Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 3rd, 2019

እኅተ ማርያም “አውሬው ኢትዮጵያውያንን የሚያፈናቅለው የህይወትን ዛፍ በእጁ ለማስገባት ነው” ስትለን፤ አለቃቀሰ የመስጊዱ ጋኔን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 3, 2019

ይህ ሚያጠራጥር አይደለም፤ ምስጢሩ የተገለጠለት የዲያብሎስ ሠራዊት በኢትዮጵያ ላይ አተኩሯል፤ እኛን አስተኝቶ እርሱ ወደ ኢትዮጵያ ጠጋ ጠጋ ማለት ከጀመረ ውሎ አድሯል። አሁን በኢትዮጵያውያኑ ከሃዲዎች እርዳታ ሠራዊቱን በግልጽ በማሰባሰብ እናት ኢትዮጵያን ከብቧታል፣ ሠርጎ ገብቷል፣ ዓለማዊውን የመንግስት እና መንግስት ያልሆነ መዋቅር ሁሉ ተቆጣጥሮታል።

“የታሪክ አባት” በመባል የሚታወቀው ዝነኛው የግሪክ ዓለማዊ ፈላስፋ፤ ሄሮዶትስ እንኳን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር

ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የውሃ ምንጭ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው”።

አዎ! ከሌሎች ብዙ ነገሮች ጋር፡ የውሃው ምንጭ የሚገኝባት እና የህይወት ዛፉ የሚበቅልባት ቦታ ያለው በአገራችን ነው።

የሉሲፈራውያኑ ቀጠሮዋቸው አሁን ደርሷል። ለአዲሱ የምድር መንግስት ምስረታ ይህችን የተቀደሰች ቦታ ከኢትዮጵያውያን እጅ ፈልቅቆ መንጠቅ የመጨረሻው ግባቸው ነው። ለዚህ ግባቸውም መሰናክል የሚሆኑትን ጽኑ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያኑን አንድ ባንድ በማፈናቀል፣ በመመረዝ ብሎም በመግደል ኢትዮጵያን “ለማጽዳት” በመታገል ላይ ናቸው።

ደጋግሜ የምናገረው ነው፡ የ ዶ/ር ማዕረግ ያላቸው ኢትዮጵያዊውያን በየመስኩ ብቅ ብቅ እንዲሉ እየተደረገ ነው (የ ዶ/ር ማዕረግ ከ666 ማኽተሞች አንዱ ነው)። ዶ/ር አብይ፣ ዶ/ር ደብረጺዮን፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ዶ/ር አድሃኖም ወዘተ።

ሰሞኑን በተሠራጨው ዜና፤ “አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በብዛት ተስፋፍቷል” ብለው ሲናገሩ ሰምተናል፤ ከዚህ ዜና ጀርባ የተለመደው ተንኮል አለበት። አውሬው በፈጠረው አጋጣሚ ሁላ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ማንቋሸሽ ወይም መኮነን አለበትና። በረሃብ፣ በበሽታ፣ በጦርነት ወዘተ።

ከሃጢዓታችን የተነሳ በጣም የረቀቀውን፣ ዘላለማዊን እና የእግዚአብሔርን ሕግ የሚከተለውን ሥርዓት ወደ ጎን በማድረግ ሉሲፈራውያኑ ባጠመዱልን ጊዚያዊ ደካማ ርዕዮተ ዓለማት (ካፒታሊዝም፣ ኮሙኒዝም፣ ፌሚኒዝም፣ እስላም፣ ዲሞክራሲ፣ ሊበራሊዝም ወዘተ)ጊዚያችንና ጉልበታችንን እናባክናለን። በዚህም ለአውሬው ልጓም አመች ሰለምንሆን ልክ ጅራቷን ለመያዝ እንደምትሽከረከር ውሻ ምንም ነገር ሳንይዝ እራሳችንን ደግመን ደጋግመን ለመጉዳት እንበቃለን።

አንድን ሕዝብ አዕምሮውን በማጠብ ለመቆጣጠር ያስችለው ዘንድ አውሬው በኢትዮጵያ ላይ የሚጠቀምበት ስልት፦

  • 1. የሕዝቡን ሞራል ማውደቅ (ዘመነ ኃይለ ሥላሴ፦ ድርቅ፣ ረሃብ የነገሠበት)
  • 2. አገሪቷን መተናኮል/ማናጋት የግጭት፣ ቀውስ መፍጠር፣ የጦርነት እና ዕልቂት ዘመን(ዘመነ ደርግ፦ ጦርነት፣ ግድያ፣ ድርቅ፣ በሽታ፣ ስደት የሰፈኑበት)
  • 3. የመረጋጋት ዘመን (ዘመነ ኢህአዴግ/ ዘመነ ሸኽ አላሙዲን፦ ሰላምና የ ኢኮኖሚያዊ እድገት የታየበት)

እንደገና ተመልሶ፦

1. እና 2. የሕዝቡን ሞራል ማውደቅ ብሎም አገሪቷን መተናኮል/ማናጋት የግጭት፣ ቀውስ፣ ጦርነት እና ዕልቂት ዘመን(ዘመነ ግራኝ አህመድ)

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያውያኑን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ብሎም ሃገራቸውን ለመቆጣጠር ላለፉት ፳፯ ዓመታት በመሠረቷቸውና ባደራጇቸው የፌደራል ክልሎች መካከል ግጭቶች ይካሄዳሉ።

በኢትዮጵያ የስልጣን ለውጥ ከተካሄደ ከአሥር ወራት ገደማ በኋላ በሀገሪቷ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ ብዙ ሕይወት የቀጠፉ የኅብረተሰብ ብጥብጦች በመፈጠር ላይ ናቸው። ይህ የተከሰተው ለበርካታ ዓመታት የፖለቲካ መረጋጋት ከሰፈነ በኋላ ነው። ኢትዮጵያ ምናልባት አሁን እስከ መገነጣጠል ድረስ ሊያደርስ የሚችል ጽኑ ብጥብጥ ሊያጋጥማት ይችላል። እነዚህም ግጭቶች ድርቅን፣ ረሃብን፣ በሽታን እና ሞትን ይወልዳሉ። ይህም ሁኔታ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ማለቅ፣ መፈናቀል እና መሰደድ ምክኒያት ይሆናል። ይህን የሚታዘበው የዓለም አቀፋዊው ማሕበረሰብም ለ ”እርዳታና” “ሰላም ለመፍጠር” ያዘጋጀውን ሠራዊት በጣልቃ ገብነት ወደ ኢትዮጵያ ይልካል፤ የመረጠውንም ተዋሕዶ ያልሆነ አዲስ ነዋሪ ያሠፍራል፤ በዚህም የህይወት ዛፍ የምትገኝበትን ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራል ማለት ነው።

አዎ! እግዚአብሔር ለአባታችን ኖህ የገለጠለትንና የማርያም መቀነት ያረፈባቸውን የኢትዮጵያ ቀለማት ከስነደቅ ዓላማችን ላይ ይሠርዙ ዘንድ የሉሲፈርን ኮከብ እንዲያሳርፉበት እንዳዘዟቸው፤ አሁንም የህይወትን ዛፍ መቀዳጀት አላማቸው እንደሆነ የሚጠቁመንን ሰንደቅ ዓላማቸውን („ኦሮሞ” የሚባሉት የሚይዙትን) በማስተዋወቅ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያውያን የእግዚአብሔር ልጆች ኮከቡ ከባንዲራቸው ላይ እንዲነሳ ሲሹ፥ ሉሲፈራውያኑ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ደግሞ ባንዲራውን በዋቄዮ አላህ ባለዛፍ ባንዲራ ለመተካት እየታገሉ ነው።

ታሪክ እንደሚያስረዳን፤ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሊወገዱ ጥቂት ዓመታት ሲቀራቸው፡ ሉሲፈራውያኑ በሰሜን ኢትዮጵያ (የህይወት ዛፍ በሚገኝበት አካባቢ)ሃይለኛ ድርቅ እንዲፈጠር አደረጉ፤ በዚህም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጡ፤ ኢትዮጵያ ሞራሏ ወደቀ። ኢትዮጵያ የሚለው ስም የረሃብ ተመሳሳይ ቃል መግለጫ ሆነ።

በወቅቱ የነበሩ ብዙ የዓይን ምስክሮች ስለዚህ ጉዳይ እንዳጫወቱኝ፤ ይህ ዜና በእነ ቢቢሲ እና የተባበሩት መንግስታት አማካኝነት በመላው ዓለም እንዲሠራጭ ተደረገ፤ ብዙም ሳይቆይ፤ የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ የናቶ ሠራዊት በትግራይ እና ወሎ እንዲሠፍር ተደረገ። (የናቶ ሠራቲ እዚያ ምን ያደርግ ነበር??? ጸሐፊዎቻችን እና የሜዲያ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ለምን እንዳልተናገሩ/ እንደማይናገሩና እንደማይጽፉ በጣም ነው የሚገርመው።) እንግዲህ አሁን ለሚካሄደው ትግላቸው በወቅቱ መርዛማ ዛፋቸውን መትከላቸው ነበር ማለት ነው። የ፶ ኛው ዓመት ኢዮቤልዩአቸውን እየጠበቁ ነው።

ሆኖም ብዙ ልንጎዳ እንችላለን፤ ነገር ግን ከአለቃቸው ከዲያብሎስ ጋር አንድ በአንድ እየተሠባበሩ የራሳቸውን መውደቂያ ያዘጋጃሉ እንጅ አገራችንን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሯት አይቻላቸውም።

ለማንኛውም፤ አባቶቻችንን ፍዬል ጣልያንን ያንበረከኳት በሁዳዴ ጾም ነበርና፥ እኛም በዚህ የአብይ ጾም ወቅት የዲያብሎስን ሽንገላ መቃወም እንዲቻለን፣ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ መልበስ ያስፈልገናል። ወገብን አጥብቆ ለመያዝ ዝናር እጅግ አስፈላጊና በጦርነት ሥፍራ መታጠቅ እንደሚገባ እንዲሁ፣ ለመንፈሳዊ ውጊያ እውነትን እንደዝናር መታጠቅ ይገባናል። በውጊያው ውስጥ ከእውነት በቀር ሌላ ነገር መቀላቀልና መሸቃቀጥ ፈጽሞ አይገባንም። በውጊያው ውስጥ ከጭካኔና ካለመራራት ይልቅ እውነተኛ የሆነውን የክርስቶስን ጠባይ በሕይወታችን ገንዘብ ማድረግ ይገባናል። እውነትን እየሠዉ ውጊያ የለም፣ ከእውነት እየቀነሱ ውጊያ የለም፣ በእውነት ላይ እየጨመሩ በመሸቃቀጥ ውጊያ የለም፤ እውነት እንደዝናር ታጥቆ በመዋጋት ግን እውነተኛ ውጊያና ድል በዚያ አለ።

የተጠራነው፣ “ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አይደለም(፪ቆሮ. ፲፫፥፰)፤ ማናቸውንም ነገሮች መፈጸም ያለብን በእውነት መንገድ ብቻ በመሄድ ነው። ያለእውነት ሰይጣንንም ሆነ አገልጋዮቹን ሐሰተኝነታቸውን በማጋለጥ ድል ልንነሣቸው አንችልም። በማኅበረሰባችን እሳቤ “ዋሽቶ ማስታረቅ” እንደመልካም እሴት ይቆጠራል፤ ነገር ግን ያለእውነት የሚሆነው ማናቸውም ትጥቅ ለዲያብሎስ ፈንታ የመስጠት ያህል ምቹ ነው።

____________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ ጣልያንን ያሸነፈቻት በሁዳዴ ጾም ወቅት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 3, 2019

እየጾመ የተዋጋው የኢትዮጵያ ጦር ፤ የዐድዋ ጦርነት የተካሔደው በገና እና በሑዳዴ አጽዋማት ወቅት ነው

የዓምባላጌ እና የመቐሌው ውጊያዎች የተካሔደው በገና ጾም ሲኾን ዐድዋ ላይ በአሻሾ፣ ራዕዮ እና ሰማያታ ተራራ እና ሜዳ ላይ የካቲት ፳፫ ቀን የተደረገው ዋናው የዐድዋ ውጊያ ደግሞ የተደረገው በሑዳዴ ጾም ነው። የያኔው ጾም ደግሞ እንዳሁኑ አልነበረም። ምእመኑ ቀኑን ጾሞ ምሽት ላይ ነበር የሚመገበው።

በዚህ ምክንያት “ሠራዊቱ እንዳይደክምብኝ በማለት ንገሠ ነገሥቱ ዐፄ ምኒልክ፣ ለጦርነቱ ሲባል የዘንድሮውን ጾም እንዳይጾም ዘማቹን ወታደር ይፍቱልኝ። ጾሙ ለወታደሮቼ ይሻርልኝ፤” ብለው አቡኑን ጠይቀው ነበር። አቡነ ማቴዎስ ግን እምቢኝ አሉ። “ወታደርም ቢኾን፣ ዘመቻም ቢኾን ጾምን ሻሩ አልልም፤” ብለው እምቢ አሉ።

ጳውሎስ ኞኞ፣ “ዐጤ ምኒልክ” በሚለው መጽሓፉ ላይ ይህን አስገራሚ ታሪክ እንዲህ አስፍሮታል፡

የዐድዋ ጦርነት የተካሔደው በገና እና በሑዳዴ ጾም ነው። ክርስቲያኑ ዘማች በዚያን ግዜ እንደነበረው አጿጿሙ ራቱን በልቶ እስከሚቀጥለው ጀምበር መጥለቅ ምንም አይቀምስም። ውኃ እንኳን አይጠጣም ነበር። ይህን የተገነዘቡት ዐጤ ምኒልክ ጳጳሱን አቡነ ማቴዎስን፦ ጦርነት ላይ መኾናችንን ያውቃሉ። ሠራዊቱ በጦርነቱም በጦሙም ተደራራቢ ጉዳት እንዳይደርስበት ያገኘውን እየበላ እንዲዋጋ ይፍቱት። ቢያስፈልግ ከጦርነት መልስ ይጾማል፤ ቢሏቸው አቡኑ፣ አልፈታም፤ ብለው እምቢ አሉ። ምኒልክም በዚህ አዝነው፣ እግዚአብሔር የየዋህ አምላክ ይርዳው፤ አሉ።” ይላል።(ገጽ ፻፸፪)

ሌላኛው ደራሲ ደግሞ፣ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ዐፄ ምኒልክን፣ “ስለ ኢትዮጵያ የሚዋጋው እግዚአብሔር ነው። ሰልፉ የሰው ሳይኾን የእግዚአብሔር ነው። ድሉም የኢትዮጵያ ይኾናል፤“ ብለው መናገራቸውን ዘግቧል። አቡኑ ተሳስተው ይኾን? ያነ የኾነውን እስኪ እንመልከት?

የካቲት ፳፪ ቀን ሌሊት የጣልያን ጦር ለውጊያ ከመነሣቱ በፊት ከባድ ድግስ ተዘጋጅቶለት በፌስታ ነበር። የጣልያን ወታደሮችም የኢትዮጵያን ሠራዊት ለመውጋት ከሳውራ ተነሥተው ገንዳብታ ሲደርሱ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ነበር። ውጊያ ከመግባታቸው በፊት ዕረፍት እንዲያደርጉና በሚገባ እንዲመገቡ ታዘዙ። በቆርቆሮ የታሸጉ ምግቦችን በልተው የሚበቃቸውን ያህል ውኃ ጠጥተው ዝግጅታቸውን አጠናቀው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወዳለበት መሥመር በደፈጣ መግባት ጀመሩ።

የኢትዮጵያ ጦር መኰንኖች ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ላይ ነበሩ። የጣልያኖች የተኩስ ድምፅም እንደተሰማ ኢትዮጵያውያኑ የጳጳሱ አቡነ ማቴዎስን መስቀል እየተሳለሙ ወደ ውጊያ ገቡ። እህል አልቀመሱም። ውኃም አልጠጡም። በጥድፊያ ወደ ሰልፋቸው አመሩ። ውጊያው ተጀመረ። የጣልያን ጦር በሦስት አቅጣጫ ተለጥጦ በመምጣቱ ጦርነቱ ከጠዋቱ ዐሥራ ኹለት ሰዓት ጀምሮ ቀኑን ዋለ።

የኢትዮጵያ ጦር ቀኑን የተዋጋው እህል ውኃ ሳይቀምስ ነበር። ጦርነትን ምክንያት አድርጎ የገናን ጾም ሳይሽር፣ አሁንም ውጊያውን ምክንያት አድርጎ ሁዳዴን ጾም ሳይሽር እየጾመ ተዋግቶ የኢትዮጵያ ሠራዊት ደል አደረገ። አቡነ ማቴዎስ አልተሳሳቱም ነበር። ጳጳስ ይሉሃል እንዲህ ነው። ሐሞተ ኮስታራ። የእምነት ሰው።

አቡነ ማቴዎስ የዐድዋን ጦርነት ከሚመሩት ሰዎች አንዱ ነበሩ፤

አቡነ ማቴዎስ በመንፈሳዊው ጉዳይ ብቻ ሳይኾን የኢትዮጵያን ጦር የበላይ ኾነው ከሚመሩትና ከሚያስተባብሩት አዝማች መሪዎች ውስጥ አንዱ ነበሩ። የጦር ዕቅዱ ላይ ከጦር መሪዎቹ ጋራ አብረው ይመክራሉ። የጦር ውሎ ግምግማ ላይም ተሳታፊና ዋነኛ ተዋናይና ገምጋሚም ነበሩ። ለምሳሌ፣ የዓምባላጌን የጣልያን ምሽግ የሰበሩትና ድል ያደረጉት ጀግናው ራስ መኰንን መቐሌ ላይ ያን መድገም ባለመቻላቸው ራስ መኰንን ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ ካቀረቡት መሀል አንዱ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ።

ዐፄ ምኒልክም ከባድ ውሳኔ ሲያጸኑ አቡነ ማቴዎስን አማክረው ነበር፤

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ኢጣልያን ድል ካደረጉ በኋላ ምርኮኞችን በተመለከተ በኢትዮጵያ አመራሮች መካከል ከፍተኛ ክርክር ተደርጎ ነበር። የመጨረሻውን ውሳኔ ንጉሡ የወሰዱት አቡነ ማቴዎስን አማክረው ነበር።

ለጥቁር ሕዝብና በቅኝ አገዛዝ ሥር ለነበሩ ወገኖች ኹሉ የተስፋ ብርሃን የኾነው የዐድዋ ጦርነትና ድል አንዷና በዘመኑ ቋንቋ ወሳኟ መሐንዲስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን! የነጻነታችን እናት! የኢትዮጵያ ባለውለታ! ተገቢው ክብር ይሰጣት:: ውለታዋ አይዘንጋ! ዕዳ አለብን ጎበዝ!

_________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: