Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2018
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 6th, 2018

ከመጥፎ ሃሳብ፣ ከአጋንንት ሥራ፤ ወገን እና ወገንን በቋንቋ ምክኒያት ከሚለያይ ከዘረኝነት እግዚአብሔር ይሠውረን!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 6, 2018

ነገሥታት መኳንንት ግብር ለመሰብሰብ በየዞኑና በየክፍለሃገሩ ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው በከፋፈሏቸው አካባቢዎች ምክኒያት በማድረግ፡ ወገን እና ወገን፡ ሁላችንም የክርስቶስ ልጆች፣ የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ሆነን፡ ነገር ግን በተልያየ ምክኒያት፤ በቋንቋ ምክኒያት፣ በወንዝና በተራራ ምክኒያት ከመጠላላት፣ ከመወጋገዝ፤ ከመጎዳዳት እግዚአብሔር ይሠወረን! ስነ ልቦናችን በጎ በጎውን እንዲያስብ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ያሳድርብን! ኃይለ አጋንንትን ያስወግድልን! የአጋንንት ሥራ ነው።

ሰዎች ከህገ እግዚአብሔር ወጣ ወጣ ሲሉ እግዚአብሔር ወደ ዓለም ቅጣቶችንና የቅጣት ምልክቶችን ያመጣል። የእኛ ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ባህልና ስልጣኔ እየመሰለን የውጭ ባህሎችን፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣሉ ባህሎችን እየተከተልን፤ ካለባበሳችን ስርዓት ጀምሮ፣ ለሃጢዓትና ለዝሙት ከሚጋብዙ አለባበስ ስነ ሥርዓትና ባህል ጀምሮ፤ መብትና ዲሞክራሲ ተብሎ ሰዶምን እስከመፈጸም ጀምሮ፡ ዓለማችን ዲሞክራሲ ብሎ እግዚአብሔርን የሚያስቆጡ፣ በሰዶም ዘመን ሰዶምና ገሞራ የተቀጡበትን ነገር ባህል ብሎ እንደ ቀላል ነገር ዓለም እየተቀበለው እንደሆነ እናያለን።

ወገኖች፡ ከህገ እግዚአብሔር ወጣ ባልን ቁጥር እግዚአብሔር ዓለምን ይቀጣል

ድንቅ ትምህርት፥ ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: