ተዓምረ ማርያም | ክርስቲያን ወገኖቻችንን ለመግደል መጥቶ የነበረው ሰይጣን በራሱ ፈንጅ ተበጣጥሶ ሞተ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 12, 2018
በትናንትናው ቅዳሜ ዕለት ከካይሮ ከተማ በስተሰሜን ከምትገኘው ሞስቶሮድ ከተማ በሚገኝ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የታቀደወን የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ቅድስ ድንግል ማርያም አክሽፋዋለች።
ድንቅ ተዓምር ነው፤ ልክ በጅጅጋው የጂሃድ ጥቃት ሣምንት፤ እነ ቀብሪ ደኃር ደብረ መድኃኒት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለት፣ እነ ቄስ ኪዳነ ማርያም ንብረቱ እና አባ ገብረ ማርያም አስፋው በተገደሉ በሳምንቱ።
ቀናችንን በዚህ ዓይነት ዜና ስንጀምር እንዴት ደስ ይላል! እጅግ በጣም እንጂ! ፍርድ ለማየት ዛሬ ብዙ መጠበቅ የለብንም፤ ክብር ለፍትህ አምላክ ለእግዚአብሔር!
______
Leave a Reply