በሙስሊም ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ዛቻ ከደረሰባቸው በኋላ በላይኛው የግብፅ ኮፕቲክ ሃገረሰብከት ውስጥ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት አሁን ለመዘጋት በቅተዋል።
የክርስቲያኖች ጠበቃ የሆኑት ጋሚል አይይ እንደገለጹት ሦስት ሺህ የሚሆኑት የመንደሩ ክርስቲያን ነዋሪዎች ለቤተክርስቲያን ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት በመታገል ላይ ናቸው። ከሁለት ዓመት በፊት የግብጽ መንግስት ዓብያተ ክርስቲያናት ልክ እንደ መስጊዶች አንድ ዓይነት ሕጋዊ መብት ሰጠቻለሁ ብሎ ነበር።
እስካሁን 3,500 የሚሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ህጋዊ ዕውቅና ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም በመንግስት ያልተፈቀደላቸው አብያተ ክርስቲያናትን ግን ቀስ በቀስ በመዘጋት ላይ ናቸው። የሚገርም ነው፡ “ህጋዊ ዕውቅና ያልተሰጠው መስጊድ ግን አገልግሎት ሲያቋርጥ ወይም ሲዘጋ ተሰምቶ አይታወቅም። ይህ ፍትሕ ነውን? እኩልነት የት አለ? የሃይማኖት ነጻነት የት ነው? ህጉ የት አለ? የመንግስት ተቋማት የት ይገኛሉ?” በማለት ኮፕት ወገኖቻችን ይጠይቃሉ።
ከ ሉክሶር ከተማ በስተደቡብ በምትገኘው ድንግል ማሪያም እና ቅዱስ ሞህራኤል ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ ነሐሴ ፳፪ ላይ አንድ ሺህ በሚሆኑ ሙስሊሞች የተቃውሞ ጩኸት እና ወረራ ሳቢያ እንድትዘጋ ተደርጋለች። ቪዲይዎ ላይ እንደሚታየው ከ ፲፮ እስከ ፳፮ ዓመት እድሜ ያላቸው በርካታ ሙስሊም ወጣቶች “አላህ ዋክብር! (አላህ ከሁሉም አማልክት ይተልቃል) እና ” የእኛ የእስልምና መንደር ውስጥ ቤተክርስቲያን እንዲኖረን አንፈልግም” እያሉ በጥላቻ በመጮህ ቤተክርስቲያኗን ከብበው እንደነበረ፤ “የፊት ለፊቱን በር ለመስበር ሞክረው ነበር ነገር ግን ከውስጥ ቆልፈነው ነበር፡ ወዲያውኑ የፖሊስ ፖሊሶች መጥተው ሙስሊሞቹን ሊያባርሩ በቅተዋል፤ ነገር ግን ማንንም ማሠር አልፈለጉም።” በማለት የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ በሃዘን ተናግረዋል።
ይህ ሁሉ ጉድ በሉክሶር ሃገረ ስብከት አካባቢ ብቻ ነው እየተከሰተ ያለው። በተለያዩ የግብጽ አውራጃዎችም ተመሳሳይ ፀረ–ክርስቲያኖች እንቅስቃሴ በመጧጧ ላይ ነው።
ያውም በአገራቸው! ኮፕት ወገኖቻችንን ትክክለኛዎቹ የግብጽ ነዋሪዎች፣ ከባቢሎን አረብ ሙስሊም ወራሪዎች በፊት እዚያ የነበሩ ግብጻውያን ናቸው። ግብጻውያን በአገራቸው ብቸኛውና ትክክለኛውን አምላካቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማምለክ እንዳይችሉ እየተደረጉ ነው። ምናለ የእኛን ሙስሊሞች ወደ ግብጽ፡ የግብጽን ኮፕቶች ወደ ኢትዮጵያ በመላክ እንደ ግሪክ እና ቱርክ የሕዝብ ልውውጥ ብናደርግ?!
እናት ኢትዮጵያ ባክሽ የሕዳሴውን ግድብ ቶሎ ጨርሺው!
+ Copts Attacked in Egypt’s South Over Homes Used as Churches