ጀግኖቹ እህቶቻችን ግዙፉን አውሮፕላን በ ኖርዌይ ኦስሎ ማረፊያ እንደ ርግብ አሳረፉት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 9, 2019
ንቅንቅ የማይል ድንቅ አስተራረፍ!፤ የሴቶች ቀን የኢትዮጵያ ሴቶች ቀን ተብሎ ቢሰይም ጥሩ ነው | አዎ! ባለፈው አመት ወደ አረጀንቲና ዘንድሮ ወደ ኖርዌይ፤ ሰማዩ ገደብ ነው፤ የምታኮሩ ናችሁ እህቶች።
የዛሬውን ዕለት ምዕራባውያኑ “የሴቶች ቀን” ይሉታል። ሜዲያው ሁሉ ሊያወራለት የሚገባው ሌላ ታሪካዊ ቀን ነው። እህቶቻችን በኢትዮጲያ አየር መንገድ ሙሉ በሴቶች ብቻ የተከናወነ የበረራ ጉዞ ወደ ኖርዌይ ዋና ከተማ ወደ ኦስሎ አድርገዋል። ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው በዚህ መልክ ሲበሩ።
በሴቶች ብቻ የበረረ ዓየር መንግድ የኢትዮጵያ ብቻ ነው። ለሴቶች መብት እንቆማለን የሚሉት ምዕራባውያን እንኳን ተመሳሳይ ተግባር ፈጽመው አያውቁም፤ ኖርዌይ እራሷ አንዷ ምሳሌ ናት።
ሴቶቻችን በዚህ መልክ ሲጎብዙ ደስ ይላል፤ ያኮራል፣ እሰይ ያሰኛል፣ ሊበረታታም ይገባዋል፤ በአረብ መጋረጃ የተሸፈኑ ግብዝ አስመሳዮች ግን የመከላከያ ሚንስትርና የ ”ስላም” ሚንስትር ሲሆኑ ያንገበግባል፣ ያሳዝናል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ክፉኛ ያሰድባል፣ በታሪክ ያስወቅሳል፣ መቅሰፍት ያመጣል። እስኪ በቅድሚያ ሳውዲ አረቢያ ለሚገኙት የእምነት እህቶቻቸው መኪና ማሽከርከር እንዲፈቀድላቸው ጠበቃ ይቁሙ።
____________
Mario said
ENDE AMORA HO ENDE AMORA HO YEKEREWN ZEFEN ENANTE KETELUT. EGHEZIABHER ETHIOPIAN YEBARKAT.