ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ጀርመን ዛሬ በምስራቅ…
በምስራቅ ጀርመኗ ኬምኒትስ ከተማ ውስጥ በትናንትናው እሑድ ዕለት፡ ሁለት የሶሪያ እና ኢራቅ አረቦች የ35 ዓመቱን ኩባ–ጀርመናዊ በቢለዋ ቆራርጠው በመግደላቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጀርመናውያን የከተማዋ ነዋሪዎች መንግድ ላይ በመውጣት አረቦችን ማደን ጀመርዋል። በዛሬው ምሽት ከፍተኛ ብጥብጥ ይነሳ ይሆናል ተብሎ ይፈራል።
አንዳንድ ምንጮች እንደጠቆሙት ከሆነ በአንድ የከተማዋ የበዓል ስነሥርዓት ወቅት፡ ይህ ክልስ ኩባ–ጀርመናዊ፡ ሴት ጀርመናውያንን ለመድፈር የሞከሩትን አረቦች ለማባረር ሲሞክር ቢለዋ መዝዘው ይህን ዳንኤል የተባለ ግለሰብ ገደሉት። ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት ጓደኞቹም ክፉኛ ቆስለው ሆስፒታል ውስጥ የሞት አፋፍ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። ሁለተኛው የዳንኤል ጓደኛም (የሩሲያ ዝርያ ያለው ጀርመን) ዛሬ በሆስፒታል ሞቷል።
ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው ቁጣቸውን ለመግለጽ በካርል ማርክስ አደባባይ የወጡትን ጀርመናውያን ፖሊሶች ይመክቷቸዋል፤ ልክ እንደ አንጌላ ኤሊዛቤል ሜርከል፡ አረቦቹን ለመከላከል ማለት ነው። ሜዲያውም የእነዚህ አረብ ወራሪዎች ተባባሪ ነው። ተቃዋሚዎቹ. “Wir sind das Volk!, Das ist unsere Stadt / ሕዝቡ እኛ ነን! ከተማዋ የእኛ ናት!“ የሚሉ መፈክሮችን በጩኸት ያሰማሉ።
ተመሳሳይ የተቃውሞ ድምጽ እንደ አ.አ.አ በ 1989 ዓ.ም ላይ አንጌል ሜርከልን ባፈራው የምስራቁ ኮሙኒስት ጀርመን ሥርዓት ወቅት፡ በዚህች 250 ሺህ ነዋሪዎች ባላት የኬምኒትስ ከተማ (የቀድሞዋ የካርል ማርክስ ከተማ) ይሰማ ነበር።