Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2018
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October, 2018

ትንቢተ እኅተ ማርያም በሥራ ላይ | ዶ/ር አብይ ወደ አውሮፓ የሄዱት “ኢትዮጵያን” ለመሸጥ ነውን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 31, 2018

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ፈረንሳይን እና ጀርመንን በመጎብኘት ላይ ናቸው። ፈረንሳይና ጀርመን የአውሮፓው አውሬ ዋንኛ ቀንዶች ናቸው። የ ዶ/ር አብይ ጉብኝት የአቶ ለማ መገርሳን ፊርማ ለማጽደቅ ነውን?

እኅተ ማርያም የምትለንን በጥሞና እናዳምጥ፦

ከጥቂት ወራት በፊት ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እና የኢትዮጵያ ቴሌኮምን ለመሸጥ በድብቅ ወደ ጀርመን ሄዶ ነበር፤ የተፈለገውም ሦስቱ ድርጅቶች መጠሪያ ላይ “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ስላለ፡ ኢትዮጵያን ለመሸጥ ነው። ለሦስት ጀርመናውያን ኢትዮጵያን ወክሎ ፊርማውን ፈርሞላቸዋል። ከእነዚህ ሦስት ጀርመናውያን መካከል ሁለቱ የሰው ልጆች ሲሆኑ ሦስተኛው ግን የሰው ዘር አይደለም።”

Joint Declaration Between PM Abiy and President Macron በጥቂቱ:

Both States welcome the intensification of the French Development Agency’s activities in Ethiopia. For this purpose, France and Ethiopia have signed two declarations of intent regarding:

  • the support to Ethiopian Airlines investment program;
  • Macron and Abiy also pledged to increase cultural cooperation, especially on World Heritage sites such as the rock-hewn churches of Lalibela. France will contribute to the maintenance and renovation of the site, Abiy said.
  • Macron announced he will visit Ethiopia in March. (M & M = Mason)

ልጅአልባዎቹና ሰዶማውያኑ መሪዎቻቸው፤ ሜርከልና ማክሮን (M & M) እንኳን ለእኛ ሊቆረቆሩ ቀርቶ ለራሳቸው ዜጎች የማያስቡ፤ የሉሲፈራውያንን ቡድኖች ፍላጎት ከማሟላት በቀር ለመጭው ትውልዳቸው የማይጨነቁ እርኩስ መሪዎቹ እንደሆኑ በመደቆስ ላይ ያሉት ሕዝቦቻቸው ይመሰክራሉ። ፕሪዚደንት ማክሮን በፈረንሳይ፣ አንጌላ ሜርከል በጀርመን የተጠሉ ፖለቲከኞች ናቸው።

አንጌል ኤሊዛቤል ሜርከል ያው በትናንትናው ዕለት ከፖለቲካው ዓለም ለመሰናበት ቃል ገብተዋል (አንድ ቀን፡ ከወስላታው ማክሮን ጋር የአውሮፓው ህብረት መሪ ለመሆን ስለሚፈልጉ ምናልባት ከሃላፊነትና ተጠያቂነት ለመሸሽ በማሰብ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም፡ የኢትዮጵያ አምላክ መልአክቱንና መልዕክቱን ልኳል፤ ዶ/ር አብይ ጀርመንን በሚጎበኙበት ዋዜማ)

ሰዶማውያን የተደሰቱበት፣ እነ ሜርከል፣ ማክሮን፣ ሜይ እና መሀመዳውያን (4 x M) የሚያሞካክሹትና የሚደግፉት የእኛ መሪ ለሕዝባችን በጎ ነገር ሊሠራ በፍጹም አይችልም፤ በጭራሽ አይሆንም!!!

እህታችን በእውነት ትልቅ መልዕክት ነበር ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ያስተላለፈችልን። እንመናት፤ አውሮፓና አሜሪካ ውስጥ ሰውመሰል ፍጥረታት በየቦታው አሉ፤ በእብራይስጡ ኔፌሊም፣ በግዕዙ ደግሞ ረዓያት ከሚባሉት የወደቁ መላዕክት የተገኙ ዘሮች በመካከላችን አሉ ማለት ነው።

በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ግዕዙ “መላእክት ውሉደ ሰማያት” የሚል መጠሪያን ይጠቀማል። ይህም ሲተረጎም የሰማያት ልጆች መላእክት ማለት ይሆናል። አንደ ማስረጃ ከሚጠቀሱት ጥቅሶች መካከል እንመልከት፡

የሰው ልጆች ከበዙ በኋላ እንዲህ ሆነ። በእነዚያ ወራት መልከ መልካሞችና ደመ ግቡዎች ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። የሰማይ ልጆች መላእክትም እነርሱን አይተው ወደዷቸው። እርስ በርሳቸውም – “ኑ ለእኛ ከሰው ልጆች ሴቶችን እንምረጥ፤ ለእኛም ልጆችን እንውለድ” አሉ። አለቃቸው ስማዝያ – “እኔስ ይህ ሥራ ይሠራ ዘንድ ምናልባት አትወድዱ እንደ ሆነ እፈራለሁ። የዚህችም ታላቅ ኀጢያት ፍዳ ተቀባይ እኔ ብቻ እሆናለሁ” አላቸው። “ይችን ምክር እንዳንለውጣት÷ ይችንም ምክር ቁም ነገር እንድናደርጋት ሁላችን መሐላ እንማማል፤ እርስ በእርሳችንም እንወጋገዝ” ብለው ሁሉም መለሱለት። ያንጊዜም ሁሉም አንድ ሆነው ማሉ፤ እርስ በርሳቸውም በነገሩ ተወጋገዙ፤ ሁሉም ሁለት መቶ ሆኑ። አርዲስ ወደሚባል ቦታም ወረዱ፤ ይኸውም የኤርሞን ተራራ ራስ ነው።” [ሄኖክ21-7]

ይህ መጽሐፈ ሄኖክ በእነዚህ “መላእክት” ተብለው በተገለጹት እና በሰው ልጆች መካከል የነበረው ጾታዊ ተራክቦ ውጤት የነበሩትን “ኔፊሊም” ወይም “ረዓይት” ስለተባሉት ፍጥረቶች ሲገልጽ እንዲህ ይላል፡

እነርሱም ፀንሰው ረጃጅሞች ረዓይትን ወለዱ። ቁመታቸው ሦስት ሦስት ሺህ ክንድ ነበር። እነዚህም ሰዎች እነርሱን መመገብ እስኪሳናቸው ድረስ ሰው የደከመበትን ሁሉ በሉ። ረዓይትም ሰዎችን ይበሏቸው ዘንድ ተመለሱባቸው። በወፎችና በአራዊት÷ በሚንቀሳቀሱና በዓሳዎቸም ይበድሉ ዘንድ ጀመሩ። እርስ በርሳቸውም ሥጋቸውን ተባሉ፤ ከእርሷም ደምን ጠጡ። ያንጊዜም ምድር ዐመፀኞችን ከሰሰቻቸው።” ሄኖክ [212-16]

የ ረዓይቶች ዝርያው ስኮትላናዳዊው ነፃግምበኛ ጄምስ ብሩስ መጽሐፈ ሄኖክንና ሌሎችንም የኢትዮጵያ ንብረቶችን ሠርቆ መውሰዱን አንረሳም።

አሁን መጠየቅ ያለብን፡ የተመረጡትን ጨምሮ፡ ብዙ ኢትዮጵያውያንን በአስገራሚ መልክና ፍጥነት ያሳቱት የእኛስ መሪዎች ከእነዚህ የረዓይት ዘሮች የተገኙ ይሆኑን? ወይስ ሊቁ አባታችን መሪራስ አማን በላይ “መጽሐፍ ብሩክ፤ ዣንሸዋ ቀዳማዊ” በሚለው ድንቅ መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት “በኢዩር ሰማይ ክልል ውስጥ ከአሉት አሥራ ሁለት ዓለሞች ስም መካከል፡ “ሰውድ” የሚባለው ዓለም ይገኝበታል።” ብለው እንደገለጹት መሪዎቻችን ከሰውድ ዓለም ነውን የተገኙት?

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሜክሲኮ እና ኢንዶኒዥያ አውሮፕላን አደጋዎች ሲነጻጸሩ | አላህ አያድንም፥ ክርስቶስ ግን ያድናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 30, 2018

በዛሬው ዕለት፡ እ..አ ጥቅምት 29 / 2018

189 መንገደኞችን የያዘው የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን ከመከስከሱና ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመሞታቸው በፊት እንዴት እንደሚጮሁና አላሃቸውንም እንደሚማጸኑ ቪዲዮው ያሳየናል።

+ ማክሰኞ ዕለት፡ እ... ነሐሴ 31 / 2018 .

103 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረው የሜክሲኮ አውሮፕላን ተመሳሳይ አደገኛ ሁኔታ ላይ ነበር፤ ቀጣዩ ቪዲዮ ላይም መንገደኞቹ አንዱን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲማጸኑ ይሰማሉ። ሁሉም ተሳፋሪዎች በተዓምሩ ተርፈዋል።

ተዓምሩን በከፊልም ቢሆን በቪዲዮ የቀረጸው አብሮ ይጓዝ የነበረውና፡ እስልምናን በመተው ወደ ክርስትና የመጣው ኢራናዊ ነው።

ሁለት ደቂቃ በሚወስደው ቪዲዮው ላይ፡ አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት እና ከአደጋውም በኋላ ከበስተጀርባ ሴቶች፣ ወንዶች እና ሕፃናት ሲጯጯሁ ይሰማል፤ የ እግዚአብሔር ስም ጮክ ብለው ሲጠሩ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ባክህ በሩን ክፈተውበማለት ሲማፀኑ ይሰማሉ።

የቪዲዮው አንሺ ኢራናዊ በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፦

በእግዚአብሔር ጸጋ ደህና ነኝ፡ እርሱ ይመስገን በህይወት አለን፣ ይህ ሌላ ነገር አይደለም ትልቅ የእግዚአብሔር ተዓምር ነው፣ ሕይወት ስላለሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብድር አለበኝ፣ ዲያቢሎስ ሕይወቴን ሊወስድ እችላለሁ ብሎ አስቦ ነበር፡ ነገር ግን አሁን እንዲያውም ለ ኢየሱስ ክርስቶስ እራሴን በይበልጥ እንደሰጥ ረድቶኛል”

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

Happy Autumn 2018

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 29, 2018

____________

Posted in Ethiopia, Music, Photos & Videos | Tagged: , , , | Leave a Comment »

ለሳዑዲው ሽህ ሰይጣነህ ሰግደው የተመለሱት አቶ ደመቀ ጣና ሐይቅ እምቦጭ ላይ ወደቁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 28, 2018

መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ?

ምን ዓይነት ሤራ በአገራችን ላይ እየተጠነሰሰ እንደሆነ፣ ተንኮሉ ከየት እንደሚመጣና ማን እንደሚያመጣው እግዚአብሔር እያየ ነውየሳዑዲን መሬት የረገጠ የእናት ኢትዮጵያን ምድር መርገጥ የማይችልበት ጊዜ በቅርቡ ይመጣልእነርሱን አያድርገን። ለመሆኑ ለምንድን ነው መሪዎቻችን ፍየሎቹ የእግዚአብሔርና የሕዝባችን ጠላት ወደሆኑት አገራት ጉብኝቱን ሲያዘወትሩ፡ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ወዳጆች ወደ ሆኑት ወደ እስራኤል፣ ግሪክ ወይም አርሜኒያ ጉብኝት ከማድረግ የተቆጠቡት?

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ እስጢፋኖስ በቤተክርስቲያን ታሪክ ስለክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 28, 2018

ቀዳሚ ሰማእት / እስጢፋኖስ በጥቅምት ፲፯ ዕለት ሊቀዲያቆናት ተደርጎ በሐዋርያት ተሾመ፡

እንኳን አደረሰን!

መስቀል፤ የመስከረም ፲፯ / ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም ደማቅ ክብረ በዓል

የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንን ግቢ እንዲህ ግጥም፡ ሙልት ብሎ አይቼው አላውቅም፤ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማታችን ያሸበረቁ በጣም ብዙ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም ታታሪ የሆነው ክርስቲያን ወገናችን ሊመሰገን፣ ሊወደስና ሊደነቅ ይገባዋል፤ ብዙ ጊዜ ሲኮነን እንጂ ሲደነቅ አንሰማም። ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አንስቶ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ቀዳሚ ሰማዕት ቅ/እስጢፋኖስን ለማስታወስ በቤተክርስቲያኑ ተገኝቷል።

እስኪ የት ሌላ ዓለም ነው ተመሳሳይ ሁኔታ የሚታየው? በየትኛውስ ሌላ ሃይማኖት? ካቶሊኩና ፕሮቴስታንቱ ከአንድ ሰዓት በኋላ፣ እስላሙ ከሠላሳ ደቂቃ በኋላ ነው ለአምላኮቻቸው ጸልይው የሚበታተኑት።

ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ።

ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው ሥራ በሥራ ሚኒስቴር ኃላፊነት በዘመናዊ መልክ እንዲሠራ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስትሩ ባላምባራስ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአንድ በኩል የአካባቢውም ኗሪ እና የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን በመሆናቸው እና በሚኒስቴራዊ ኃላፊነታችው፤ ሥራውን በቅርብ እየተከታተሉና እየተቆጣጠሩ አሠርተውት የአሁኑ ሕንጻ ግንባታ ፍጻሜ አግኝቶ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ የግብጽ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በተገኙበት ተባረከ፡፡

+ እስጢፋኖስ በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡

+ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀዳጃቸው ሦስቱ አክሊላት፡

  1. ስለንፅህናው ስለድንግልናው

  2. ስለሰማዕትነቱ /ስለምስክሩ/ ስለተጋድሎው

  3. ስለስብከቱ /ስለትምህርቱ/ ስለተአምራቱ

+ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንፆበታል፡፡ /ሰባት ቤተክርስቲያናትን አንጿል፡፡/

+ የቤተክርስቲያን አባቶች የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን እንድናይበት አድርጎናል ሲሉ ይገልፁታል እውነት ነውና፡፡

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር | መብረቅ የቀሰቀሰው እሳት ቤተክርስቲያኑን ሲያቃጥል የተረፈው የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል ብቻ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 27, 2018

በአሜሪካዋ ቦስተን-ዋክፊልድ ከተማ150 ዓመት ዕድሜ የነበረው ታሪካዊ የ ቤተክርስትያንን ሕንጻ በመብረቅ ከተመታ በኋላ በጣም ኃይለኛ እሳት ተቀስቅሶ ሁሉም ነገር ድብን ብሎ ሲቃጠል፡ የተረፈው አንድ ትልቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል ብቻ ነው። ስዕሉ ትንሽ ጭረት ወይም ጥላሸት እንኳን ሳይነካው ነበር ሙሉ በሙሉ ከወደመው ህንጻ የወጣው።

ይህን ተዓምር ያዩ የቦስተን ከተማ ነዋሪዎች በስዕሉ መትረፍ በጣም መደሰታቸውንና መጽናናታቸውንም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ቃጠሎው የሰው ሕይወት አላጠፋም፤ ነገር ግን የ 1 ሚሊየን ዶላር ንብረት ወድሟል።

በተጨማሪ፡ የእሳቱ ነበልባል የራስ ቅል የመሰል ቅርጽ ያሳየናል (በስተጎን ሲታይ)። የሚገርም ነገር ነው፤ ምን ሊሆን ይችላል?

በእውነት እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነ ዘመን ላይ እንገኛለን!

Large Painting of Jesus Christ Miraculously Survives Hellish Seven-Alarm Fire Completely Intact While 150-Year-Old Church is Destroyed

  • Large painting of Jesus Christ miraculously SURVIVES hellish seven-alarm fire completely intact while 150-year-old church is destroyed
  • First Baptist Church in Wakefield, Massachusetts was destroyed in a furious fire
  • The 150-year-old church is a landmark in the Boston area
  • Fire broke out Tuesday evening, ignited by a lightening bolt strike witnesses say
  • The blaze completely burned the church spire, roof, and interior
  • Although the structure still stands, it suffered an estimated $1million in damages
  • A painting of Jesus Christ that once hung in the church entrance was pulled practically unscathed from the rubble
  • For grieving parishioners, the recovered painting is a sign of hope
  • The church will be torn down and demolition started Wednesday

A seven-alarm hellish fire has destroyed a historic 150-year-old church in Massachusetts – but a massive painting of Jesus Christ miraculously survived the blaze.

First Baptist Church in Wakefield, Massachusetts has been a landmark in the Boston area for over 100 years but its interior and roof was reduced to ash after the church was reportedly struck by a lightening bolt and a furious fire broke out on Tuesday evening.

But by some stroke of luck, the human-sized painting of Jesus that once hung at the front entrance of the church was recovered practically unscathed, according to Boston25.

The fire completely destroyed the 150-year-old church, burning down its spire and roof. For parishioners the recovered painting is a sign of hope for their community.

According to witnesses, a lightning bolt struck the steeple of the church, which was built in 1872, around 7pm as powerful thunderstorms rolled through the greater Boston area.

The strike ignited the fire that quickly spread throughout the church structure.

Officials have not announced a cause of the fire yet.

The vicious inferno devastated the church, but parishioners found comfort in the fact that the Jesus Christ painting somehow survived the blaze.

‘It’s a beautiful sign and a reminder that Jesus is with us,’ parishioner Maria Kakolowski said.

‘I’m personally just taking as a sign and a reminder that the Jesus Christ we serve is still alive and even though our church building is gone, our church is here and the God that we serve is still here,’ she added.

The portrait will be gifted for a former pastor at the church.

A team of more than 100 firefighters toiled for hours to quell the sudden inferno, some sustaining minor injuries.

‘I was down about a mile away and I just saw this fireball in the sky. It just went up like a tinderbox. It’s a building built in 1870 and and it’s balloon-style so once the fire starts you know the whole building just went up quickly,’ the church’s pastor Reverend Doctor Norm Bendroth said.

When the fire was finally extinguished much of its exterior was still standing but its steeple and roof was completely burned down to its skeletal wooden frame.

A meeting was taking place in the church at the time of the fire but everyone was evacuated by the time the flames gained momentum.

No one was harmed in the blaze and the church will be torn down. Talks are in place to see if they will rebuild the structure.

The fire cost about $1million in damages, according to the Boston Globe.

‘When the windows were all aglow — every stained glass window was aglow — it looked like you were looking into hell. It was just an awful, awful sight,’ former parishioner Susan Auld said.

The church released a statement following the fire:

‘While we lost our historic building from a lightning strike this week, we praise Jesus that our church community was kept safe. A very big thank you to the many firefighters who did their jobs with excellence, and to the outpouring of support from the community,’ the statement said.

‘We know that we serve a God who specializes in restoring brokenness and who can bring beauty even from ashes. So we move into the future with trust, hope, and gratitude,’ the statement continued.

Parishioners gathered at the church site on Wednesday to see crews clear the wreckage. The remains of the spire were dismantled as was the Tall Spire Nursery School which was housed inside.

People on the scene took comfort in seeing that the painting of Jesus, standing in a white robe with his hands extended, was successfully recovered.

Source

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በታጣቂዎች የተከበቡት የአሰቦት ገዳም መነኰሳት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤ የወረዳው አስተዳዳሪ “ለቃችሁ ውጡ” በማለት ከታጣቂዎቹ ጋር አብሯል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 26, 2018

  • + ከጥቅምት 7 ጀምሮ በየምሽቱ ከታጣቂዎቹ ጋራ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ላይ ናቸው፤
  • + ታጣቂዎቹ፣“የኦነግ ወታደሮች ነን”ቢሉም ተከፋይ ሁከተኞች ሊኾኑ እንደሚችሉ ተነግሯል፤
  • + የወረዳው አስተዳደሪ፣ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው በዞኑ የተላለፈለትን ትእዛዝ አልፈጸመም፤
  • + በሶማሌ ክልል ወሰን በኩል የመከላከያ ድጋፍ ቢጠየቅም ኦሮሚያ መፍቀድ አለበት፤ተብሏል፤
  • + አንዱ በሌላው ሲያመካኝ፣ የግንቦት 1984 ዐይነቱ ወረራና እልቂት እንዳይደገም አስግቷል፤
  • + በስብሰባ ላይ ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በአስቸኳይ የኦሮሚያን ክልል እገዛ ሊጠይቅ ይገባል፤
  • + ፓትርያርኩ በመክፈቻቸው እንዳሉት፣ በተጽዕኖና በማፈናቀል የማዳከም ስልቶች አንዱ ነው፤
  • + ከጸጥታና ፍትሕ አካላት ጋራ በመቀናጀት፣ጥቃቱን ከወዲሁ ለማምከን መፍጠን ያስፈልጋል፤

ማንነታቸው በውል በማይታወቁ ታጣቂዎች የጥቃትና ወረራ ስጋት ውስጥ ቀናትን ያስቆጠሩት ጥንታዊው የአሰቦት ደብረ ወገግ ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ገዳም ማኅበረ መነኰሳት፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለመንግሥት አካላት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፡፡

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሜኤሶ ወረዳ የሚገኘው የገዳሙ መነኰሳት እንደተናገሩት፣ ታጣቂዎቹ ከጥቅምት 7 ጀምሮ በየምሽቱ ወደ ገዳሙ በመተኰስ ማኅበሩን ለማሸበር እየሞከሩ ሲኾን፤ የወረዳውና የዞኑ አስተዳደር ጥበቃ እንዲያደርጉላቸውና ከይዞታቸው እንዲያስወጡላቸው ያደረጉት ጥረት ውጤት ባለማስገኘቱ የክልሉ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥሪ አሰምተዋል፡፡

ገዳማውያኑ እንዳስረዱት፣ በቁጥር ከ25 ያላነሱ ታጣቂዎቹ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ የገዳሙ ይዞታ ወደኾነው ደን ውስጥ ገብተው ድንኳን ተክለው ተቀምጠዋል፡፡ ስለማንነታቸው ሲጠየቁ፣ የኦነግ ወታደሮች እንደኾኑና የመጡበትም ምክንያት፣ “የሶማሌ ወታደሮች ወደዚህ ይገባሉ ተብለን ወደ እነርሱ ነው የምንሔደው፤” ብለዋል፡፡ ቀደም ሲልም ጫካ ውስጥ ገብተው ወደ ገዳሙ በዘፈቀደ የሚኩሱ፣ ዐጸዶቹን የሚቆርጡ ሁከተኞች እንደነበሩ ያወሱት ገዳማውያኑ፣በኦነግ ስም ቢጠሩም በብጥብጥ ለመጠቀም የፈለጉ ተከፋዮች ሊኾኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በተለይ ባለፉት ሦስት ቀናት በየምሽቱ በተኩስ ለማሸበር የሚያደርጉትን ሙከራ አጠናክረው እንደቀጠሉና መሰል አጸፌታ ከመስጠት ውጭ ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ መነኮሳቱ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሰኞ ምሽት ከምሽቱ 2 እስከ 4 ሰዓት የቀለጠ የተኩስ ልውውጥ እንደነበርና በትላንትናው ዕለት ሌሊትም ኹለት አብሪ ጥይቶችን ወደ ገዳሙ በመተኰሳቸው መጠነኛ አጸፌታ እንደሰጡ አክለዋል፡፡

የችግሩ ምልክት እንደታየ መነኰሳቱ ጥያቄያቸውን ያቀረቡለት የሜኤሶ ወረዳ አስተዳዳሪ፣“የያዛችሁት የሰው ቦታ ነው፤ ለምን ለቃችሁ አትወጡም” በማለት እንደሚያመናጭቃቸው ገዳማውያኑ ተናግረዋል፤ ለዞኑ ባቀረቡት አቤቱታ፣ ጥበቃ እንዲያደርግላቸውና መፍትሔ እንዲሰጣቸው ቢታዘዝም ሓላፊነቱን ለመወጣት ፈቃደኛ እንዳልኾነ አስታውቀዋል፡፡

ገዳሙ ከሶማሌ ክልል በሚዋስንበት አቅጣጫ ለሚገኘው የመከላከያ ኃይል ድጋፍ መጠየቃቸውን መነኰሳቱ ጠቅሰው፣“የኦሮሚያ ክልል በመኾኑ ፈቃድ ካላገኘን መግባት አንችልም፤ክልሉን ደጋግማችሁ ጠይቁ፤ የሚል ምላሽ ብቻ ነው የሰጡን፤” ብለዋል፡፡ አንዳችም ጥበቃ እየተደረገላቸው ባለመኾኑ የክልሉ መንግሥት እና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ለድረሱልን ጥሪያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጧቸው ተማፅነዋል፡፡

ከጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ ዘኢትዮጵያ ደቀ መዛሙርት አንዱ በነበሩት ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል በ13ኛው መ//ዘ የተመሠረተው ገዳሙ፣ በግራኝ ወረራ ጊዜ ከጠፉት ገዳማት አንዱ ነበር፡፡ እንደገና የቀናው እጅግ ዘግይቶ በ1911 .. ሲኾን፣ አቅኝውም የታወቁት ሊቅ አለቃ ገብረ መድኅን ናቸው፡፡ በ1912 .. የጻድቁ አቡነ ሳሙኤልን ቤተ ክርስቲያን በሣር ክዳን ሠሩ፡፡ በ1918 .. ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሥራት ጀምረው፣ ፍጻሜውን ሳያዩ ቢያርፉም በ1919 .. የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተጠናቋል፡፡

1929 .. በሶማልያ በኩል በገባው የፋሽስት ኢጣልያ ጦር ገዳሙ ተዘርፏል፤ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንም ፈርሷል፡፡ በወቅቱ በገዳሙ ከነበሩት 500 መነኮሳት መካከል ከፊሉ ታቦቱን ይዘው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲሸሹ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ተወስደው ታስረዋል፡፡ ወራሪው ከተባረረ በኋላ መነኮሳቱ በ1936 .. ተሰባስበው ወደ አሰቦት መጡ፡፡ ከ22 ዓመት በኋላ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ በ1952 .. ተሠራ፡፡ ግንቦት 16 ቀን 1984 ..፣ የኦሮሚያ ነጻነት እስላማዊ ግንባር (ጃራ) የተባለ አክራሪ ኃይል፣ ገዳሙን ወርሮ በዙሪያው የሚኖሩ መነኮሳትንና 16 ክርስቲያን አባወራዎችን አርዷል፡፡

ካህናትንና ክርስቲያኖችን በተጽዕኖና በጥቃት ማፈናቀል፣ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም አንዱ ስልት እንደኾነ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግራቸው የጠቀሱት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በየአካባቢው ከሚገኙ የፍትሕ እና ጸጥታ አካላት ጋራ በመቀናጀት ጥቃቶችን አስቀድሞ የማምከንና ሲደርሱም የመከላከል አሠራር እንደሚቀየስ ጠቁመዋል፡፡ የታጣቂዎቹ ፍላጎት፣ ድምፃቸውን አጥፍተውና መነኮሳቱን አጋዥ አሳጥተው ገዳሙን ማጥፋት እንደኾነ መነኮሳቱ እየተናገሩ በመኾኑ፣ ከክልሉ መንግሥትና ከወረዳው አስተዳደር ጋራ በመነጋገር ለድረሱልን ጥሪያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው መፍጠን ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አንዴ ሙስሊም ፖሊሶችን፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ፡ የራያ ጨፋሪዎችን ወደ ቤተክርስቲያናችን ይልኳቸዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 25, 2018

በተዋሕዶ ላይ ያነጣጠረው ጦርነት ከሁሉም አቅጣጫ ነው እየመጣ ያለው። አባቶቻችንን በየገዳማቱ ማጥቃትና መግደል የመጨረሻው ዒላማቸው ነው፤ መጀመሪያ ግን ክርስቲያናዊ ሕይወትን በየመንገዱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በጉርብትና በመቅረብ ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን በመጠጋት ይዋጋሉ።

የተዋሕዶ ልጆች በእናት ቤተክርስቲያናቸው ቅጥር ግቢ እግዚአብሔርን ሲያወድሱ ሙስሊም ፖሊሶች እንዲተናኮሏቸው ተደረጉ(ይገርማል፤ በክርስቲያኖች ከተማ የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዡ ሙስሊም ተደርጓል)

በሌላ በኩል ደግሞ ከ ራያ ያመጧቸውን የባህል ጨፋሪዎች(ድሮም ወደ አክሱምና ላሊበላ አካባቢ አምጥተው እዚያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸው የጣዖቱን ዋቄዮ አምልኮት ያስፋፉ ዘንድ በእባባዊ መልክ በማቀድ ነበር)በየአብያተክርስቲያናቱ እንዲገቡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለማበላሸትና እምነታችንንም ወደ ባሕላዊ ሥርዓት ለመለወጥ እየሞከሩ ነው። በዚህ አጋጣሚ ግን ፖሊሶች ድርሽ አይሉም።

በነገራችን ላይ፡ እንደ “መስቀል” እና “ጥምቀት” የመሳሰሉትን ክብረ በዓላት የየተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፤ በምህጻሩ UNESCO በሚባለው ድርጅት እውቅናን እንዲያገኝ መደረጉ መንፈሳዊ የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ወደ ዓለማዊው የባህል፣ ወግና ልምድ ሥርዓት ይለወጥ ዘንድ የተጠነሰሰ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው።

ቤተክህነትም ሆነች ምዕመናን ክርስቲያናዊ በዓላታቸውን በአውሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ዕውቅና እንዲያገኙ ከመታገል መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አሊያ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሸህ ሰይጣነህ ለአቶ ደመቀ መኮንን ሃሰን አብዱልቃድር፦ “ሁለተኛ አገርህ ወደ ሆነችው ወደ ሳዑዲ እንኳን ደህና መጣህ”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 24, 2018

የዜናው ርዕስ እራሱ ይገርማል “የሁለቱ “ቅዱስ” መስጊዶች ጠባቂ ሞግዚቱ የሳውዲ ንጉሥ ለአረብ መሪዎች አቀባበል አደረጉ” ይላል። አቶ ደመቀ መኮንን ሃሰን አብድሉልቃድር አረብ ናቸው ማለት ነው።

ምናልባት አሁን፡ ለብዙ ዓመታት በሳዑዲ እስር ቤት የሚማቅቁትና የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችንን “አስፈታኋቸው” በማለት ሰሞኑን ለሚታየው ድራማ አስተዋጽዖ ያበረክቱ ይሆናል አቶ ደመቀ።

እነዚ ሰው ነገሮች እጅግ በጣም ተቻኩለዋል፡ አሁንማ የሚደብቁት ነገር የለም!

______

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

እኅተ ማርያም ባየችበት ዕለት፡ ጨረቃዋ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ተከባ፤ ሰማይ ላይም የኢትዮጵያ ካርታ በደመና ተስላ እኔም አይቼ ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 21, 2018

ተዓምር በኢትዮጵያ፦

የኢትዮጵያ ካርታ፣ ከማርያም መቀነት ያገኘናቸው አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለማት እንዲሁም መስቀልና ሌሎች ምልክቶች ሰማይ ላይ በየጊዜው እየታዩን ነው።

አዎ! በእውነት ድንቅ ዘመን ላይ ነን!“ዓይን የሌለው ያዳምጥ፤ ጆሮ የሌለው ይመልከት!“ የምንልበት ዘመን ላይ ደርሰናል።

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: