Boing 747 Max 8 | የማርያም መቀነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሞዴል አውሮፕላን የበረረበት ሰማይ ላይ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2019
የመጀመሪያው ክፍል ላይ፤ የተከሰሰከው አውሮፕላናችን የሄደበትን መስመር (አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ) በቀጥታ ይከታተለው የነበረው ዓለም አቀፋዊ ተቋም ቀርጾት ይታያል፤ ቀጥሎ የተከሰከሰው አውሮፕላን ናሙና ቦይንግ የተባለውና አምራቹ አሜሪካዊ ድርጅት እንደ ማስታወቂያ አድርጎ የለቀቀውን ቪዲዮ ያሳየናል። በዚህም አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዩ ቀለማችን በፀሃይዋ ዙሪያ ክብ ሠርቶ ይታያል።
እረፍት ተነሳን፤ ይህ አደጋ ብዙ ውስብስብ ነገሮችን የያዘ ነው፤ እንዲሁ በድንገት የተፈጸመ ነገር አይደለም። የሰላሳ አመስት አገር ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች አርፈዋል (ነፍሳቸውን ይማርላቸው) – የሁሉም ሃገራት መሪዎች የሃዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፤ ከ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በቀር፤ ስምንት አሜሪካውያን ሞተዋል። ምክኒያቱ ምን ይሆን? ፕሬዚደንቱ የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን? ያውም አውሮፕላኖችን አምራቹ የቦይንግ ድርጅት በአሜሪካ ኤኮኖሚ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለቦይንግ የረጅም ጊዜ ታማኝ ደምበኛ ነው።
በነገራችን ላይ፤ ዶ/ር አህመድ አሜሪካን ሲጎበኝ ፕሬዚደንት ትራምፕ አልተቀበሉትም ነበር።
የሚገርመው ዶ/ር አህመድ በዚህ አጋጣሚ “ጥልቅ የሆነ” የሃዘን መግለጫ ለማስተላለፍ ደቂቃ አልወሰደበትም፤ እንዲያውም ዜናውን የሠበረው እሱ ነው ማለት ይቻላል። የለገጣፎን ቅሌት፤ “አላውቅኩም፡ አልሰማሁም”፤ ኢንጅነር ስመኘው ሲገደል፡ “እንትና የሚባል ሰው ሞተ አሉ” አለ በቀዝቃዛ መንፈስ። በጂጂጋ በከርስቲያኖች ላይ የጭፍጨፋ ጂሃድ ሲካሄድ ሳምንት ቆይቶ ነበር የተነፈሰው።
Leave a Reply