በኢዮጵያ ቀለማት በተዋበው ድንቅ የቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ፡ “መልክአ እስጢፋኖስን”፡ እንስማ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 25, 2019
“እውነት ይህ በኢትዮጵያ ነውን?” ይሉኛል የሥራ ባልደረቦቼ፡ ደግመው ደጋግመው በመደነቅ። የሚቀጥለው ዓመት አብረውኝ ለመጓዝ የተመኙ ሦስት ባልደረቦች አሉ።
የአዲስ አበባ መኪና ቁጥር ለአደጋ እና ለሕይወት አሳሳቢ በሆነ መልክ በጣም እየጨመረ መጥቷል።
ሁልጊዜ ይደንቀኛል፤ ብዙ ተሽከርካሪዎች(ባቡሩንና አውሮፕላኖችን ጨምሮ)በሚገኝባት በዚህች አማካይ ቦታ ላይ ከመንገዶቹ አምልጠን ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያ ግቢ ውስጥ ስንገባ ያለው ፀጥታ እና ሰላም በእውነት ገነታዊ ነው።
ሌላው ደግሞ፤ ባቅራቢያዋ “መናፈሻ” የተባለ አንድ የከተማችን መናፈሻ ቦታ አለ፡ ነገር ግን፡ ለ ECA የሚሠሩትን ቦርጫም አፍሪቃውያን ፖለቲከኞችን (ዓብያተክርስቲያናቶቻችን አይጎበኙም) ለማስደሰት ሲባል የመናፈሻው በር ሁሌ ዝግ እንዲሆን ተደርጓል(ለባለሥልጣን ሠርግ ብቻ ነው የሚከፈተው)።
የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን መንፈስ አዳሽ ግቢ ግን ለሁሉም ሁልጊዜ ክፍት ነው።
የቤተክርስቲያኑን ግቢ እንዲህ ለሚንከባከቡት እናቶች፣ አባቶች፣ እህቶችና ወንድሞች የከበረ ምስጋና ይድረሳቸው።
Leave a Reply