ቅዱስ ገብርኤል ሆይ፥ ሕዝባችንን በመተናኮል ላይ ያለውን ዘንዶ እና የአገራችንን ጠላቶች ሁሉ በሰይፍህ ቀጥቅጠህ ጣላቸው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 30, 2018
[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፰]
፲፭ እኔም ዳንኤል ራእዩን ባየሁ ጊዜ ማስተዋሉን ፈለግሁ፤ እነሆም፥ የሰው ምስያ በፊቴ ቆሞ ነበር።
፲፮ በኡባልም ወንዝ መካከል። ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ።
፲፯ እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል አለኝ።
፲፰ ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ።
፲፱ እንዲህም አለኝ። እነሆ፥ በመቅሠፍቱ በመጨረሻ ዘመን የሚሆነውን አስታውቅሃለሁ፤ ይህ ለተወሰነው ለፍጻሜ ዘመን ነውና።
____________
Leave a Reply