ያሳዝናል፤ የምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ሜዲያ በ666 ቁጥጥር ሥር ነው። ሜዲያዎቹ እና ሠሪዎቻቸው ፀረ–ክርስቶስ፣ ፀረ–ተዋሕዶ፡ ፀረ–ኢትዮጵያ የሆነ አቋም ነው ያላቸው።
ትክክል ናት እህታችን፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልን!
ዓለም እራስን በሚያስጠላ ቫይረስ ተለክፋለች
“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!” ይላል የሸገር ራዲዮ ተናጋሪ ውስኪ በጠበሰው ጉሮሮው። የትኛዋ ኢትዮጵያ? ሥላሴን እና ማርያምን መስማት የማትሻዋ ኢትዮጵያ? ደግሞ እኮ በጣም የሚያሳዝነው፤ እኅታችን ባሏን እና ወንድማችንን ባጣችበት ማግስት ይህን ነገር መስማቷ ነው፤ በሃዘን ወቅት፤ ያውም ገንዘቧን ከፍላ… አይይይ ግብዝነት…በዲያብሎስ የተመረጡት እራስን በሚያስጠላ ቫይረስ ተለክፈዋል…እንዴት አስቀያሚ ነገር ነው ጃል!
ለምሳሌ የኢትዮጵያ ናቸው የሚባሉት የውስጥም ሆኑ የውጭ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ኢትዮጵያዊ የሆኑትን የተዋሕዶ አጽዋማትንና በዓላትን በማስመልከት በአግባቡ ሲያስተዋውቁ አይሰሙም/አይታዩም። ልብ ብለው ጣቢያዎቹን የሚከታተሉ ወገኖች ከታዘቧቸው ክስተቶች መካከል፤ ለምሳሌ የልደት ወይም የመስቀል በዓል ሲሆን፤ ገንዘብን ከሚመለከቱ ማስታወቂያዎች ጋር የተያያዘ ካልሆነ፡ ስለ በዓላቱ ምንነት ነካ ነካ አድርገው የሚያወሱት ልክ ዕለቱ ሲደርስ ነው። የተዋሕዶ መዝሙራትንማ በጭራሽ አሰምተው አያውቁም። በሌላ በኩል ግን የሙስሊሞች በዓላት ሲቃረቡ ከሁለት ሳምንታት ጀምረው ነው የፕሮግራሞቻቸውን ይዞታ ሁሉ የሚቀያየሩት። እንዲያውም በአረብኛ የተዜመ የእስላም ሙዚቃ በተደጋጋሚ ይቀርባል። የኢትዮጵያ የሆኑትን መዝሙራት አያቀርቡም፤ የጠላት አረብ የሆኑትን ግን ያስተዋውቃሉ። ይህ ታዲያ ቁጣና መቅሰፍት የሚያመጣ መርገም አይደለምን?
ከሁለት ዓመታት በፊት ባቀረብኩት ቪዲዮ የመድኃኔ አለም፣ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ቂርቆስ ጸበል አገልጋይ ወንድማችን የሚከተለውን መረጃ እንደጠቆመኝ አውስቼ ነበር፦
፪ሺ፱ ዓ.ም ላይ ድንቁ የመድኃኔ ዓለም ፍልውሀ ጠበል በቂርቆስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲገኝ፤
(”ሸገር ራዲዮ”፣“ኢቢሲ” እና ”ሙስሊም ፖሊሶች”)በቦታው ተገኝተው፤ “ውሃው በኬሚካል የተበከለ ነው፤ እንዳትጠመቁ! እንዳትጠጡ! ወዘተ” በማለት በሃሰት ለማስፈራራትና ተፈዋሹን ለማባረር ሞክረው እንደነበር፡ ነገር ግን ጠበሉ በሚፈውሳቸው ሰዎች ብዛት ለማፈር እንደበቁ…