Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • January 2019
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  28293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

የእኅተማርያም እህቶችና ወንድሞች | “ዶ/ር አብይ ጥምቀትን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ፀረ-ተዋሕዶ ነው”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 27, 2019

እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን ከተናገሯቸው ነገሮች መካከል፦

 • + /ር አብይ የተናገሩት እንኳን አንድ አገር እመራለሁ ከሚል ሰው፤ ከአንድ ምዕመን እንኳን የማይጠበቅ ነው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው

 • + ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ማለታቸው፤ ሃይማኖታችን ጠፍቶ ሁሉ ነገር እንደ ፌስቲቫል እንዲሆን ነው

 • + እራሱን የመቻል ብቃት ያለው ቅዱስ ታቦት ለምንድን ነው በታጠቁ ወታደሮች ታጅቦ እንዲሄድ የሚደረገው? ምን ዓይነት ቅሌት ነው?!

 • + አብይ አህመድ ኦርቶዶክስን ወዴት እየወሰደው ነው? የሚለውን ጥያቄ ሁሉም ሰው ሊጠይቀው የሚገባው ነገር ነው። ወዴት ወዴት ፎቀቅ እያልን ነው? ሃይማኖቱን ሁሉ ጨምቀው አንድ ሃይማኖት ለመፍጠር እየታገሉ ነው፤ አባቶች ስለዚህ ጉዳይ መናገር ይጠበቅባቸዋል።

 • + ትናንትና ስልጣን ላይ የወጣ ሰው እንዴት ይህን ያህል ተዋሕዶን ደፍሮ ሊናገር ቻለ?!

ቃለ ሕይወት ያሰማለን፤ እኅቶች እና ወንድሞች፤ ጀግኖች! ምን አለ እያናዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ እንደ እናንተ መሆን ቢችል! ቸኩለው “አብይ አብይ” ሲሉ የነበሩት የአንዳንድ አባቶች ዝምታ ያደነቁራል። እየተካሄደ ስላለው ነገር እንዴት ዝም ማለት ይቻላል?

ዔዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያኑ ሕዝባችንን ከውስጥ እስከ ውጭ አብጠርጥረው አጥንተውታል፤ ቀስ በቀስ በማለማመድ ሕዝባችንን ፀረክርስቶሱን እንዲቀበል ለማድረግ ማዘጋጀት ከጀመሩ ቆይተዋል። ምን እንደሚፈልግ፣ ምን መስማት እንዳለበት፣ ማንን መቀበል እንደሚችል በደንብ አውቀውታል። ስለዚህ ሕዝባችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ይችሉ ዘንድ ሰዎች እራሳቸው ፈቃደኛ ሆነው መርዛቸውን እንዲቀበሉላቸውና የፈጠሩት አጋጣሚም እንዳያመልጣቸው አሁን በጣም በመጣደፍ ላይ ናቸው።

ልክ ከዚህ በፊት ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም እና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳደረጉት እነ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊም (ስሙ ላይ በደንብ እናተኩር፤ ቍልፍ ሚና ይጫወታልና) በሲ.አይ.ኤ እና ኤፍ..አይ እንዲሁም በእንግሊዝ የስለላ ድርጅቶች አማካኝነት ስልጠናን አድረገዋል። እነዚህ ድርጅቶች የ666ቱ ዋና ተዋንያን ናቸው። መሪዎቻችን የእነርሱን ትዕዛዝ መቀበል አለባቸው፤ የማይቀበሉ ከሆነ፡ ልክ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ ይገደለሉ።

እነ ዶ/ር አብይ አኅመድንና አቶ ለማ ለገሰን ሰልጣን ላይ ለማውጣት የወሰኑት ገና ከ፳፯ ዓመታት በፊት ነበር፤ ኦነግ የኢሕአዴግ መንግስትን ለቅቆ እንዲወጣ የተደረገው በሉሲፈራውያኑ ፕላን ነው፤ ምክኒያቱም፡ ፩ኛ. በቋንቋ የተከፋፉሉ ክልሎች ተመሥርተዋል፤ “እስከ መገንጠል” የሚለው ሕገ መንግስት በመጽደቁም ግቡን መትቷል፣ ፪ኛ. የመስተዳደሩን ኃላፊነት በተለይ ለትግርኛ ተናጋሪዎች በማስረከብ የተዋሕዶ የጀርባ አጥንት በሆኑት ትግሬዎች ላይ መጥፎ ስም በመስጠትና በመኮነን ሕዝቡ ጥላቻ እንዲኖረው ለማድረግ ይችላሉና ነው። በ፳፭ ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና ሁኔታ መረዳት የማይችል አንድ ትውልድ ተፈጥሯልና። ይህን አሁን በተከታታይ በግልጽ የምናየው ነው።

ኢትዮጵያውያን መስማት የሚፈልጉትንና ማየት የሚመኙትን ድራማ እንዲነግሯቸውና እንዲያሳዩአቸው እነ ዶር አብይ አህመድን መረጡ፤ ግን እነርሱን በደንብ ከማስተዋወቃቸው በፊት፡ ሉሲፈራውያኑ ያዘጋጇቸው ምሁራኑ እና ሜዲያዎቹ “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” አሉ (መንግስቱ ኃይለማርያምም “ያለምንም ደም፤ ኢትዮጵያ ትቅደም! እያለ ነበር ሥልጣን ላይ የወጣው) ፣ “ባንዲራችን ላይ ኮከቡ መስፈሩ ተገቢ ነው አይደለም ” እያሉ የመረጧቸውን ሰዎች በማወያየት ኢትዮጵያውያንን አጠኑ፤ ሕዝቡ የት ድረስ አብሯቸው ሊጓዝ እንደሚችል ተገነዘቡ።

በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተጠሙ አገር ወዳዶቹ ኢትዮጵያውያን በየዋህነት “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” የሚለውን መፈክር አብረው ማሰማት፣ ኮከቡ ያላረፈበትንም ባንዲራ በየአደባባዩ ይዘው በመውጣት መፈንደቅ ጀመሩ። አሁን ይህ አገር ወዳድ የሆነው ኢትዮጵያዊ፡ ልክ፡ ቀደም ሲል “ነፍጠኛ” በማለት አማርኛ ተናጋሪውን ሲኮንኑት እንደነበረው፤ አሁን ደግሞ “ወያኔ” በማለት ትግርኛ ተናጋሪውን መኮነን እንዲበቃ ተደረገ፤ አንጎሉ ታጠበ። “ነፍጠኛ” እና “ወያኔ” የሚሉት የመወንጀያ ቃላት መግቢያ ሆኖ ለ “ተዋሕዶ ክርስቲያኖች” የተሰጠ ኮድ ናቸው።

የእኅተማርያም ማሕበር አባላት ግሩም በሆነ መልክ በትክክል ጠቁመውታል፤ ኮከቡ ያላረፈበትን ባንዲራችንን በየቤተክርስቲያኑ መሰቀል ጀምረው ነበር፤ አሁን ግን ሁሉም ኮከቡን እንደገና እንዲለጥፉ ታዘዋል።

/ር አብይ ሥልጣኑን በተረከበ ማግስት፤ “እውነት ሕዝባችንን ለማገልገል የመጣ ሰው ከሆነ እነዚህን ሦስት ነገሮች በፍጥነት መፈጸም ይኖርበታል” ብዬ ነበር፦

 • ፩ኛ. በቋንቋ የተከፋፈልውን የክልል ሥርዓት እንዲያፈርስ

 • ፪ኛ. ኮከቡን ከባንዲራችን ላይ በአዋጅ እንዲየነሳ

 • ፫ኛ. ከአረብ አገሮች ጋር ያለንን ጥብቅ ግኑኝነት እንዲያላላ

አመት ሆነው፤ ግን ሦስቱንም ጉዳዮች እስካሁን ለማስተካከል ሙከራ አላደረገም፤ እንዲያውም ሁኔታዎችን ወደ ባሰ መንግድ እየመራቸው ነው፤ በዚህም ሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን፣ አረቦችና የተባበሩት መንግስታት ፈላጭ ቆራጮች ታይቶ በማይታወቅ መልክ እያጨበጨቡለት ነው። ይህም በጣም ስላደፋፈረው፡ መጀመሪያ በትግርኛ ተናጋሪዎች ላይ ሤራ መጠንሰስ ጀመረ፤ አሁን ደግሞ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዞረ። አቤት ድፍረት!

የእኅተ ማርያም እኅቶችና ወንድሞች ያሉት ትክክል ነው፤ ሁኔታዎችን በደንብ የሚቃኝ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጅ ሊወስደው የሚገባው ግንዛቤ ነው። አዎ! /ር አብይ እና አጋሮቹ የ666ቱን ማህተብ ካልተቀበሉ በቀር ሥልጣን ላይ አይወጡም፤ አይቆዩምም። ሥልጣን ላይ ከወጡ ደግሞ የሉሲፈራውያኑን ትዕዛዝ መቀበል ግድ ነው፤ አሻፈረን ካሉ የመለስ ዜናዊ ዓይነት ዕጣ ስለሚደርሳቸው ይፈራሉ፤ ስለዚህ ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረተዋሕዶ የሆነውን አጀንዳ የማራመድ ግዴታ አለባቸው ማለት ነው። እንደነርሱ ከሆነ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነችው ተዋሕዶ መጥፋት አለባት፤ እርሷ ከጠፋች የአንድ ዓለም ሃይማኖት እና መንግስት መመስረት ይቀላቸዋል።

ግን አይሳካላቸውም፤ ወዮላቸው! ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር አምላክ የቀዳውን ቪዲዮ አንድ ባንድ ተንትኖ በኋላ ያሳያቸዋል። እነርሱን አያድርገን!

አዎ የሚያምን ከማያምን ጋር ምንም ሕብረት ሊኖረው አይገባም፦

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥ ፲፬፡ ፲፭]

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥ ፴፬፡፴፮]

በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።

__________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: