Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2018
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 5th, 2018

የግራኝ አህመድ ጊዜ እንዳያገረሽ – ቤተ ክርስቲያናችን ዘመቻ ፊልጶስን ልታውጅ ይገባታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 5, 2018

ሞኙ ሕዝባችንን፡ ላይ ላዩን በድራማዎች እና በ “አዲስ ዜና” ፕሮፓጋንዳዎች እያታለሉ ውስጥ ውስጡን ግን የመቶ ዓመት ህልሞቻቸውን በሥራ ላይ በማዋል ላይ ናቸው።

በጅጅጋ፣ በአምቦ፣ በጅማና በመሳሰሉት የደቡብ ከተሞች ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ተመንጥረው ቀስበቀስ በመገደል ላይ ናቸው፤ ክርስቲያን ሕፃናቱ ደክመው ሕይወታቸው እንድታጠር መርዝ እየተሰጣቸው ነው። አዲስ አበባም ከደቡብ በመጡ አማርኛ ተናጋሪ ባልሆኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች ተወርራለች (ይህ የማፈናቀያ ዘመቻ በደንብ መጧጧፍ የጀመረው፡ በተለይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ነው፤ የደቡብ ሰዎችና ሙስሊሞች በብዛት ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡና የንግድ ቦታዎችን እንዲከፍቱ፣ በየጎረቤቱ ተሰግሰው እንዲገቡ፣ ወላይታዎች ደግሞ ጉራጌዎችን በመተካት እንደ ጫማ ጠረጋ በመሳሰሉት የስራ መስኮች ላይ እንዲሰማሩ፤ በሌላ በኩል ክርስቲያኖች (“አማራና ትግሬ) የእኔቢጤዎች ሆነው በየቦታው እንዲለምኑ፤ በተለይ በቤተክርስቲያን አካባቢ። ይህ ማንም የሚያየው የአዲስ አበባ ገጽታ ነው።

አሁን ደግሞ በመካሄድ ላይ ያለውን ለው ተከትሎ ወይም ተገን አድርጎ የሚነሣ ፀረ ክርስትና ቡድን በሚወስደው ኢክርስቲያናዊ ርምጃ ምክንያት የአምልኮተ እግዚአብሔር መፈጸሚያ የኾኑት የተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ሲደፈሩና ሲወድሙ፤ በአገልጋዮቿ ካህናትና በተከታዮቿ ምእመናንም ላይ እስከ ኅልፈተ ሕይወት ጉዳት ሲደርስ፣ ሌላ አቅም ባይኖራትም የተከታይ አቅም እያላት፣ “ዝም በሉ የእኔን እግር ነው የሚበላው” እንደተባለው ዐይነት ነገር የደረሰባትን ጉዳትና ችግር ኹሉ በትዕግሥት፣ በአርምሞና በጽሞና ማሳለፍ ከጀመረች እነኾ ወደ ግማሽ ምእት ዓመት አጋማሽ ተጠግቷታል፡፡

ይህን በማስመልከት ሐራ ዘተዋሕዶ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቦልናል፦

የሩቁን ለታሪክ እንለፈውና በቅርቡ የተደረገውን ስናስታውሰው፣ በ1997 .. በአርሲ ሀገረ ስብከት በኮፈሌ ወረዳ ውስጥ የምትገኘው የአይሻ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ በወቅቱ በተፈጠረው የምርጫ ግርግር ምክንያት፣ ፀረ ክርስትና አቋም ባለው ቡድን ስትቃጠልና አገልጋዮቿ ካህናት በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲታረዱ ዝም ብላ አሳልፋለች፡፡ እንደገናም በ1999 .. በጅማ ሀገረ ስብከት የበሸሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 5 ቀን በዕለተ በዓሉ በፀረ ክርስትና ኃይሎች ሲቃጠልና አገልጋዮቿ ካህናትና ተከታዮቿ ምእመናንም በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንደ በግ ሲታረዱ አሁንም ለኅብረተሰቡ የከፋ እልቂት እንዳይደርስ በማሰብ በብዙኃን ተከታዮቿ ዘንድ እየታማች ጉዳቷን ጉዳት አድርጋ ድምፅዋን ሳታሰማ በትዕግሥት አሳልፋለች፡፡

አሁን ደግሞ በቅርቡ፣ ባሳለፍነው በ2010 .. መገባዳጃ ላይ፣ አገር የኾነችውን ወይም ኹለንተናዊ ጠቃሜታዋና ትሩፋቷ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ የኾነችውን አንጋፋዋን ቤተ ክርስቲያን ከሌላው ነጥሎ ለመምታትና የተከታዮቿ ምእመናንን አሻራ ከገጸ ምድር ለማጥፋት ወይም አሳምኖ የራሱ ተከታዮች ለማድረግ፣ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ባለው የሱማሌ ክልል ፀረ ክርስትና ቡድን በፈጸመው ጥቃት፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያንን በሙሉ አውድሟቸዋል፤ ሀብታቸውን፣ ንብረታቸውንና ቅርሶቻቸውንም ዘርፏቸዋል፤ አገልጋዮቿ ካህናትንም እንደ ካህኑ ዘካርያስ በየቤተ መቅደሳቸው ውስጥ አርዷቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ በማነጣጠር በተከታታይ የተፈጸመው ይህ ዐይነቱ ጥቃት ወይም ኢክርስቲያናዊ ድርጊት ከትዕግሥት በላይ ቢኾንም፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ አገር እንደ መኾኗ መጠን፣ አሁንም በቤተ ክርስቲያንም ኾነ በሕዝብ ላይ የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ በማሰብ ብዙ መጎዳቷንና መጠቃቷን ለመንግሥትና ለሕዝብ ይፋ ያደረገችው ከብዙ ጉዳትና ትዕግሥት በኋላ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ከዓመታት በፊት በሊቢያ በረሓ ላይ በአይኤስኤስ ፀረ ክርስትና ቡድን ለተሠዉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሰማዕትነት ክብርና ማዕርግ እንደሰጠቻቸው ኹሉ ይልቁንም፣ በራሳቸው አገር በቤተ መቅደስ አገልግሎት ላይ እንዳሉ ለተሠዉት ለራሷ ካህናትና ምእመናን የሰማዕትነት ክብርና ማዕርግ መስጠት ነበረባት፤ ከአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚጠበቀውም ይህ ውሳኔ ነበር፤ ወደፊትም ቢኾን የሰማዕትነት ክብርና ማዕርግ እንዲያገኙ ውሳኔ መስጠት ይገባታል፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ፣ ለኹሉም በተሰጠው ገደብ የለሽ የእምነት ነጻነት መሠረት፣ ኹሉም የራሱን እምነት በሰላም ማራመድ ሲገባው በተቃራኒው ፀረ ኦርቶዶክስ ዘመቻ በኹለት ግንባር በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡ በአንድ በኩል ቀደም ሲል በዝርዝር እንደተገለጸው፣ ፀረ ክርስትና አቋም ያለው ቡድን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙትን የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን እያቃጠለ ነው፤ ካህናትንና ምእመናንንም እያረደ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ እንደእነ ፓስተር ኢዩ ጬፋን የመሳሰሉት የእነ ሬንሐርድ ቦንኬ ደቀ መዛሙርት፣ በቡድን ተሰማርተው ሕዝቡን በወንጌል ሳይኾን በመናፍስት መንፈስ በማስገደድና በካራቴ በግድ በማሳመን የእነርሱ ተከታይ ለማድረግ እየተጣጣሩ ነው፡፡

ስለዚህ የብሉይ ኪዳን እምነትና የሐዲስ ኪዳን እምነት መሠረት የኾነችው ሀገረ አምላክ ኢትዮጵያ፣ የእነ ሬንሐርድ ቦንኬ ሠራዊት መፈንጫ አገር ከመኾኗም ባሻገር ኹለተኛዋ ሊብያ እንዳትኾንና የግራኝ አሕመድ ጊዜ እንደገና እንዳያገረሽ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ዘመቻ ፊልጶስን ልታውጅ ይገባታል፡፡ በስሟ ተጠቃሚዎች የኾኑት አንጋፋ ማኅበራትም፣ ከቤተ ክርስቲያኒቷ ጋራ በአቻነት ለመሰለፍ የሚያደርጉትን ግብግብ ለጊዜው አቁመው በሚቻላቸው ኹሉ ሊያግዟት ይገባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ትዕግሥትዋ ያለቀ በመኾኑ፣ ከጥቅምት 11 እስከ 22 ቀን 2011 .. ድረስ ባደረገችው ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ባሳለፈችው ውሳኔ፣ ከጦርነት ኹሉ የሃይማኖት ጦርነት ስለሚከፋ፣ የከፋ ችግር ከመፈጠሩ በፊት በሀገሪቱ ምሥራቃዊ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች እየተፈጸመ ያለው ኢክርስቲያናዊ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲገታ መንግሥት የራሱን አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድ ያቀረበችው አቤቱታና ከኅዳር 1 እስከ 7 ቀን 2011 .. 7 ቀናት ያህል በመላ ኢትዮጵያ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ የዐወጀችው ዐዋጅ የሚደገፍ ነው፡፡

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: