ምናልባት ከግራኝ አህመድ ለግብጽ የተሰጠ ስጦታ ይሆን?
በአረቡ ዓለም ከፍተኛውን ክፍያ የሚያገኘው ታዋቂው የግብፅ ቴሌቪዥን አስተናጋጅ አሚር አዲብ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሂደት በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት መዘግየቱና ለአራት ዓመት ያህል እንዲቆይ የኢትዮጵያ መንግስት ማሳወቁ “ለግብጻውያን ትልቅ የአላህ ስጦታ ነው” ብሎታል።
አሚር አዲብ በምሽት ፕሮግራሙ ላይ ባደረገው ንግግር እንዲህ ብሏል፦
“ለአላህ ምስጋና ይግባው የግድቡ ግንባታ መዘግየት ለግብጽ ጥሩ ነው፡ ምክንያቱም ግድቡ ለግብፅ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ነው።“
አሚር አዲብ በመቀጠል፦
«አላህ ለጋስ ነውና፣ ይህ ለግብጻውያን ያበረከተው ትልቅ ስጦታ ነው፣ አላህ ግብጽን ይወዳታል! ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንን አሁን የምመክረው፤ ጊዜ ውሰዱ፣ ታገሱ፣ አትጣደፉ! ቀስበቀስም እስካሁን የተገነባውን ግድብ ኡ–አፈራርሱትና እንደገና ከመጀመሪያው ጀምሩ፡ ከዚያ እኛ መሐንዲሶቻችንን እንልክላችኋለን።”
ወይኔ የእስማኤላውያን መሳለቂያና መጫወቻ ሆነን ቀረን!? እንዴት ነው ተመላልሰን ጭቃ ውስጥ የምንገባው፤ መቼ ነው ከታሪክ ተምረን በቃን የምንለው!?
አውሮፓውያን የአረቦችን ፖሊሶችና ወታደሮች ያሰለጥናሉ፤ የአረብ ኤሚራቶች ደግሞ የግራኝ አህመድን ፖሊሶች “ለማሰልጠን” ቀሚሶቻቸውን በማውለቅ ላይ ናቸው፣ አውሮፓውያን የአረቦችን ከተሞች ይገነባሉ፤ የአረብ ኤሚራቶች ደግሞ አዲስ ከተማ “ለመገንባት” ወደ አዲስ አበባ ይጋበዛሉ። ወገኖቻችን ለባርነት ወደ አረብ አገር ይላካሉ፣ በአረቦች ይገደላሉ፣ ክርስቲያን ወገኖቻችንና መሐንዲሶቻችንን የሚገድሉት አረቦች ደግሞ ወደ ኢትዮጵያና አውሮፓ ይሰደዳሉ።
ደማችሁ አይፈላም እንዴ፡ ወገኖቼ! አገራችን እራሷን መከላከል እንኳ የማትችልበት አደገኛ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። የአባቶቻችንን ወኔ ቶሎ ካላስመለስን ስልጣን ላይ የተቀመጡት የግራኝ አህመድ ሴት አርበኞች ዓይኖቻቸውን በድንኳናቸው ሸፍነው ወደ መካ ሹልክ ብለው ይሄዳሉ፤ ያኔ አንድ የግብጽ የፖሊስ ቡድን እንኳን አገራችንን ሊወር ይችላል።
ባለፈው ወር ላይ ያነጋገርኳቸው አንድ አባት አገራችን ውስጥ የሚታየውን ሁኔታ ከደርግ መንግስት ጋር እያነጻጸሩ ሲያጫውቱኝ እንዲህ ብለው ነበር፦
“ኃይለ ሥላሴ ሲወርዱ ሰው ሁሉ ተደስቶ ለወታደሮች፣ ለመኪናዎቻቸውና ለታንኮቻቸው የእቅፍ አበባ ስጦታ ያበረክት ነበር፣ ሙስሊሞች በመርካቶ በደስታ ይጨፍሩ ነበር፤ በዚህ የተበረታታውም የደርግ መንግስት “የፍየል ወጠጤ” እያለ ኢትዮጵያን ሊከላከሉ የሚችሉትን እና የጦር ልምድ ያላቸውን ጄነራሎችና የጦር አበጋዞች ማሰርና መግደል ጀመረ፤ ይህን ያየችው ሶማሊያም እስከ ጅጅጋ ድረስ በቀላሉ ሰተት ብላ ገባች፤ ከዚያ ኢትዮጵያውያን እርስበርስ ከመበላላት አልፈን በየመንገዱ ሲታደኑ የነበሩት ወጣቶቻችን የጅቦች እና የውሾች ምግብ ለመሆን በቁ፣ አንድ ቀን ከቤቴ ስወጣ መንገድ ላይ ወድቆ የነበረውን ወጣት ሬሳ ላይ ውሾች አንጎሉን ሲበሉት አይቻለሁ” በማለት እንባ ተናንቆቸው ያጫወቱኝን አልረሳውም።
እኔም፦ “ታዲያ አሁን የፍየል ወጠጤው አሁን የቀን ጅብ ሆነ ማለት ነው?!“ አልኳቸው። “እግዚአብሔር ይርዳን፡ አዎ! ታሪክ እየተደገመች መሰለኝ” አሉኝ።