ሳውዲ ሴቶች ወደ አውሮፓ በብዛት በመሰደድ ላይ ሲሆኑ፡ ፳ሺህ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ደግሞ እንደ ከብት ለሳውዲ ሊሸጡ ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 18, 2019
ይህ ወገኖቼ ካለፈው ዘመን የከፋ ዘመናዊ ባርነት ነው
የግራኝ አህመድ መንግስት በመጭው መጋቢት ወር ብቻ ሃያ ሺ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ለሳውዲ አረቢያ ለመሸጥ መወሰኑን የሳውዲ ሜዲያዎች ዘግበዋል።
በ ፳፩ ኛው ክፍለ ዘመን ወገኖቻችን ወደ እስላም ሃገራት ለሥራ የሚያደርጉት ጉዞ፡ በ ፲፰ ኛው ክፍለዘመን ጫካ ለመመንጠር በባርነት ተገደው ወደ አሜሪካ ከተወሰዱት አፍሪቃውያን ጋር ተመሳሳይነት አለው፤ በአረብ ሃገራት የሚታየው የሥራ ባሕርይ እንዲያውም ከዚያ በጣም የከፋ ነው። ከሦስት መቶ ዓመታት በፊት፡ እንደ አሁኑ በቂ መረጃ በሌለበት የጨለማው ዘመን፡ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው አፍሪቃውያን ተገደው የተወሰዱ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ሁሉም ነገር ግልጥ ብሎ በሚታይበት ዘመን የራሳችን ሰዎችና መንግስታችን የአገሪቷን ዜጎች ለጠላት ይሸጣሉ፤ ለሰላሳ አመታት ያህል ባልተቋረጠ መልክ።
ነፃ ሆነው የተፈጠሩት ኢትዮጵያውያን ለዚህ ዓይነቱ ባርነት በ ፳፩ ኛው ክፍለ ዘመን መጋለጣቸው እጅግ በጣም ነው የሚያሳዝነውና የሚረብሸው። በተለይ ለታሪካዊ ጠላቶቻቸውና ለእግዚአብሔር አምላካቸው ጠላቶች መሆኑ በይብለጥ የሚያስቆጣ ነው።
ባለሥልጣናቱ በእህቶቻችን ገንዘብ መሥራቱን ቀጠሉበት ማለት ነው፤ “በቃን!” ለማለት በቂ ጊዜ ነበራቸው። ዛሬ በዚህ ጽንፈኛ ተግባር ላይ የተሠማሩትን ባለሥልጣናት እና ተቋማት እግዚአብሔር የሚገባቸውን ፍርድ ይስጣቸው!!!
Leave a Reply