በተዋሕዶ ላይ ያነጣጠረው ጦርነት ከሁሉም አቅጣጫ ነው እየመጣ ያለው። አባቶቻችንን በየገዳማቱ ማጥቃትና መግደል የመጨረሻው ዒላማቸው ነው፤ መጀመሪያ ግን ክርስቲያናዊ ሕይወትን በየመንገዱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በጉርብትና በመቅረብ ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን በመጠጋት ይዋጋሉ።
የተዋሕዶ ልጆች በእናት ቤተክርስቲያናቸው ቅጥር ግቢ እግዚአብሔርን ሲያወድሱ ሙስሊም ፖሊሶች እንዲተናኮሏቸው ተደረጉ(ይገርማል፤ በክርስቲያኖች ከተማ የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዡ ሙስሊም ተደርጓል)።
በሌላ በኩል ደግሞ ከ ራያ ያመጧቸውን የባህል ጨፋሪዎች(ድሮም ወደ አክሱምና ላሊበላ አካባቢ አምጥተው እዚያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸው የጣዖቱን ዋቄዮ አምልኮት ያስፋፉ ዘንድ በእባባዊ መልክ በማቀድ ነበር)በየአብያተክርስቲያናቱ እንዲገቡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለማበላሸትና እምነታችንንም ወደ ባሕላዊ ሥርዓት ለመለወጥ እየሞከሩ ነው። በዚህ አጋጣሚ ግን ፖሊሶች ድርሽ አይሉም።
በነገራችን ላይ፡ እንደ “መስቀል” እና “ጥምቀት” የመሳሰሉትን ክብረ በዓላት የየተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፤ በምህጻሩ UNESCO በሚባለው ድርጅት እውቅናን እንዲያገኝ መደረጉ መንፈሳዊ የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ወደ ዓለማዊው የባህል፣ ወግና ልምድ ሥርዓት ይለወጥ ዘንድ የተጠነሰሰ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው።
ቤተክህነትም ሆነች ምዕመናን ክርስቲያናዊ በዓላታቸውን በአውሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ዕውቅና እንዲያገኙ ከመታገል መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አሊያ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።