Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2018
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 9th, 2018

ድንቁ አቡነ የማታ ጎህ ገዳም | ባዕዳውያኑ ኢ-አማንያን፣ ካቶሊክ፣ ሙስሊም እና ፕሮቴስታንት በመልካምና በበጎ ልብ ሲመሰክሩልን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 9, 2018

የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን በሰማይ ላይ በሚል ርዕስ በ፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፃድቁ አባታችን አቡነ የማታ ስላሠሩት የጸሎት ቤትክርስቲያን አጠር ያለ ቪድዮ አቅርቦልናል። ይህን ድንቅ ቪዲዮ እዚህ ድህረ ገጽ ገብቶ ማየት ይቻላል ፡ Great Big Story

ዓለማችን ተወዳዳሪ በሌለው የክፍፍል እና ጥላቻ አዝቀጥ ውስጥ በተዘፈቀችበት በዚህ ዘመን የሚከተሉትን ድንቅ ዘገባዎች “ባዕዳኖች” ሲሰጡ ብሎም እነዚህ የውጩ ዓለም ኢአማንያን፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ እና ሙስሊም ግለሰቦች ይህን ያህል ፖዘቲቭ ሆነው ሲመሰክሩልን መስማቱ እጅግ በጣም የሚያስደስት ነው። በእውነት ይህ በመካከላችን ለበቀሉት ጡት ነካሽ መዥገሮች እና ጥገኛ አረሞች ትልቅ ትምህርት ይሆናል።

አንዳንድ የተመልካቾች አስተያየት፦

  • How humble would you have to be to go here an say “I just went to Church on Sunday”

ወደ እዚህ ድንቅ ቦታ መሄድና እሁድ እሁድ ወደ ቤተክርስቲያን እሄድ ነበርብሎ መናገ ምን ያህል

ትሁት እንደሆናችሁ ያሳይ ነበር

  • Look how they dress. Such modesty and beauty. Souls above flesh. The true followers of The God of Abraham

እንዴት እንደሚለብሱ ይመልከቱ እንዲህ ያለው ልከኝነትና ውበት። ከሥጋ ውጭ የሆኑ ነፍሳት የአብርሃም አምላክ እውነተኛ ተከታዮች!

  • REAL FAITH: The last real Christians. She rocked it with a baby on her back. amazing!

እውነተኛ እምነት፤ እነዚህ ናቸው የመጨረሻዎቹ እውነተኛ ክርስቲያኖችእናትየዋ ህፃኗን በጀርባዋ እያወዛወዘች ዳገቱን ትወጣለች፤ በጣም አስደናቂ ነው!

  • I don’t believe in God but this is truly amazing.

በአምላክ አላምንም ነገር ግን ይህ በእውነት በጣም አስገራሚ ነው

  • Orthodox Christianity in its original form before Rome plagiarized and whitewashed everything.

ካቶሊኳ ሮም ነገሮችን ከማበላሸቷ በፊት የቀድመው የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት እንደዚህ ይመስላል

  • I’m not religious, but that’s beautiful

እኔ ሃይማኖተኛ አይደለሁም ግን ይህ ውብ ነው

  • Christian Africa can be absolutely beautiful! islamic Africa.. not so much…

ክርስትያ አፍሪካ በጣም ውብ ሲሆን፥ ስላሙ አፍሪካ ግን አይደለም

  • GODBLESS these beautiful people

  • Love Ethiopia

እነዚህ ቆንጆ ሕዝቦች ይባረኩ፤ ኢትዮጵያን አፍቅሩ!

  • Going to the church itself is a challenge, imagine building it.

ወደ ቤተክርስቲያ መሄ በራሱ ተፈታታኝ ነገር ነው፤ ይህን መገንባቱ ደግሞእስኪ አስቡበት

  • Going to a church located in the mountain at such altitude is truly a test of faith and courage!!!

በተራራ ላይ ወዳለው ቤተ ክርስትያን መጓዝ በእውነት የእምነትና እና ድፍረት ፈተና ነው !!!

  • No country parallels amazing,ancient and proud Ethiopia’s history!!!! Ethiopia is where everything starts be it religion, fauna and flora, mankind, sciences,astrology, etc. United and ancient Ethiopia forever!!!!

አስገራሚ፣ ጥንታዊ እና ኩሩ የሆነውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚወዳደር አገር የለም፤ ሀይማኖት እንስሳት እና እጽዋት የሰው ልጅሳይንስ ኮከብ ቆጠራ ወዘተ ሁሉም ነገር የሚጀመረው በኢትዮጵያ ነው

  • Ethiopia fought off islam and won. No wonder they are so beautiful and prosperous.

ኢትዮጵያ እስልምናን ተዋግታ አሸነፈች፤ ስለዚህ በጣም የሚያም እና የበለጸጉ ሆነዋል

  • These people ancestors built ancient Egypt and got pushed back by the expansion of Islam

የኢትዮጵያውያን የቀድሞ አባቶች የጥንቷን ግብፅ ገንብተዋል፤ በኋላ ግን በእስልምና መስፋፋት ተገፍተዋል

  • Glad that the Islamists didn’t convert this to a Mosque

ሙስሊሞች ይህንን ቦታ ወደ መስጊድ ባለመቀየራቸው ደስተኛ ነኝ

  • Im muslim and somali i think this is Amazing level of dedication.

እኔ ሶማሌ ሙስሊም ነኝ ሆኖም ይህን አስገራሚ የእምንት ጽናት አደንቀዋለሁ

  • Natural skyscraper.

ተፈጥሯዊ ሰማይ ጠቀስ

  • Ethiopians were practicing Christianity 900 years before Europe! It’s fair to say they have one of the most authentic versions on the planet

ኢትዮጵያውያን ከአውሮፓ 900 ዓመታት ቀድመው ክርስቲያኖች ነበሩ! በፕላኔታችን ላይ በጣም ትክክለኛውን

ክርስትና ይዘዋል ብንል ፍትሃዊ የሆነ አባባል ነው።

  • Ethiopian churches are declarations of FAITH

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት የእምነት መግለጫዎች ናቸው

  • Before I’d die, I’d love to visit this divine church carved on such heights. On behalf of the Catholic Church, may they always keep the faith strong.

ከመሞቴ በፊት፡ በእንዲህ መሰል ከፍታ ላይ የተቀረጸውን ይህ መለኮታዊ ቤተክርስቲያን መጎብኘት እወዳለሁ። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስም ይህን እምነታችሁን ሁልጊዜ ጠብቁ እላለሁ።

  • I wanna go there even though i don’t believe in God

በአማላክ አላምንም ግን ወደዚህ ቦታ መሄድ እሻለሁ

  • True Christians

እውነተኛ ክርስቲያኖች

  • Such powerful and spirit filled Christians. We can learn from these people’s devotion to God.

እንዲህ ጠንካራ የሆኑ እና መንፈስ የተሞላባቸው ክርስቲያኖች ናቸው እነዚህ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች መማር እንችላለን

  • Unconditional love for GOD Almighty

ፍፁም የሆነ ፍቅር ለኃያሉ አምላክ

  • I’m far from religious, and even I am touched by this. The devotion and craftsmanship is wonderful. So raw, thank you for sharing.

እኔ ሃይማኖተኛ አይደለሁም፤ ግን ይህ እኔን እንኳን ልቤን ነክቶታል። ጥልቅ የእምነት ፅናቱ እና ተዓምረኛ

ድንቅ ነው። ይህን ስላጋራችሁ እናመሰግናለን

  • I like how humble and down to earth (no pun intended) that priest sounds

ዝቅ ብለው በትህትና መናገራቸውን ወድጀዋለሁ (መቀለዴ አይደለም)

  • Faith written in the stone through the hands and feet of the lords children.

በእግዚአብሔር ልጆች እጆች እና እግሮች በድንጋይ ላይ የተፃፈ እምነት

  • I don’t think even Moses went that high to receive the 10 commandments.

ሙሴ እንኳ አሠርእዛዛትን ለመቀበል፡ ይህን ያህል ወደ ላይ ከፍ ብሎ ወጥቷል ብዬ አላስብም

  • Ethiopia is a land of wonders, God fearing people. Ethiopia stretches her hands unto God.

ኢትዮጵያ የብዙ ተዓምራት ምድር ናት፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ሕዝብ፤ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች!

ምንጭ: Great Big Story

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: