ጉድ በታናሿ ብሪታኒያ | ክርስቲያኑ መጽሐፍ ቅዱስን ስለሰበከ ታሠረ ፥ ሙስሊሙ ለፖሊስ ስለጠቆመበት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2019
አንድ አፍሪቃዊ የጎዳና ሰባኪ ወንጌልን ለእግረኞች በሚያካፍልበት ወቅት “ዘረኛ የሆነ ስድብ ተሳድበሃል” በሚል ወቀሳ በእንግሊዝ ፖሊሶች ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህ ቪዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን ጊዜ በላይ ተጋርቷል። ቪዲዮው በ ሰባኪው እና ሁለት የፖሊስ መኮንኖች መካከል ያለውን ልውውጥ ያሳያል። በዚህ ምልልስ ሰባኪው “ከፈልጋችሁ ልታሰሩኝ ትቻላላችሁ”፤ ብሎ ለ መኮንኖቹ ሲነግራቸው ይሰማል። ቀጥሎም“ህይወታችሁን ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስጡ” አላቸው። ከፖሊስ መኮንኖቹ አንዱ፡ “ምን እያደርግክ ነው እዚህ?“ ብሎ ሲጠይቀው፥ ሰባኪው፤“እየሰበኩ ነው” በማለት መለሰለት።
ከቪዲዮው እንደሚሰማው መኮንኑ ሰባኪውን፡ “ሂድ ከዚህ ቦታ!” አለው። ሰባኪውም ከቦታው ንቅንቅ እንደማይል ሲነግረው፤ ፖሊሱ “እንግዲያውስ ሰላም እየነሳህ ስለሆነ ህግ ጥሰሃል በቁጥጥር ስር ትውላለህ”፡ አለው። ሰባኪው በምላሹም፡ “አልሄድም፤ ምክንያቱም ለእነርሱ እውነትን መናገር ስላለብኝ ነው። ኢየሱስን ብቸኛ መንገድና እውነት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ብቸኛ መንገድና እውነት ሕይወትም ስለሆነ ነው። “መኮንኑም፡ “ይሄን አደንቃለሁ፤ ግን ማንም ሊያዳምጠው አይፈልግም“በማለት መለሰለት።
ሰባኪውም፡ “እርስዎ መስማት አይፈልጉም? ሲሞቱ ይሰሙታል።” በማለት መለሰለት። በዚህ ጊዜ መኮንኖቹ ሰባኪውን ገስጠው አሠሩት፤ መጽሐፍ ቅዱሱንም ወሰዱበት። ሰባኪውም፡ መጽሐፍ ቅዱሴን አትውሰዱብኝ” ሲል፥ ሌላኛው ፖሊዝ “ይህን ዘረኛ ከመሆንህ በፊት ይህን ቀድመህ ልታስብበት ይገባህ ነበር።” አለው።
የዓይን ምስክሮች እንደጠቆሙት፤ ብዙዎች ለዘመናት ሰበካ በሚያደርጉበት በዚህ በለንደን ሳውዝጌት ባቡር ጣቢያ አካባቢ፡ ይህ አፍሪቃዊ ባለፈው ቅዳሜ እንደተለመደው ሲሰብክ አንድ ሙስሊም ወደ እርሱ መጥቶ መጽሐፍ ቅዱሱን አንቋሽሾ እና ሰባኪውንም ሰድቦ ካለፈ በኋላ ወደ ፖሊሶች ሄዶ “ይህ ጥቁር ክርስቲያን እስልምናን ተሳድቧል” በማለት ክስ አቀረበ(ይህ በአላህ እና ዋቄዮ ባሪያዎች ዘንድ የተለመደ ነገር ነው፤ በዳዮች ሆነው ተበዳዮች…)፤ ፖሊሶቹም በጥድፊያ ወደ ክርስቲያኑ ሰባኪ አመሩ…
ዋውው! በአንድ ጤናማ ማሕበረሰብ ሊታሠር የሚገባው ሙስሊሙ ነበር…ግን ታላቋ ብሪታኒያ እየወደቀችና እያነሰች ነው…ተበለሻሽታለች። በዋና ከተማዋ በለንደን ፓኪስታኒውን ሙስሊም በከንቲባነት ካስቀመጡበት ጊዜ አንስቶ በከተማዋ በጣም የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ ሥራ እየተሠራ ነው። እስኪ ይታየን፤ ይህ አፍሪቃዊ ክርስቲያን ከናይጄሪያ ነው፤ በናይጄሪያ ወንድሞቹ በሙስሊሞች እየጨፈጨፉ ነው። ወደ እንግሊዝ መጥቶ ደግሞ የሳጥናኤል አሸከሮች ዔሳውያን ፖሊሶች እና መሣሪያዎቻቸው በሆኑት በእስማኤላውያኑ የዱር አህዮች እግር ይረገጣል።
አቤት ቅሌት! በእውነት እጅግ በጣም የሚገርም ዘመን ላይ ነን።
Leave a Reply