Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ታዋቂው የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ግብረ-ሰዶማውያንን በማውገዛቸው የ፯ወር እሥራት ተፈረደባቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 31, 2019

በደቡባዊው የፔሎፖኔ ክልል የካላቭሪታ እና አይጊያሊያ ጳጳስ የሆኑት አምቭሮሲዮስ ለሰባት ወራት እንዲታሠሩና እና ለሦስት ዓመትም ከሥራቸው እንዲታገዱ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ዋውው! ልክ በእርኩሶቹ ፓኪስታን እና ሳውዲ አረቢያ እንደሚታየው፡ በአውሮፓም “መሳደብን የሚከለክል ህግ” በሥራ ላይ እየዋለ ነው ማለት ነው

በዓለማችን ላይ አሁን ከሚታዩት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች አንዱ የግሪኩ ጠቅላይ ሚንስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ነው። ኮሙኒስቱ //ር አሌክሲስ ሲፕራስ ከ አራት ዓመት በፊት ስልጣኑን ሲረከብ በመጽሐፍ ቅዱስ መሃላ አልፈጽምም ለማለት የደፈረ የመጀመሪያው ግሪካዊ መሪ ነው።

ከግሪክ እስክ አሜሪካ፡ ከቬኔዝዌላ እስከ ኢትዮጵያ ስልጣን ላይ እየወጡ ያሉት በፖለቲካው ዓለም “ወጣት” የሚባሉት ናቸው። ለበጎም ይሁን ለክፉ፡ ትኩስ የወጣት ደም ማሕበረሰብ ውስጥ የጃጀውን አሮጌ ደም ለማዘዋወር/ለማመስቃቀል አስተዋጽዖ ያበረክታል። አሁን በመላው ዓለም የምናየው ይህ ነው።

ልክ እንደ ዶ/ር አብይ አህመድ፤ ጠ//ር አሌክሲስ ሲፕራስም በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ይዘምታሉ፤ ውድቀታቸውም ይህ ይሆናል፤ ምክኒያቱም የተላኩት ለሌላ ዓላማ ነበር፤ እምነተቢስ ስለሆኑ የተላኩበትን ዓላማ እነርሱ እራሳቸው አያውቁትም እንጂ የተላኩት የክርስቶስን ልጆች ከሚተናኮሉት ሉሲፈራውያን ጋር እርስበርስ እንዲፋለሙ ነው። ከእባብ መርዝ መዳኛው እራሱ የእባቡ መርዝ ነውና፤ ጃዋር የሚባል መርዛማ እባብ ከነደፈን አላሙዲን የተባለ መርዛማ እባብ መድኃኒት ይሆናል።

[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፩]

፳፮ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።

፳፯ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤

፳፰ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥

_________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: