የወንድማችን የስመኘው በቀለ ደም መፍሰስ ያመጣው መቅሰፍት?
ያውም በጣሊያን ብሔራዊ ቀን (Ferragosto) እና በካቶሊኮች ፍልሰታ/ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እርገት በዓል ዋዜማ…
ሰሜን ምዕራብ ጣሊያን የወደብ ከተማ በጄኖዋ ወንዝ ላይ የተሠራው አንድ የፈጣን መንገድ ድልድይ ፈራርሶ ቢያንስ 35 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኃይለኛ ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የድልድዩ ፍርስራሾች እና ተሽከርካሪዎች ወደ 45 ሜትር ጥልቀት ላይ በሚገኙ የባቡር ሀዲዶች፣ ሕንፃዎች እና ወንዝ ላይ ተከስክሰው ወድቀዋል። “ወንዝ”
ባካባቢው የነበሩ ሰዎች እንደጠቆሙት ድልድዩ ሊፈርስ ሲል የመብረቅ ብልጭታ አስቀድመው አይተው ነበር። “አምላኬ!” እያሉ በድንጋጤ ሲጮሁ ቪዲዮው ላይ ይሰማሉ።
ልብ እንበል፦ ድልድዩ ወንዙ ውስጥ ከመውደቁ በፊት የመብረቁ ብልጭታ ይታያል።
ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማርላቸው!
ይህን ዜና ስሰማ እንደ መብረቁ በሰከንድ ብልጭ ብሎ የታየኝ በአባይ ወንዝና የኅዳሴው ግድብ ዙሪያ እየተሠራ ያለው ተንኮል ነው። የወንድማችን የስመኘው በቀለ መገደል፡ በእግዚአብሔር ዘንድ፡ እንዲሁ የሚረሳ እና ቀላል ሆኖ የሚታይ ጉዳይ አይደለም። እኛ ብንረሳ እግዚአብሔር አይረሳም!
ታላቁን የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ኮንትራት ወስዶ የሚገነባው “ሳሊኒ” የተባለው ጣሊያናዊ ኩባንያ ነው።
ከዓመት በፊት ስለዚህ ጉዳይ በጥቂቱም ቢሆን እንደሚከተለው ጦምሬ ነበር፦
+ ከሶሪያ በኋላ | ሮማውያኑ ሉሲፈራውያን በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ሴራ እየጠነሰሱ ነው
“አገራችንን፣ ጥንታዊ እምነታችን እና ቅዱሱን የአባይ ውሃ በሚመለከት ግብጻውያን ብቻ ሳይሆኑ፣ ሁሉም በሮማውያን ሥር ያሉት ሉሲፈራውያን አገሮች ተጨንቀዋል። የቫቲካን ሰዎች በታሪክ ከገዳይ አረቦች ጋር በመተባበር ይሰሩ እንደነበር የሚታወቅ ነው፤ ፀረ–ኢትዮጵያ ዘመቻዎችም በታሪክ አጋጣሚ ተደጋግመው ተከስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያከናውነው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ መሆኑ ይከነክነኝ ነበር፤ ኩባንያው በኢትዮጵያ ላይ በተጠነሰሰው ሴራ ምን ዓይነት ሚና እንደሚጫወት ባላውቅም፤ ግን የአባይ ጉዳይ ግብጽን ብቻ ሳይሆን፡ ወንዛችን የሚነካቸውን መላውን የሚዲቴራንያን ባሕር አገራት፡ ጣሊያንን ጨምሮ፡ በጥልቅና በጥብቅ የሚመለከት ጉዳይ ነው።“
+ በሳውዲዋ መካ መጥቶ የነበረውን መቅሰፍት እናስታውሳለንን?
+ ከ ፪ ዓመት በፊት በመካ ፭ሺ “ሀጂዎችን” የገደለው ፡ ከቁልቢ በቱርኮች ተሠርቆ ወደ መካ የተወሰደው የ ‘ቅ/ ገብርኤል ጽላት’ ይሆን?
+ Could The Crane Collapse in New York Be Related to The Mecca Collapse on 9/11?