በመስከረም ወር ላይ የኦሮሞ ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ለመቃወም በሰላማዊ መልክ በአደባባይ ወጥተው ከነበሩት ብዙ ወገኖቻችን መካከል ሁለት ወጣቶች መገደላቸው የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በታሪካዊው ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የወጣቶቹን ጸሎተ ፍትሀት እና ጸሎት በማከናወን አስፈላጊ የሆነውን ክብርም ተሰጥቷቸው ነበር።
የኀዘን ሥርዓቱ ላይም ብዙዎች ነጭ ለብሰው ይታያሉ።
በቁስቋም ማርያም ውሎዬ ይህን መሰሉ ታሪካዊ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር፤ ቀደም ሲል ስለ ቀብር ሥርዓቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረምና። ይህን እታዘብ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ነው ወደዚህች ቅድስት ቦታ የመራኝ።
በረከታቸው ይደርብን!