በሙስሊሞች ቁጥር ብዛት በዓለም የመጀሪያውን ቦታ የያዘቸው ኢንዶኔዥያ በክርስቶስ ተከታዮች ላይ ከፍተኛ በደል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ባለፈው ዓመት በዋና ከተማዋ ጃካርታ አንድ ክርስቲያን ጠቅላይ ገዢ ወይም ከንቲባ ሊሆን አይችልም በማለት ሙስሊሞቹ አምጸው ክርስቲያኑን ፖለቲከኛ እንደወነጀሉትና ከስልጣኑ እንዳስወረዱት የሚታወስ ነው። በዛሬዋ ኢንዶኔዥያ፤ ዓብያተክርስቲያናት ማሠራት ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ እና ግብጽ ከባድ እየሆነ መጥቷል። ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው ያሉትም ዓብያተክርስቲያናት በመሀመድ አርበኞች በመፈራረስ ላይ ናቸው። ለከርስቲያኖች ያላቸውን ጥላቻ እንመልከት!
ከሦስት ቀናት በፊት ክርስቲያኑ ቄስ የተቀበሩበት መቃብር ላይ የተተከለውን የእንጨት መስቀል ሙስሊሞች “ይህች የእስላም አገር ናት” በማለት ሰባብረውታል። ለሙታን እንኳን ተገቢውን ክብር አለመስጠታቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ምን ያህል ጥላቻ እንዳላቸው ነው የሚያሳየው።
እግዚአብሔር አምላክ ግን “በቃ!” የሚልበት ዘመን ላይ ደርሰናል፤ የሚፈጸሙብንን ግፎች ዝም ብሎ አያልፍም።
በገና በዓል አካባቢ ኢንዶኔዥያ በተፈጥሮ አደጋ ብዙ ጊዜ ትናወጣለች፤ ዛሬም እሳተ ገሞራው ፈነዳ፤ ባሕሩም ኃይለኛ ሞገድ ሠራ በመስቀሉ ጠላቶች ላይ ከፍተኛ ቁጣ መጣ!
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯፥፶፡፶፩]
“ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥
ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤“