በትናንትናው ቅዳሜ ዕለት ከካይሮ ከተማ በስተሰሜን ከምትገኘው ሞስቶሮድ ከተማ በሚገኝ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የታቀደወን የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ቅድስ ድንግል ማርያም አክሽፋዋለች።
ድንቅ ተዓምር ነው፤ ልክ በጅጅጋው የጂሃድ ጥቃት ሣምንት፤ እነ ቀብሪ ደኃር ደብረ መድኃኒት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለት፣ እነ ቄስ ኪዳነ ማርያም ንብረቱ እና አባ ገብረ ማርያም አስፋው በተገደሉ በሳምንቱ።
ቀናችንን በዚህ ዓይነት ዜና ስንጀምር እንዴት ደስ ይላል! እጅግ በጣም እንጂ! ፍርድ ለማየት ዛሬ ብዙ መጠበቅ የለብንም፤ ክብር ለፍትህ አምላክ ለእግዚአብሔር!
______