ተዓምር በሜክሲኮ | እግዚአብሔርን እየለመኑ በሕይወት የተረፉትን መንገደኞች አንድ ክርስቶስን የተቀበለ የቀድሞ ሙስሊም በቪዲዮ ቀርጿቸው ነበር
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 2, 2018
ባለፈው ማክሰኞ በነበረው የሜክሲኮ የአውሮፕላን አደጋ መንገደኞች ‘እየሱስ ክርስቶስ በሩን ክፈትልን እያሉ ሲማፀኑ የሚያሳይ አስደናቂ ቪዲዮ ነው።
አውሮፕላኑ ከዱጋንጎ አለምአቀፋዊ አውሮፕላን ማረፊያ በ 3፡ 45 ፒኤም፡ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በነበረበት የአየር ጠባይ ላይ አሽኮብክቦ ለመብረር ሙከራ አድርጓል። ይህ ወደ ሜክሲኮ ከተማ ለመብረር አቅዶ የነበረው አውሮፕላን እንደተነሳ ከፍታውን ለመያዝ ሲሞክር፡ እንደገና በመውረድ ማሽኮብኮቢያውን መንገድ ስቶ በመወርወር በ 460 ሜትር ርቀት በሚገኘው ሜዳው ላይ ተከሰክሷል።
የተዓምር ነገር ሆኖ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት በአጠቃላዩ 103 ሰዎች፡ ቀሳውስትን ጨምሮ፤ በሕይወት ተርፈዋል። አውሮፕላኑ በድህረ–ፍርስራሽ የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
ሁለተኛው ክፍል ላይ እንደሚታየው ተዓምሩን በከፊልም ቢሆን በቪዲዮ የቀረጸው አብሮ ይጓዝ የነበረውና፡ እስልምናን በመተው ክርስቶስን የተቀበለው ኢራናዊ ነው።
ሁለት ደቂቃ በሚወስደው ቪዲዮው ላይ፡ አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት እና ከአደጋውም በኋላ ከበስተጀርባ ሴቶች፣ ወንዶች እና ሕፃናት ሲጯጯሁ ይሰማል፤ የ እግዚአብሔርን ስም ጮክ ብለው ሲጠሩ እና “ኢየሱስ ክርስቶስ ባክህ በሩን ክፈተው” በማለት ሲማፀኑ ይሰማሉ።
የቪዲዮው አንሺ ኢራናዊ በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን ተናግሯል፦
“በእግዚአብሔር ጸጋ ደህና ነኝ፡ እርሱ ይመስገን በህይወት አለን፣ ይህ ሌላ ነገር አይደለም ትልቅ የእግዚአብሔር ተዓምር ነው፣ ሕይወት ስላለሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ብድር አለበኝ፣ ዲያቢሎስ ሕይወቴን ሊወስድ እችላለሁ ብሎ አስቦ ነበር፡ ነገር ግን አሁን እንዲያውም ለ ኢየሱስ ክርስቶስ እራሴን በይበልጥ እንደሰጥ ረድቶኛል”
Leave a Reply