Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የሩሲያ ፓትርያርክ፡ “ዘመናዊ ስልኮች ለፀረ-ክርስቶሱ መምጣት መንገድ ይከፍታሉ” በማለት በጥብቅ ያስጠነቅቃሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 11, 2019

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል የግና በዓልን በማስመልከት ከሩሲያ ቴሌቪዥን ጋር በተደረገ አንድ ቃለ ምልልስ ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፦

የክርስቶስ ተቃዋሚ፡ አሁን የተስፋፉትን ዘመናዊ ስልኮችን ወይም ስማርት ስልኮችን ለመጥለፍ የሚያስችለው ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ አጠቃቀም ስልት በጣም ሰፊ ነው

ቤተክርስቲያኗ የቴክኖሎጂ ዕድገትን አትቃወምም፥ ነገር ግን በኢንተርኔት የተገናኙ መሳሪያዎች ለሰው ዘር ሁሉ ዓለም አቀፍ ቁጥጥርማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥረዋል

ሰዎች በትክክል የት እንዳሉ ምን እንደሚፈልጉ፣ ምን እንደሚፈሩ ተከታያቾቻቸው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል

እንዲህ ያለው መቆጣጠሪያ መንገድ፡ ፀረክርስቶሱ ከአንድ ቦታ ሆኖ አስቀድሞ እንዲመለከት ይረዳዋል።

ፀረክርስቶሱ የሰው ዘር ሁሉ የሚቆጣጠር ዓለም አቀፋዊ መሪ ይሆናል ይህም ማለት ይህን መሰሉ የቴክኖሎጂ መዋቅ እራሱ አደጋን ያመጣል ማለት ነው

የአለም ፍጻሜን ቶሎ ለማድረስ ካልፈለግን በቀር ነገሮች በአንድ ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ቁጥጥር ሥር መውደቅ የለባቸውም፤ ማዕከላዊ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ነገር መጥፋት አለበት።” ብለዋል።

ፓትርያርክ ኪሪል ብልህ የሆነ እና በጣም ጠቃሚ የሆነ መልዕክት ነው ያስተላለፉልን። በተለይ ሕፃናት ከስማርት ስልኮች መራቅ ይኖርባቸዋል። አሁን እንኳን ምዕራባውያኑ ሕፃናት በስማርት ስልክ ሳቢያ ዓይኖቻቸው ክፉኛ እየተጎዱ ነውእዚህ እና እዚህ ያንብቡ።

ከጥቂት ዓመታት በፊት እነ ቢል ጌትስ ከወስላታው ኮፊ አናን ጋር በማበር ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕፃን አንድ ላፕቶፕ እንሰጣልን( One Laptop Per Child) ሲሉ፡ “ኡ! ! አውሬው ሕፃናቶቻችንን ሊቆጣጠር ይሻል!” በማለት ስጋቴን ገልጬ ነበር።

ስለ ፀረክርስቶሱ፡ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስጠንቀቂያዎች ፩ኛ የዮሐንስን ጨምሮ በሌሎችም መጻሕፍት ውስጥ እናገኛለን፦

፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፪ ፲፰ እንዲህ ይላል

ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።

ውድ ልጆች ሆይ, ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው; የክርስቶስ ተቃዋሚ እንደሚመጣ እንደ ሰማችሁ መጠን አሁንም ብዙዎቹ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል

ኢትዮጵያ አገራችንንም በጥቂቱ ላለፉት 50 ዓመታት እየመሩ ያሉት ፀረክርስቶሶቹ ናቸው። ለመሆኑ ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት መቆጣጠሪያ ባለሥልጣንን የገነቡ ግለሰብ መሆናቸውን እናውቅ ነበርን? ታዋቂው የስዊዘርላንድ ጋዜጣ NZZ ይህን በማስመልከት ከሁለት ወራት በፊት በሰፊው አትቶ ነበር።

በሌላ በኩል የ ጉግል ተቋምና የአሜሪካ ኤምባሲ፡ በልማት እና ስራ ፈጠራ ስም፡ ወንጀላዊ የኢንተርኔት ጠለፋና ፕሮፓጋንዳን የተመለከተ ሥልጠና በአሜሪካ ኢምባሲ በኩል ለኢትዮጵያውያን እንደሚሰጡ ባለፈው ኅዳር ላይ ተገልጾ ነበር።

በአገራችን ላይ እየተካሄደ ያለው ፀረክርስቶሳዊ ድራማ በቅደም ተከተል ነው በደንብ የተቀነባበረው። ነገሮች ሁሉ ወዴት እያመሩ እንደሆነ እያየን ነው።

______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: