እኅት ፅጌ ማርያም | “የኢትዮጵያ ታላቁ ኃብቷ ተዋሕዶ ክርስትናዋ”
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 18, 2018
ከልጅነቱ ጀምሮ መርፌ እየተወጋ ያደገው ትውልድ ገና አልገባውም፤ የተስፋቢስነት ወጥመድ ውስጥ እንዲገባ፣ ማንነቱን እንዳያውቅ፣ ምድራዊ መሲህን እንዲጠብቅ ተደርጓል፣ እንደ ዔሳው ብኩርናውን በቀይ ምስር ወጥ/ በሃምበርገር ለነጮች ለመሸጥ ይፈቅዳል።
እስኪ እንታዘብ፤ እኅታችን ፅጌ ማርያም ኢትዮጵያ ስላላት ታላቅ ኃብት ቆንጆ በሆነ መልክ ሃቁን ስትናገር ስቱዲዮ ውስጥ ያሉት “ኢትዮጵያውያን” አድናቆታቸውን በሞቅታና በድንገተኛ መልክ በጭብጨባ እንደመግልጥ፤ ሰይፉ “አጨብጭቡላት እንጂ” ብሎ እስኪነዳቸው ይጠብቃሉ።
Leave a Reply