እኅተ ማርያም ይህን ሤራ ባስታወቀች ማግስት ጀርመን “ሦስተኛ ጾታ” መታወቂያ ላይ እንዲሠፍር አዘዘች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 15, 2018
በትናንትናው ዕለት ጀርመን ከወንድና ሴት ሌላ “ሦስተኛ ጾታን” የሚመርጡ ወላጆች መታወቂያና ፓስፖርት ላይ እንዲያሠፍሩ በመፍቀድ የመጀመሪያዋ አውሮፓዊት አገር ሆነች።
እንግዲህ ይታየን፤ ይህን በመሰለው እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ጉዳይ ላይ ሕዝቡ ምንም አልተጠየቀም፣ ክፍት የሆነ ውይይት እንኳን አልተደረገበትም፤ የውሳኔውም ዜና የሜዲያዎችን አትኩሮት እንዳይኖረው ተደርጓል፤ የመጭውን ትውልድ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ጉዳይ፡ ትልቅ ጉዳይ!
የኢትዮጵያን የመታወቂያ ማውጫ፣ አሻራ እና ደም መስጪያ ሥራ ኃላፊነት የተረከብችው ጀርመን ናት በማለት እኅተ ማርያም ባለፈው ሰኞ ጠቁማን ነበር። …ነጠብጣቦቹን እናገናኝ
በአፍ ለመናገር የሚቀፍ ድርጊት እየተሠራ ነው። የፀረ–ክርስቶሱን አንድ ዓለም መንግሥት ለመመስረት የተነሱት የፍዬል አገራት ወደ አገራችን ጠጋ ጠጋ ማለታቸው በጣም ሊያሳስበን ይገባል። እነዚህ አገራት በእግዚአብሔር እና ተፈጥሯዊ ሕግጋት ላይ እንዲሁም በልጆቹ ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ለረጅም ጊዜ ”የፍራንክፈርት ትምህርት ቤት” በመባል የሚታወቀውን የፀረ–ክርስቶሱን ዓላማ አራማጅ ቡድን ተልዕኮ እነ አንጌላ ኤሊዛቤል ሜርክል አሁን በሥራ ላይ በማዋል ላይ ናቸው። የዚህ የፍራንክፈርት ትምህርት ቤት ቅጥረኛ የነበረው ሩሲያዊው ቭላዲሚር ሌኒን እንዲህ ብሎ ነበር፦
“አንድን ማሕበረሰብ ማውደም ከፈለግክ፤ ቤተሰብን በቅድሚያ አጥቃ!”
አዎ! እነ ሜርከል፣ ሜይ እና ማክሮን አሁን እነ ሌኒን እንኳን በሥራ ላይ ለማዋል ያልደፈሩትን በቤተሰብ ላይ ያነጣጠረ ዲያብሎሳዊ ሤራ በተግባር ላይ በማዋል ላይ ናቸው።
ባለፈው ወር ላይ ወደ ፍራንክፈርት ከተማ ተጉዘው የነበሩት ዶ/ር አብይ አህመድም ከዚህ የተለየ ተልዕኮ ሊኖራቸው አይችልም።
Leave a Reply