Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2018
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 11th, 2018

ማማ ኢትዮጵያን በመተናኮል ላይ ያለችው ፀረ-ክርስቶስ ቱርክ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብታለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 11, 2018

እንግዲህ፤ “ተውውው፡ ኢትዮጵያን አትንኩ ተብለዋል!

ከዛሬው ዕለት እስከ መስከረም ፩ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም ድረስ አንድ ወር ነው የሚቀረው!

ቱርክ ጥልቅ ውድቀት ላይ ነች፤ የውጭ ገንዘብ አጥሯታል፣ ዕዳ በዕዳ ነች፤ የ “ሊራ” ገንዘቧ ዋጋ አሽቆልቁሎ በመውደቅ ላይ ነው።

ባለፈው ጊዜ ወፈፌው የቱርክ ፕሬዚደንት “በመስቀልና በግማሽ ጨረቃ መካከል ጦርነት ይነሳል” ብሎ ነበር። ዛሬ ደግሞ የተቀመጠበት ዙፋን ሲያቃጥለው፡ “እናንተ ዶላር አላችሁ እኛ አላህ አለን” በማለት ይቀበጣጥራል።

  • ኢየሱስ ክርስቶስ “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ፡ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯፥፳] ይለናል።
  • መሀመዳውያኑ ግን “አላህ ዶላርን ይተካል” ይሉናል።

በጣም የተቅበጠበጠችው ቱርክ እንዲህ ስትወራጭ ማየት እንዴት ደስ ይላል!? „ሻደን ፍሮይደ” „Schadenfreude„ (የጉዳት ደስታ) ይሉታል በታሪክ ቱርክን በመርዳት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ጀርመኖች።

መተተኛዎቹ ቱርኮች ምግባችንን፣ ውሃችንን፣ ስኳራችንን፣ ጨርቃጨርቃችንን በአዘጋጃቸው ወኪሏ በፕሬዚደንት ሙላቱ (ቱርክ አምባሳደር ነበሩ) ፈቃድ በመበከል ላይ ናች። ይህ አልበቃ ብሏት፡ በድፍረት፡ ክቡር መስቀላችንን ጫማዎች ላይ እየለጠፈች ትልክልናለች።

ኢትዮጵያን በሱዳንና ሶማሊያ በኩል በመክበብ ለመተናኮል ላይ የምትገኘው ቱርክ አሁን ከፍተኛ ቀውጥ ላይ ናት፣ አሜሪካውዊን ክርስቲያን ከእስር ቤት አልፈታም በማለቷ አሜሪካ ፊት ተጋፍጣለች፤ አቶ አብይ አህመድን ለማየት ፈቃደኛ ያልነበሩት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ማዕቀቡን ደርደረውባታል። ታዲያ በብድር ገንዘብ (እስከ 200 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የምዕራባውያን ባንኮች ዕዳ አለባት) ሰክሮ የነበረው ወፈፌ ፕሬዚደንቷ ስካሩ በረድ ሲልለት፡ “እናንተ ዶላር አላችሁ፡ እኛ አላህ አለን” ማለት ጀመረ።

ከሙስሊም እህትማማች አገሮቿ ጋር ተመሳጥራ ኢትዮጵያ ዶላር እንዳታገኝ ሤራ ስትጠነስስ የነበረቸው ቱርክ አሁን ገንዘብ ከየት አምጥታ ነው እነ አልሸባብን የምትቀልበው?

ግን አየን አይደል፡ ምዕራባውያኑ የቱርክን ኤኮኖሚና ጦር ሠራዊት ለዘመናት እየደጎሙ ተወዳዳሪ የሌለው እርዳታ እንዳበረከቱላት። 200 ቢሊየን ዶላር ብድሩ ባጠቃላይ ከሚያደርጉላት እርዳታ 5% ቱን እንኳን አይሆንም። ኢትዮጵያ አገራችን ለህዳሴው ግድብ እንኳን 3 ቢሊየን ዶላር ከምዕራባውያኑ ማግኘት አልቻለችም።

  • ለነገሩማ እናት ኢትዮጵያ ናት “እናንተ ዶላር አላችሁ፡ እኛ እግዚአብሔር አለን” ማለት የሚገባት።

______

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: