የጣዖቱ ዋቄዮ ዛፍ ሲመለክበት በነበረበት ቦታ ላይ ተዓምረኛ የ ቅድስት አርሴማ ጸበል ፈለቀ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 10, 2018
በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወጣቶች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ይህችን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተዋል። ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች የዋንዛ ዛፉን ቅቤ ይቀቡበት ነበር።
አንድ ሌላ የገረመኝ ነገር፡ ቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው፡ አንድ አባት እኔን በቅድስት አርሴማ ጸበል በሚያጠምቁበት ወቅት አንዲት እርግብ በርራ በመምጣት እራሳቸው ላይ ልታርፍባቸው መብቃቷ ነው። በዕለቱ እንዴት ከሩቅ ሠፈር ወደዚህ ቦታ ተመርቼ ለመሄድ እንደበቃሁ አላውቅም፤ ታክሲው ዝምብሎ አወረደኝ፤ ያውም እዚያ የደረስኩት የመጠመቂያው ሰዓት ካለፈ በኋላ ነበር። ተዓምር ነው!
በአዲስ አበባ ለቡ አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ሱባኤ የሚገቡ እህቶችና ወንድሞችን ለማየት በቅቼ ነበር።
እንኳን አደረሰን!
Leave a Reply