፻፹ ሜትር ከፍ በማድረግ – ማሠራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተዋሕዶ ልጅ በፍጥነት ተረባርቦ በተግባር ሊያውለው የሚገባው ሥራ ነው።

የአቡነ ሃብተማርያምን የፀሎት መጽሐፍ በብሔረ ፅጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሲያከፋፍል የነበረውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንድማችንን፡ “መስቀል አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ጫፍ ላይ ሊተከል ነው፤ ምን ይሰማሃል” ስለው፤ ቪዲዮው ላይ የቀረበውን ግሩም ትምህርት በደስታ አካፍሎኝ ነበር። እርሱም እንደ አብዛኛው/መላው አዲስ አበቤ መስቀል እዚያ የመትከል ዕቅድ አልሰማም። ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

በመጭዎቹ ወራት አዲስ አበባውያን የተዋሕዶ ልጆች በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ይፈተናሉ፦

፩ኛ፦ ለክቡር መስቀሉ ምን ያህል ፍቅር እንዳላቸው በማሳየት

፪ኛ፦ በሊቢያ በሙስሊሞች ለተሰውት ሰማዕታት አስከሬን እንዴት አቀባበል እንደሚያደርጉ

በመቅሰፍት የተመታችው አዲስ አበባ መዳን የምትችለው በፖለቲከኞች የተመሰቃቀለ ጭንቅላት ሳይሆን በክቡር መስቀሉ ነው። ቶሎ እናሠራው! መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!

ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: