Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 16, 2018
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፵፩፥፬]
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፪፥፮]
ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፥ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል።
[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፭፥፲፱]
ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: ሳውዲ አረቢያ, ነፍስ መስረቅ, እስልምና, የኢትዮጵያ ሴት, ዲያብሎስ, ጭካኔ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 16, 2018
ከሁለት ቀናት በፊት በእንግሊዟ ለንደን፡ ብሪታኒያ ምክር ቤት አጠገብ የእግር መንገደኞችንና ብስክሌት አሽከርካሪዎችን ለመግደል አቅዶ የነበረው ሱዳናዊው ሙስሊም በ መኪና አደናቸው።
ይህ ሱዳናዊ ከ ፭ ዓመት በፊት ወደ ብሪታኒያ መጥቶ የብሪታንያን ዜግነት አግኝቷል። የ ፳፱ ዓመት እድሜ ያለው ሳሊህ ካተር ከዚህ ቀደም በዚሁ በዊስትሚንስትር የለንደን ከተማ አካባቢ (ፓርላማው እዚህ ይገኛል) ሽብር ፈጽመው ከነበሩት የበርሚንግሃም ሙስሊሞች ጋር ግኑኝነት እንደነበረው አሁን ተገልጿል።
አይገርምም? እንግሊዞች ለሽብር ፈጣሪዎቹ በ፭ ዓመት ብቻ የብሪታኒያ ዜግነት ይሰጧቸዋል። ፲ ዓመት ቆይተው ዜግነቱን ያላገኙ ኢትዮጵያውያንን አውቃለሁ።
በትናንትናው ዕለት ደግሞ፡ በሱዳን አገር አንድ ፵ ተማሪዎችን የያዘች ጀልባ አባይ ወንዝ ላይ ሰጥማ ፳፬ ሕፃናት ሞቱ፤ ነፍሳቸውን ይማርላቸውና።
ለ ሺህ ዓመታት ውሃውን በነፃ በሚጠጡት ምስጋና ቢሶቹ ላይ እግዚአብሔር ተቆጥቷል፣ በ አባይ ቁጣውን ይገልጻል፦
ይገርማል፤ እንግሊዝ መጀመሪያ ላይ የአባይን ውሃ ለግብጽና ሱዳን ሰጠች፤ ኢትዮጵያ ግን ተጠማች፣ አሁን ግን አምላካችን በቃችሁ አላቸው፤ ኢትዮጵያን የሕዳሴውን ግድብ እንድትሠራ አዘዛት፣ ተንኮለኞቹ ጣሊያኖች “እንርዳ” ብለው ከች አሉ፥ ግብጾች ከከሃዲዎች ጋር ተባብረው ግንበኛ ስመኘውን ገደሉ… አቤት ድፍረት!
ሱዳን፣ ግብጽ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፤ ተውን! አትተናኮሉን፤ ኢትዮጵያን አትንኩ!
አባይ የእግዚአብሔር ወንዝ ነው!
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: ለንደን, ሙስሊሞች, ሱዳን, ሽብር, አባይ, አደጋ, እንግሊዝ, የሕዳሴ ግድብ, ግዮን, Boat Accident, Britain, Islamic Terror, River Nile, Sudan, Westminster | Leave a Comment »