Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • November 2018
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  2627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for November 10th, 2018

አፈወርቂ & አህመድ እንደገና ተገናኙ | ሉሲፈራውያኑ ሌላ የሩዋንዳ እልቂት በተዋሕዶ ትግሬዎች ላይ አቅደዋልን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 10, 2018

ሉሲፈራውያኑ ላለፉት 50 ዓመታት ከፍተኛ ትኩረት ያደረጉት የተዋሕዶ ክርስትና ማዕከል በሆነችው በትግራይ ግዛት ላይ ነው። ለዚህም በተደጋጋሚ ሲታዩ የነበሩት፤ ረሃቡ፣ በሽታው፣ ጦርነቱ፣ አስገድዶ ማፈናቀሉ፤ ይመሰክራሉ። ከሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች የበለጠ እዚህ ይፈጸም ነበርና።

በለንደኑ ስምምነት መሠረት፡ ላለፉት 27 ዓመታት መንግስታዊ ሥልጣኑን በከፊልም ቢሆን ለትውልደ ትግራዮች ከሰጡ በኋላ፡ የደቡቡ ኢትዮጵያ ግዛቶች ተወላጆችን (ኦሮሞ፣ ወላሞ፣ ሶማሌ፣ ጉራጌ) በፖለቲካው፣ በተለይ ደግሞ በምጣኔ ኃብትና ሃይማኖት ዘርፍ አገሪቷን እንዲቆጣጠሩና አሁን ለደረስንበት ዘመን እንዲያዘጋጇቸው አደረጓቸው፤ አንድ አዲስ ትውልድ ፈጠሩ ማለት ነው።

ይህ አዲስ ትውልድ በትግሬዎች ላይ ጥላቻ እንዲኖረው ከፍተኛ ቅስቀሳ ከማድረጋቸውም ሌላ የመረጧቸውን ቡድኖች ወደ ኤርትራ በመላክ አሁን እየተካሄደ ላለው ድራማ አሰለጠኗቸው። ለዶ/ር አብይና የትግል ዘመዶቹ በዚህ መልክ ሥልጠና ካደረጉ በኋላ አመቺ ጊዜ በመጠበቅ (የሰው በትግሬ ላይ ያለው ጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ) ሥልጣን ላይ አወጧቸው። የዶ/ር አብይ በሞኙ ሕዝባችን ተወዳጅነት ማትረፍ ሰው ሁሉ በትግሬ ላይ ምን ያህል ጥላቻ እንዳለው ነው የሚያንጸባርቀው፤ ሌላ ለዚህ ዓይነት ተወዳጅነት የሚያበቃ ምክኒያት ሊኖር አይችልም፤ ዜሮ።

ምንም እንኳን ኢአማንያኑ ትውልደ ትግራይ ኢሀዴጎች ፀረተዋሕዶ የሆነ አቋም ያላቸው ኮሙኒስቶች መሆናቸው ቢታወቅም፤ ግን፡ “ምናልባት ልክ እንደ መለስ ዜናዊ ወደ ተዋሕዶ ሊመለሱ ይችላሉ፥ ነበር ዥንጉርጉርነቱን ሊለውጥ አይችልም”፥ በሚል ስጋት ሊቆጣጠሯቸው የሚችሏቸውን የደቡብ ሰዎች (ጴንጤዎችና ሙስሊሞችን) ሥልጣን ላይ ማውጣቱን መርጠዋል። ትግሬ አይሁን እንጅ ሌላው የፈለገው ሰው ሥልጣኑን ቢይዝ የሚደሰት ትውልድ የፈራበት ዘመን ላይ ደርሰናልና።

የሉሲፈራውያኑ ሤራ ዒላማውን እየመታ ነው፤ ዋናው ዒላማቸውም ተዋሕዶ ክርስትና ናት፤ የተዋሕዶ ክርስትና መሠረት ደግሞ ትግራይ ናት። ትግራይን ካጠፉ ለብዙ ዕቅዶቻቸው እንቅፋት የሆነችውን ተዋሕዶን አጠፉ ማለት ነው። አሁን ትግራይን በመክበብ፥ ልክ አረቦችና ፀረሴማውያን የሆኑት ኍ በአይሁዶች ላይ እንደሚያሳዩት ጥላቻ፤ ትግሬዎችንም እንዲሁ መጥፎ ስም እየሰጡ በመኮነን እና በመተናኮል ላይ መሆናቸውን ሁላችንም የምናየው ነው።

ብዙ ጊዜ የሕዝቦች እልቂት ከመጀመሩ በፊት አንዱ የሕዝብ ክፍል ይለይና መጥፎ ስም እንዲሰጠው ይደረጋል፣ ይንቋሸሻል (ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥተህ ገደለው!) እንዲሉ። ከዚያም የራሴ ነው፣ እወደዋለሁ፤ “በውስጤ ነው” የምንለውን ሰው እንድናጣው እንደረጋለን። ብዙ ጊዜ በደንብ በተቀነባበሩ ስሜታዊና አስደናቂ የአውሮፕላን ላይ ግድያዎች።

/ር አብይን ተወዳጅ እንዲሆን ለማድረግ ከሁሉም አቅጣጫ ተሞክሯል፤ የእኛን በጎ መሆን የማይመኙት ምዕራባውያን እና አረቦች እንኳን ያጨበጭቡለታል። ቀጣፊው የእንግሊዝ መንፍስት ቱልቱላ፡ ቢቢስ እንኳን በትናንትናው ዕለት ይህን አቅርቧል፡ “Abiy-mania: Ethiopia Transformed

/ር አብይን የአውሮፕላን በረራዎች እንዲያበዛ፥ በተለይ ደግሞ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ቶሎ ቶሎ እንዲገናኝ ወይም አብሮ እንዲበር አዘውታል።

ይህ ሁኔታ ምንን ነው የሚያስታውሰን? አዎ! ... ሚያዝያ 6 ቀን 1994 .ም ምሽት የሩዋንዳን እና የቡሩንዲን ፕሬዚደንቶች ይዛ ትበር የነበረች አውሮፕላን በሚሳኤል ተመታ ፕሬዚደንት ጁቨን ሀቤራማና እና ሲፕሪንኔታሪማ ተገድለዋል። የሁለቱ ፕሬዚደንቶች መገደለም ለሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል መንስኤ ነበር።

የፕሬዚደንቶቹን አውሮፕላን ለመምታት ተጠያቂዎቹ ምዕራባውያን እንደሆኑ አንዳንድ መረጃዎች ይናገራሉ። በጊዜው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ግብጻዊው ቦትሮስ ቦትሮስ ጋሊ በአንድ ወቅት፡ “ለሁሉቱ ፕሬዚደንቶች መገደል የአሜሪካው የስለላ ተቋም፡ ሲ አይ ኤ ተጠያቂ ነው” ብለው ነበር።

በኢትዮጵያችንስ ተመሳሳይ ፅንፈኛ የሆነ ተግባር ለመፈጸም ታቅዶ ይሆን?

እስኪ እናስበው፡ ሞኙ ሕዝባችን አሁን በሚገኝበት ስሜታዊ ቅዠት ላይ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድን እና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቅን የያዘቸው አውሮፕላን ተመታ ሕይወታቸውን ቢያጡ ምን ሊከተል እንደሚችል። ትግሬዎች ናቸው አውሮፕላኑን የመቱት በማለት፤ በትግራይ እና ትግሬዎች ላይ የሩዋንዳ ዓይነት እልቂት ይመጣል ማለት ነው። አዎ! በቂ የጦር መሣሪያ ከሱዳን በጎንደር በኩል፣ ከሶማሊያ በጅጅጋ በኩል በማስገባት ላይ ናቸው።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዮሐንስ ራእይ ጥልቁ ጕድጓድ? | አረቦች ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ሲጥሩ፡ አምላክ በረሃ ምድራቸውን እየሰነጣጠቀላቸው ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 10, 2018

ላለፉት ሣምንታት በአረብ አገሮች የዘነበው ታይቶ የማይታወቅ ዝናብ መነሻው ከኢትዮጵያ ነበር። አሁን በአርብ በርሃ ላይ ግዙፍ የምድር መሰንጠቅ እየታየ ነው፤ ታዲያ ምናልባት ዝናቡ ያስከተለው ጎርፍ ምድሩን ከፍቶት ይሆን? የዮሐንስ ራእይ ላይ የተጠቀሰው ጥልቁ ጕድጓድስ ይህ ይሆን? ከአረቦቹ ጋር አንበጣም አብሮ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ ነው። ፈጠነም ዘገየም፡ አረቦቹ በአገራችን ላይ ለዘመናት በሚጠንሱስት ተንኮለኛ ሤራ ሳቢያ ወደ ሲዖል መግቢያው ጕድጓድ አሁን እየተከፈተላቸው ይሆን?

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፱]

አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።

የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።

ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።

የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: