አሁን በአረጀንቲና በሚካሄደው የዓለማችን ፈላጭ ቆላጮች ስብሰባ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ መሳተፍ አትችልም።
የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ…የእግዚአብሔር ጎል ሳጥናኤል…
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2018
አሁን በአረጀንቲና በሚካሄደው የዓለማችን ፈላጭ ቆላጮች ስብሰባ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ መሳተፍ አትችልም።
የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ…የእግዚአብሔር ጎል ሳጥናኤል…
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: Antichrist, ሊበራሎች, አንጌላ ሜርከል, አውሮፓ, ኢትዮጵያ, የተጠሉ መሪዎች, ጀርመን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሴራ, ፈረንሳይ, G20, Germany, Lizards, Merkel, Zombies | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2018
መላው ዓለምን ያንቀጠቀጠ እና የሳይንስ ሊቃውንቱ ማብራሪያ ለመስጠት የተቸገሩበት አንድ አስገራሚ ክስተት ከሁለት ሳምንታት በፊት፡ እ.አ.አ በኖቬምበር 11 / 2018 ዓ.ም ተፈጥሮ ነበር።
የዚህ ክስተት ሚስጥር መንስኤ እስካሁን ድረስ ባይታወቅም ከመሬት መንቀጥቀጥ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። “ናሺናል ጂኦግራፊክ” እንደገለጸው ከሆነ የባሕር ውስጥ መሬት መንቀጥቀጥ የፈጠርው ሞገድ ማዕከል በማዳጋስካር ሰሜናዊ ጫፍ እና ምስራቅ አፍሪቃ መካከል በምተገኘዋ የማዮቴ ደሴት የባህር ዳርቻ ነው።
የድምጽ መልእክቱ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በዛምብያ በደንብ እንደተሰማ የድምጽ ዳሳሾች አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ኃይለኛ የሞገድ ድምጽ እንደ ቺሌ፣ ኒው ዚላንድ እና ካናዳ ያሉትን አገሮች ጨምሮ ውቂያኖሶችን አቋርጦ በ 11,000 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘዋ የ ሃዋይ ደሴት ሳይቀር ይሰማ ነበር።
የኒው ዮርኩ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የርዕደ–መሬት ጥናት ተመራማሪ የሆኑት ጎራን ኤክስትሮም ስለ ኖቬምበር 11ዱ ክስተት፡ እንደዚያ ያለ ነገር በሕይወታቸው ዓይተው እንደማያውቁ ለ ናሽናል ጂኦግራፊ ተናግረዋል።
መታደል ነው፤ በእውነት እጅግ በጣም ተዓምረኛ የሆነ ዘመን ላይ ደርሰናል!
ምንጭ፦ National Geographic
[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፵፫፥፪]
“እነሆም፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ መንገድ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተምም ነበር፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።”
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ምስራቅ አፍሪቃ, ሞገድ, ኃይለኛ ድምጽ, ናሺናል ጂኦግራፊክ, የርዕደ-መሬት ጥናት, Earthquake Sensors, East Africa, Mayotte, Seismic Phenomenon, Strange Sound | Leave a Comment »