ግብጽ | ሙስሊሟ ተማሪ “ላግባሽ!” ብሎ የጠየቃትን እጮኛዋን በማቀፏ ከዩኒቨርሲቲ ተባረረች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 14, 2019
እ.አ.አ በ 2009 ዓ.ም ወስላታው ባራክ ሁሴን ኦባማ ለሙስሊሙ ዓለም ንግግር ያሰማበት ታዋቂው የግብፅ አል–አዝሃር ዩኒቨርሲቲ፡ ተማሪዋ ሴት ላግባሽ ብሎ አበባ የስጣትን እጮኛዋን በማቀፏ ከዩኒቨርሲቲው አባርሯታል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ቪዲዮ በመታየቱ ነው ዩኒቨርሲቲው እዚህ አወዛጋቢ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የደፈረው። “ቪዲዮው የትምህርት ቤቱን መልካም ስም ያጎድፋል፤ ሙስሊሞች መተቀቃፍ የለባቸውም” ብሎ በመግለጽ ተማሪዋን ለማባረር መገደዳቸውን የዩኒቨርሲቲው መስተዳደር አስታውቋል።
በ ቪዲዮ ላይ አንድ ወጣት እቅፍ አበባ በመያዝ የጋብቻ ጥያቄን እንደማቅረብ በሚመስል መልክ ወጣት ሴቷን በደስታ ሲያቅፋት ይታያል።
Leave a Reply