ቢጫ ወባ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ገደለ | የእኅተ ማርያም ማስጠንቀቂያ ይህ ይሆን?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 7, 2018
አዎ! ብዙ የተጠነሰሰልን ነገር አለ! ይህ መጀመሪያው ነው፤ እነርሱ “ቢጫ ወባ ነው” ይሉታል።
እኅተ ማርያም ያቀረባቸው ሦስት ምልክቶች፦
-
+ ዓይናችሁ ደም ይመስላል
-
+ ጥፍራችሁ ወደ ቢጫነት ይቀየራል
-
+ እንደ ሳሙና አረፋ ነገር ያስቀምጣችኋል
የዓለም የጤና ድርጅት መግለጫ፡ በሽታዉ በወላይታ አስቀድሞ በመነሳቱ ወደ መላው ኢትዮጵያ እንዳይዛመት ለመከላከል ነዉ ክትባቱን የመስጠቱ ዘመቻ የተጀመረዉ፤ ይለናል። በ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመራው ይህ የዓለም የጤና ድርጅት መንግሥታዊ ካልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የቢጫ ወባ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያ ለማካሄድ ተዘጋጅቷል። “የኢትዮጵያ ሕፃናት መከተብ አለባቸው፡ ይለናል ድርጅቱ።
አሁን 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ የክትባት መርፌዎች ወደ ኢትዮጵያ ተልከዋል።
የአሜሪካው መከላከያ ሚንስትር፡ ፔንታጎን “አይፈለጉም” የሚላቸውን ሕዝቦች ለመዋጋት መርዛማ ትንኞችን ከላብራቶሪ ቀምሞ በማውጣት ላይ በሚገኝበት በእዚህ ዘመን፡ ክትባቱ የቢጫ ወባን ብቻ ለመከላከል የተዘጋጀ እንደማይሆን አሁን የታወቀ ነው።
ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል።
ደጋግሜ የምናገረው ነው፤ ዶ/ር አድሃኖምን የመረጡት ያለ ምክኒያት አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አርገው መሾማቸው በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ያዘጋጁት ተንኮል ስላለ ነው።
ልክ ኡጋንዳዊቷን ወ/ሮ ዊኒ ቢያኒያምን የ “ኦክስፋም” መሪ (የዊኒ ማንዴላን ስም ይዛለች) አድርገው እንደሾሟት፤ ሊቀ ጳጳሳት ዴስሞንድ ቱቱን የዚሁ ድርጅት ልዩ አምባሳደር አድርገው እንደመረጧቸው፣ ወይም ኮፊ አናንን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ እንደመረጧቸው፤ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አድርገው መሾማቸው ያለምክኒያት እንደማይሆን መጠራጠር ግድ ነው።
Leave a Reply