Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2018
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 15th, 2018

የዛሬዋ ዓለማችን ይህን ትመስላለች | የፈረንሳዩ ማክሮን ሲቀባጥሩ፣ ሽህ መሀመድ ሲያንኮራፉ፣ ፕሬዚደንት ትራምፕ ሲገላምጧቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2018

በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ያለቀበት አንደኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ባለፈው እሁድ 100 ዓመት አስቆጠረ። እለቱ ከትናንት በስቲያ ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ የዓለም መሪዎች በተገኙበት ታስቧል።

በዚሁ የመታሰቢያ ስነስርዓት ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ንግግር ሲያሰሙ፤ የአረብ ሞሮኮ ንጉስ ሲያንቀላፉ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ትራምፕ ክፉኛ ሲገላምጧቸው ይታያሉ።

ለ አንደኛው እና ለሁለተኛው የአለም ጦርነቶች መንሥኤዋ ኢትዮጵያ ናት፦

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ 1906 /ም እስከ ፲፱፻፲፩ 1911/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው።

በ ፲፰፻፹ 1880 ዎቹ እኤአ የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ። በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ ፲፰፻፹፰ 1888 ዓም አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።

አንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት በኢጣሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል፡ እ..አ ከ1895 እስከ 1896 ድረስ የተካሄድ ጦርነት ነው። የኢትዮጵያ በአድዋ ላይ ድል መቀናጀት አውሮፓን ከፍተኛ ቀውጥ ውስጥ ጣላት።

በቅድመ ፪ኛው የዓለም ጦርነት ወቅትም አገራችን ኢትዮጵያ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በፋሽስት ኢጣልያ በግፍ መወረር የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ምክንያት ነበር።

______

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

ኀዳር ፮ ቁስቋም ማርያም፣ የቁስቋሟ ማርያም በምልጃዋ ትጠብቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2018

ኀዳር ፮ ቀን እመቤታችን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ ፲፩፥፩

እንኳን አደረሰን!

ስለ መንበረ ንግስት ቁስቋም

ለእግዝአብሔር ካላቸው አክብሮትና ፍርሀት ለቤተ ክርስቲያንና በንግሥና ለሚያስተዳድሩት ህዝብ ካላቸው ፍቅር የተነሣ በህዝቡ “እምዬ” የሚል ስም የተሠጣቸው ንጉሠ ነገሥት አፄ ሚኒሊክ ከባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ጋር ሠራዊታቸውን አስከትለው ከእንጦጦ ቤተ መንግስታቸው ወደ ፍልውሃ እና ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲንቀሣቀሱ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በታነፀችበት ሥፍራ ላይ ድንኳናቸውን ተክለው ቆይታ ያደርጉበት ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን እረፍት ባደረጉበት ሥፍራ እንቅልፍ ሸለብ ያደርጋቸውና አንዲት እጅግ የተዋበች ሴት ልጅ አዝላ በእቴጌ ጣይቱ አማሣል “ይህንን ቦታ ልቀቁልኝ፤ ቤቴን ልስራበት !!” ስትላቸው ያያሉ፡፡ ንጉሡም ከእንቅልፋቸው በመንቃት ያዩትን ሁሉ ለባለቤታቸው ለእቴጌ ጣይቱ ብጡል ይነግሯቸዋል፤ በመቀጠልም በእቴጌ ጣይቱ አምሣል ስለታየቻቸው በስምሽ ሆስፒታል ትሰሪበት ዘንድ ፈቅጄልሻለሁ ብለው ቦታውን ለእቴጌ ጣይቱ ይሰጧቸዋል፤ ከግዜ በኃላ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ ስለታመሙ እቴጌ ጣይቱ ባለቤታቸውን ማስታመም ይጀምራሉ፤ አብረዋቸው አባታቸውን ያስታምሙ ለነበሩት ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ አፄ ምኒሊክ ንጉሡ ያዩትን ራዕይና ሀኪም ቤቱን ለመስራት ያለመቻላቸውን ጭምር ይነግሯቸዋል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኃላ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ አርፈው እቴጌ ጣይቱም እንጦጦ በቤተመንግስት ተቀምጠው ከእምዬ ምኒሊክ ጋር ያሣለፉትን ህይወት በማስታወስ አዲስ አበባን ቁልቁል እየተመለከቱ “ነበር እንዲህ ቅርብ ነው ወይ አሉ ይባላል !!” ብዙም ዓመት ሳይቆዩ እቴጌም ባለቤታቸውን ተከትለው አረፉ፡፡

ልጅ ኢያሱ መሪነቱን ይዘው በነበሩበት ሠዓት ከመኳንንቱ፤ መሳፍንቱ እና ሹማምንቱ ጋር በአስተዳደር ባለመግባባታቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክን ንግሥናቸውን እንዲረከቡ ሲደረግ ራስ ተፈሪ መኰንን አልጋወራሽነትን እንዲረከቡ ተደረገ፡፡ የንግሥና ህይወታቸውን ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ በመባል በትረ መንግስታቸውን ከተረከቡ በኃላ እቴጌ ጣይቱ የነገሯቸውን አስታውሰው፤ ዛሬ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተተከለችበት ቦታ ላይ ሆስፒታሉን ለመሥራት የመሠረት ቁፋሮ ይጀመራል፡፡ በቁፋሮውም ወቅት አስደናቂ ነገር ይከሠታል፤ ይኽውም “ታቦተ ቁስቋም የሚል ፅሑፍ ያለበት የንግሥት እሌኒ የመዳብ ወንበር እና የብረት መስቀል” ይገኛል፡፡ ንግሥት እሌኒ የአፄ ዘርዓያቆብ እህት ሲሆኑ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ንግሥናቸውም በ1426 /ም እንደነበረ የኢትዮጵያ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ የ492 ዓመት ዕድሜ ያለው ንብረት ከመሬት ተቀብሮ በጥበብ እግዚአብሔር ተጠብቆ ምንም ሳይበላሽ መገኘቱ ድንቅ የእግዝአብሔር ሥራን ያመላክተናል፡፡ በዚህም ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ተደንቀው ንዋየ ቅዱሣቱን መስቀል እና ሌሎቹንም የተገኙትን በታሪከ ነገሥታት በዓታ ለማርያም እንዲቀመጥ ያደርጋሉ፡፡ በቁፋሮው ግዜ በተገኘው ንዋየ ቅዱሣት ምክንያት ሥራው ወደ ተቋረጠው የሆስፒታል ቦታ በመሄድ ቤተክርስቲያን ይሠራ ዘንድ ሕዳር 6 ቀን 1918 .ም የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡ መቃኞውም በአስቸኳይ ይሠራ ዘንድ ለራስ ዳምጠው ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

በበጎ ሥራቸውና ካህናትን በመውደዳቸው ምክንያት ዘመነ ካህናት ተብሎ በሚጠራበት ግዜ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ ዘመነ ንግሥና በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ፍፃሜ ዘመን በሰሜን አዲስ አባባ ልዩ ስሙ እንጦጦ በተባለ ስፍራ በራስጌ ርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም እና ደብረ ኃይል ቅዱስ ዑራኤል ወቅዱስ ኤልያስ በግርጌ ሀመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን አዋሣኝ አድርጋ በመሐል ባለ ልዩ ጉብታ (መሶብ) በምትመስል በግማሽ አዲስ አባባን ሊያሣይ በሚችል ቦታ ላይ መቅደስና ቅኔ ማህሌት ያለው መቃኞ ቤተክርስቲያን ሠርተው በትእዛዙ መሠረት አሠርተው ታቦተ ቁስቋም ማርያምንና ታቦተ መድኃኔዓለም እየሱስን ሌሎችንም ንዋየ ቅዱሳት በእጨጌ ተድላና በዓቃቤ ሠአት መምሬ አበበ ትዕዛዝ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ መኪና በካህናትና ዲያቆናት በምዕመናንና ምዕመናት ታጅቦ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና ታላላቅ ሹማምንት በተገኙበት በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ባራኪነት ታቦŸ ኅዳር 6 ቀን 1919 .ም ገባች፡፡ ስያሜዋንም “መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም” ብለዋታል፤ የመጀመሪያው አስተዳዳሪም ቄስ ገበዝ ብሥራት ኃ/ማሪያም ነበሩ፡፡

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: