Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2018
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የእኅተ ማርያም ማኅበር | እምቦጩ የኢትዮጵያን ቅዱሳት ቦታዎች ለማጥፋት የተፈጠረ አረም ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 31, 2018

ያውም ገዳማቱ መግቢያ መግቢያ ቦታ ላይ ነው እንዲበቅል የተደረገው

ወንድማችን ትክክል ነው፤ ከእምቦጩ አረም መብቀል ጋር በተያያዝ ሤራው የተጠነሰሰው በየኢትዮጵያ ጠላቶች ነው። ይህ አያጠራጥረን! እንዲያውም ይህ በአይናችን ለማየት የበቃነው አንዱ ክስተት ብቻ ነው። መታየትና መታወቅ ያለባቸው ገና ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ። ጎብኚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአረሙ ተካዮች፡ በዚያ በኩል የሚይልፉ አውሮፕላኖች በእነ ዋልድባ፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጊሸን፣ ዝቋላ፣ ቍልቢ በኩል እያለፉ መርዛቸውን በውሃና ደኑ ላይ ይረጫሉ። በአባቶቻችን ጊዜ ተደጋግሞ ይከሰት የነበረው የወሎና ትግራይ ድርቅ መንስዔ በዚህ መልክ ነበር የተካሄደው።

ወንድማችን እንዳወሳው፡ ከመቶ አመት በፊት አንስቶ ወደ ውጭ አገር እየተላክንና ስለ ጠላቶቻችንን ተንኮል ለመማርና ለማወቅ እድሉ ያለን “ኢትዮጵያውያን” ይህን ሤራ ለማጋለጥ ፈቃደኞች አለመሆናችን ሁልጊዜ የሚከነክነኝና የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያውያን የዘር ውርስ ወይም ጀነቲክስ ላይ ምርምር የሚያካሂድ አንድ የስታንፎርድ ወይም ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ “ኢትዮጵያዊ” ለምሳሌ ሴቶቻችንን መኸን ለማድረግ ሕጻናቶቻችን ለማኮላሸት የተጠነሰሰ ሤራ እንዳለ በደንብ ነው የሚያውቀው። ታዲያ እንዴት ነው፡ በድብቅ እንኳን ለሕዝባችን ሹክ ከማለት የተቆጠቡት? በጣም ያሳዝናል፡ ለንስሃ እንኳን ሳንበቃ የዶክተርና የማስተርስ ማዕረጉን ይዘን ወደ አፈር ውስጥ መግባታችን እኮ ነው።

ድንቅ ሥራ እየሠራችሁ ነው እኅቶቻችን እና ወንድሞቻችን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን!!!

 ______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: