ከካይሮ በስተደቡብ፡ በሚኒያ አውራጃ ለተገደሉት ክርስቲያን አባትና ልጅ የተዘጋጀው ሌላ እንባ አስወራጅ የቀብር ስነሥርዓት
በግብጽ መንግስት አበረታችነት በየሳምንቱ ተመሳሳይ በደል እና ግድያ በኮፕት ወገኖቻችን ላይ ይካሄዳል፤ የመሀመዳውያኑ ወዳጅ የሆነው ሉሲፈራውያኑ ዓለም ፊቱን አዙሯል፣ ሜዲያዎች የፌንጣ ድምጽ እንኳን አያሰሙም፣ ክርስቲያን ነን የሚሉት የቡና፣ ጥምባሆና፣ ጫት ሱስ ባሪያዎች ከእምነት ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ጋር አብረው እንደመቆም ለደመ–ነፍስ አጥፊዎቹ መሀመዳውያን ጠበቃ ሆነው ሲሟገቱላቸው ይሰማሉ። እስኪ መቼ ነው የኢትዮጵያ ሜዲያ “ግብጻውያን ክርስቲያኖች በሙስሊሞች ተገደሉ!„ “ቱርክ በሶርያ እና አረመን ክርስቲያኖች ላይ ጭፍጨፋ አካሄደች” የሚሉ ርዕሶችን የያዘ ዜና አቅርቦ የሚያውቀው? ለሶርያ እና ለምያንማር ሙስሊሞች ግን ተቆርቆሪዎች ሆነው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሰፊው ሲለፍፉ ይሰማሉ። ግብዞች!
ለእነዚህ አረመኔ የዲያብሎስ ልጆች መልሱን መስጠት የምትችለው ኢትዮጵያ ብቻ ነበረች። የቀደሙት አባቶቻችን፦ “ዋ! ክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ትነኩ እና ወዮላችሁ አባይን እንገድበዋለን፣ በአጻፋውም ኢትዮጵያ ያሉትን ሙስሊሞች እንበድላቸዋልን” በማለት መሀመዳውያኑን ሲያስፈራሯቸው ክርስቲያኖች ሰላም ያገኙ ነበር፣ አብያተክርስቲያናት ወዲያው እንዲሰሩ ይፈቀድላቸው ነበር።
የአሁኖቹ መሪዎቻችን ግን አላስፈላጊ ለግብጻውያኑ በማጎብደድ “አትፍሩ፣ ግድቡ መቼም አያልቅም፣ ሙስሊሞቹን አይሻንና ካዲጃንም ስልጣን ላይ እናስቀምጣቸዋለን፣ የሠራዊታችን መሪዎች እናደርጋቸዋለን፡ አይዞን!” ይሏቸዋል። በዚህም የተበረታቱት ግብጻውያን ሙስሊሞች ኮፕት ክርስቲያን ወገኖቻችንን ይጨፈጭፋሉ፣ አብያተክርስትያናቶቻቸውን ያፈራርሱባቸዋል። በአገራችንም ሳይቀር ተመሳሳይ ድርጊት እንዲጀምሩ አደፋፍሯቸዋል።
በዚህ የገና በዓል ሰሞን ክርስቲያኖች በጥሞና ሊያተኩሩበት የሚገባ ጉዳይ፡ ቱርክ ጥንታውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሆኑት አርመኖች እና ሶርያውያን ላይ የመጨረሻውን የጭፍጨፋ ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀች መሆኑ ነው። ያው በዛሬው ዕለት አሜሪካ ወታደሮቿን ከሶርያ እንደምታወጣ አስታውቃለች። ይህ ማለት ክርስቲያኖች በተከማቹበት የሰሜኑ የሶሪያ ክፍል ለፀረ–ክርስቶሷ ቱርክ ሠራዊት በሩ ተከፈተ ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ዘመቻው ወደ እናት ኢትዮጵያ እንደሚያመራ አንጠራጠር። የፀረ–ክርስቶሱ ሠራዊት እንደ አገራችን ተራራማ የሆነ መልክዐምድር ባላት በአፍጋኒስታን ለ18 ዓመታት በመለማመድ ላይ ይገኛሉ።
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፵፬፥፩፡፯]
“አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
እጅህ አሕዛብን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን ሣቀይኻቸው አሳደድኻቸውም።
በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም ክንዳቸውም አላዳናቸው፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ ወድደሃቸዋልና።
አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያዕቆብ መድኃኒትንህ እዘዝ።
በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።
በቀስቴ የምታመን አይደለሁምና፥ ሰይፌም አያድነኝምና፤
አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን፥ የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው።”
______
Like this:
Like Loading...