የግብጽ እባብ | በረሃ ላይ አዲስ ቤተክርስቲያን ሠሩ፡ ክርስቲያኖች በብዛት በሚኖሩበት ሠፈር አራት አብያተክርስቲያናትን ዘጉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 17, 2019
በልደት ዋዜማ ቤተክርስቲያን ይከፍታሉ፤ በጥምቀት ዋዜማ ቤተክርስቲያን ይዘጋሉ!
ባለፈው የገና ዕለት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በፖሊሶች እየተደገፉ የኮፕት አብያተ–ክርስትያናት ፊት ሆነው ክርስቲያኖችን ሲሳደቡና እነርሱን እንደሚያጠፏቸውም በጩኸት ሲዝቱባቸው ነበር።
አሁን ክርስቲያኖች በብዛት በሚኖሩባቸው የተለያዩ የግብጽ መንደራት የሚገኙትን አራት አብያተ–ክርስቲያናት እንዲዘጉ የግብጽ መንግስት ትዕዛዝ አስተላለፈ። ይህ ውሳኔ ያደፋፈራቸው ሙስሊሞቹና ፖሊሶቻቸውም ቀሳውስቱንና መነኮሳቱን ጠፍረው በማሠር በከብት ማመላለሻ መኪናዎች ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል።
አዎ! የእባብን ሥራ እያየን ነው? የግብጹ ፕሬዚደንት ከሁለት ሳምንታት በፊት አዲስ ካቴድራል በርሃ ላይ መርቀው ከፈተው ነበር። ባለፈው ጊዜ ልብ ያላልነው ነገር፦ እዚህ በረሃ ላይ፡ አንደኛ፤ ክርስቲያኖች አይኖሩም፣ ሁለተኛ፤ እዚህ አንጋፋ ካቴድራል አጠገብ በይበልጥ አንጋፋ የሆነ አዲስ መስጊድ በዚያው ዕለት በፕሬዚደንቱ ተመርቆ ነበር። አሁን ክርስቲያኖች በብዛት በሚኖሩባቸው ሠፈሮች የሚገኙትን አብያተ–ክርስቲያናት ዘግተዋል፤ ክርስቶስንና ተከታዮቹን ለማዋራድም ቀሳውስቱን ጠፍረው በማሠር በከብቶች ማመላለሻ የጭነት መኪናዎች ላይ ወርወረዋቸዋል።
እነዚህ እርኩስ የዲያብሎስ ልጆች፣ የእነዚህ እባቦች ምላሳቸው ካልተቆረጠ በቀር መናደፉቸውን አያቆሙም፤ ቅዱስ ገብርኤል ምላቻቸውን በሰይፉ ፈጥኖ ይቁረጥባቸው!
Leave a Reply