“የሙሴ ጽላት በኢትዮጵያ መሆኑን የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ አለ” | ይላል አሜሪካዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪ ቡድን
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 4, 2018
በታዋቂው አሜሪካዊ ተመራማሪ፡ በ ቦብ ኮርኑክ የሚመራው የመጽሐፍ ቅዱስ አርኪኦሎጂ፡ የፍለጋ እና አሰሳ ተቋም (BASE) እንደገለጸውና እንደ ተቋሙ አጥኒዎች ምርምር ከሆነ፡ የሙሴ ጽላት ምናሴ በሚገዛበት ዘመን ከኢየሩሳሌሙ የቤተመቅደስ ተራራ ከተወሰደ በኋላ በግብጽ የአይሁዶች ግዛት ወደ ነበረችው የኤሊፋንቲን ደሴት እንዲያርፍ ተደረገ።
ከዚያ በኋላ፡ የአባይን ወንዝ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን መነኩሴዎች ብቻ ወደ ሚገኙባት የጣና ሀይቅ ቅድስት ደሴት፡ ወደ ጣና ቂርቆስ ተወሰደ።
ከዚያም በኢትዮጵያ በስተሰሜን ወደምትገኛዋ ወደ አኩሱም ከተማ ተዛውሯል።
የሙሴ ጽላት በተጨማሪም ሀያል እና ተዓምረኛ እንደሆነ የሚታመነውን እንደ የአሮን በትር የመሳሰሉትን ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕቃዎች እንደሚይዝ ይነገራል።
—[link to www.foxnews.com]
—[link to sputniknews.com (secure)]
ይህ ዜና በአክሱም ጽዮን ሰሞን መውጣቱ በጣም የሚገርም ነው!!!
ጽዮን ማርያም – ዑራኤል – ጊዮርጊስ – ተክለሃይማኖት – መርቆርዮስ
[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፩፥ ፲፱]
“በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።”
Leave a Reply