Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2018
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 18th, 2018

ጅራፍ፣ ችቦ & ሙልሙል | እንኳን ለ በዓለ ደብረ ታቦር(ቡሄ)በሰላም አደረሰን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 18, 2018

የደብረ ታቦር ምሳሌነት

የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡ በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከላይ ሲወጡ ግን አባጣ ጎባጣውን ሜዳና ገደሉን ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለች፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ በሰማይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል /ፊልጵ. 320/፡፡

የደብረ ታቦር ተራራ ይህን ሁሉ ምስጢር የያዘ በመሆኑ በክርስትና ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት፣ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፤ በምእመናንም ዘንድ ቡሔ ይባላል፡፡ የቡሔ በዓል ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ የያዘ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ልናከብረው ይገባናል፡፡

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡

ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፤ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ የት መጣ ግን በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ ምሳሌ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ቡሄ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ምንጭ

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የ ሰይጣን ባፌሜት ሦስተኛው ሃውልት አሥርቱ ትዕዛዛት ሐውልት ጎን በክሊንተን ከተማ ይፋ ተደረገ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 18, 2018

ዋውው! በደብረ ታቦር በዓል ዋዜማ!!!

ዛሬ፡ እ.. 08/08/18 ነው!

ከትናንትና በስቲያ፡ እ..አ ኦገስት 16/ 2018 . የሰይጣን ቤተ እርኩስ ውስጥ የፍየል እራስን የሚያሳየው የባፎሜት ሃውልትን ይፋ አድርጓል። ይህ የሰይጣን ሃውልት 2 ሜትር ቁመት ሲኖረው በ አርካንሳስ ግዛት ዋና ከተማ፡ “ሊትል ሮክ ወይም ትንሽ ድንጋይ” (የፕሬዚደንት ክሊንተን አገር)ዋና የማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ግቢ ውስጥ ከ ከሚገኘው አሥርቱ ትዕዛዛት ሐውልት ጎን እንዲተከል ተደርጓል።

በደብረ ታቦር በዓል ዋዜማ!

ከዚህ በፊት እ..አ በ2012 .ም እንዲሁ በኦክላሆማ እና እ..አ በ2015 .ም ደግሞ በዲትሮይት፡ ሚቸገን እንዲሁ ይህን የሰይጣን ሃውልት፡ ማዘጋጃ ቤቶቻቸው ውስጥ ከአሥርቱ ትዕዛዛት ሐውልት ጎን ተክለውት ነበር።

ይህ ሰነፍና ጨምላቃ ዓለም “አትግደል! አታመንዝር! አትስረቅ! ወዘተ ብሎ በሚያስተምረን ተወዳዳሪ በሌሌው የአሥርቱ ትዕዛዛት ስርዓት ስር መኖር አይፈልግም። ስለዚህም ነው በአይሁድክርስቲያን ዓለሙ ላይ እርኩስ ጣዖት አምላኪዎች ሰዶማውያንን፣ ዮጋ ሂንዱዎችን፣ ቡዳዎች እና እስላሞችን በማሰባሰብ ላይ የሚገኘው።

ፍየል እራሱ ባፎሜት ግንባር ላይ ያለው የሚታየው ኮከብ ሉሲፈራውያኑ መሪዎቻችንን ሰንደቅ ዓላማችን ላይ እንድነለጥፍ ያስገደዷቸው ባለ አምስት ማዕዘን ኮከብ መሆኑ ነው።

/ር አብይ አህመድ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ይህን ኮከብ እንዲነሳ ካላደረገ እርሱም የባፎሜት ልጅ ነው ማለት ነው።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: