የኦሮሞው ዲያብሎሳዊ እንቅስቃሴ የአሜሪካንን ውድቀት እያስከተለ ነው | ፕሬዚደንት ትራምፕ ይህን ተረድተውታል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 15, 2019
ከ ፲፰ ዓመታት በፊት፡ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መስከረም ፩ ላይ፡ በአውሮፕላኖች ጥቃት የጀመረው ታሪካዊ የማስጠንቀቂያ ምዕራፍ አሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድ መከስከስ ቀጥሏል። አውሮፕላናችን እንዴት፣ ለምን፣ በምን እና በማን እንደተከሰከሰ፡ ታወቀ አልታወቀ፡ ምንም የሚፈጥረው ነገር የለም። እውሩን ዓለማችንን ለመቀስቀስ ይህን መሰሉ “አደጋ” መከሰት አለበት። የዓለምን ትኩረት የሚስብው የአውሮፕላን አደጋ ነው። የአውቶብስ አደጋ ያን ያህል አይሆንም።
ይህ የአውሮፕላን አደጋ በኢትዮጵያ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱ፣ እንዲሁም አውሮፕላኑ በተለይ ለአፄ ኃይለ ሥላሴ ውድቀት ምክኒያት በሆነውና ጥልቁ የአጋንንት ዋሻ በሚገኝበት “ቢሸፍቱ ሆራ” መከስከሱ፡ ዲያብሎስ መለቀቁን እና የ ጦርነቱም ሂደት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መቃረቡን ነው የሚጠቁመን።
ከክርስቶስ ተቃዋሚዎች አንዱ የሆነው ግብረሰዶማዊው የፈረንሳይ መሪ፤ ማክሮን ልክ አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ማግስት ሹልክ ብሎ ወደ ላሊበላ መጓዙ (በ አብይ ጾም ከ አብይ አህመድ ጋር) በደንብ የተቀነባበረ ትልቅ ነገር እንዳለ ይጠቁመናል።
የኢትዮጵያ ቴሌኮምን “መውረስ” የምትፈልገዋ ፈረንሳይ ከጀርመን ጋር በማበር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እና አየር መንገድ ከኢትዮጵያ እጅ መንጠቅ ትሻለች። ለገንዘቡ ብለው ሳይሆን “ኢትዮጵያ” ለሚለው ስም። ልክ “ጤፍ” የሚለውን መጠሪያ ሊነጥቁን እንደሚፈልጉት። ቡናውን “ኮፊ” ወይም “አራቢካ” ቢሉት ምንም አይቀርብንም፤ ይውሰዱት።
የተከሰከሰው አውሮፕላን ጥቁር ሳጥን (ብርቱካናማው ሳጥን፡ ጥቁር ይባላል „Orange is the new Black“) እንደተገኘ በመጀመሪያ ወደ ጀርመን ይላካል ተብሎ ነበር፤ ነገር ግን ጀርመን አይ ይቅርብኝ አለች፤ ባለፈው ወር ላይ የጀርመን ፕሬዚደንት አውሮፕላን በአዲስ አበባ “ተበላሽቶ” አልንቀሳቀስም ማለቱ በጣም አስደንግጧቸዋል፤ ለሁለተኛ ጊዜ ነበርና። ጥቁሩ ሳጥን በመጨረሻ ወደ ፈረንሳይ እንዲላክ ተወሰነ። ደም መጣጩ ፕሬዚደንት ማክሮን በመቶ ሃምሳ ስድስት ሰዎች ደም የተቀባውን ሳጥን ወደ ፈረንሳይ ይዞ ወደ ፈረንሳይ ተመለሰ ማለት ነው።
ስለ ጥቁሩ ሳጥን ምርመራ ውጤት እውነቱን እንደማይናገሩ መጠበቅ ይኖርብናል።
Leave a Reply