Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2018
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 28th, 2018

ለሳዑዲው ሽህ ሰይጣነህ ሰግደው የተመለሱት አቶ ደመቀ ጣና ሐይቅ እምቦጭ ላይ ወደቁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 28, 2018

መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ?

ምን ዓይነት ሤራ በአገራችን ላይ እየተጠነሰሰ እንደሆነ፣ ተንኮሉ ከየት እንደሚመጣና ማን እንደሚያመጣው እግዚአብሔር እያየ ነውየሳዑዲን መሬት የረገጠ የእናት ኢትዮጵያን ምድር መርገጥ የማይችልበት ጊዜ በቅርቡ ይመጣልእነርሱን አያድርገን። ለመሆኑ ለምንድን ነው መሪዎቻችን ፍየሎቹ የእግዚአብሔርና የሕዝባችን ጠላት ወደሆኑት አገራት ጉብኝቱን ሲያዘወትሩ፡ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ወዳጆች ወደ ሆኑት ወደ እስራኤል፣ ግሪክ ወይም አርሜኒያ ጉብኝት ከማድረግ የተቆጠቡት?

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ እስጢፋኖስ በቤተክርስቲያን ታሪክ ስለክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 28, 2018

ቀዳሚ ሰማእት / እስጢፋኖስ በጥቅምት ፲፯ ዕለት ሊቀዲያቆናት ተደርጎ በሐዋርያት ተሾመ፡

እንኳን አደረሰን!

መስቀል፤ የመስከረም ፲፯ / ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም ደማቅ ክብረ በዓል

የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንን ግቢ እንዲህ ግጥም፡ ሙልት ብሎ አይቼው አላውቅም፤ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማታችን ያሸበረቁ በጣም ብዙ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም ታታሪ የሆነው ክርስቲያን ወገናችን ሊመሰገን፣ ሊወደስና ሊደነቅ ይገባዋል፤ ብዙ ጊዜ ሲኮነን እንጂ ሲደነቅ አንሰማም። ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አንስቶ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ቀዳሚ ሰማዕት ቅ/እስጢፋኖስን ለማስታወስ በቤተክርስቲያኑ ተገኝቷል።

እስኪ የት ሌላ ዓለም ነው ተመሳሳይ ሁኔታ የሚታየው? በየትኛውስ ሌላ ሃይማኖት? ካቶሊኩና ፕሮቴስታንቱ ከአንድ ሰዓት በኋላ፣ እስላሙ ከሠላሳ ደቂቃ በኋላ ነው ለአምላኮቻቸው ጸልይው የሚበታተኑት።

ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ።

ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው ሥራ በሥራ ሚኒስቴር ኃላፊነት በዘመናዊ መልክ እንዲሠራ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስትሩ ባላምባራስ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአንድ በኩል የአካባቢውም ኗሪ እና የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን በመሆናቸው እና በሚኒስቴራዊ ኃላፊነታችው፤ ሥራውን በቅርብ እየተከታተሉና እየተቆጣጠሩ አሠርተውት የአሁኑ ሕንጻ ግንባታ ፍጻሜ አግኝቶ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ የግብጽ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በተገኙበት ተባረከ፡፡

+ እስጢፋኖስ በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡

+ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀዳጃቸው ሦስቱ አክሊላት፡

  1. ስለንፅህናው ስለድንግልናው

  2. ስለሰማዕትነቱ /ስለምስክሩ/ ስለተጋድሎው

  3. ስለስብከቱ /ስለትምህርቱ/ ስለተአምራቱ

+ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንፆበታል፡፡ /ሰባት ቤተክርስቲያናትን አንጿል፡፡/

+ የቤተክርስቲያን አባቶች የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን እንድናይበት አድርጎናል ሲሉ ይገልፁታል እውነት ነውና፡፡

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: