ታዋቂው ካናዳ-ኢትዮጵያዊ ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ (The Weeknd) እና ዝነኛዋ አሜሪካዊት አርቲስት ሰሌና ጎሜዝ በአንድ ወቅት የፍቅር ጓደኛሞች ነበሩ።
ሰሌና ይህን የአንገት ላይ መስቀል አጥልቃ ከተነሳቸው ፎቶ ላይ ነው የቱርክ ቴሌቪዢን (ቲቪ8) መስቀሉን በፎቶሾፕ ፍቆ (ያውም ተልካሻ በሆነ መልክ) ለተመልካቾች ያቀረበው።
እንጊድህ ይህ ቅሌት እየተፈጸመ ያለው ከሁሉም ሙስሊም ከሚባሉት አገሮች “ዘመናዊ ሆናለች፡ ተሻሽላለች” በምትባለዋ ቱርክ መሆኑ ነው። ስለ ምዕራባውያኑ የሆሊውድ አርቲስቶች ዜና እያቀረቡ እንኳን በጌታችን መስቀል ላይ ያላቸውን ጥላቻ መደበቅ እንኳን አይችሉም፤ ደካሞች!
በእውነት አሳፋሪ የሆነ የአውሬው መንፈስ ዘመን ላይ እንገኛለን፤ በግልጽ ፀረ–ክርስቶስ ሆና የምትታየው ቱርክ የጌታችን መስቀል ጫማ ላይ አሳርፋ ጫማዎችን ወደ ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያና ግሪክ እየላከች እንዲረገጥ ታደርጋለች። አብረውን የሚሠሩ ቱርኮች መስቀላችንን ሲያዩ የሚያሳዩንን ዲያብሎሳዊ ጥላቻ ሁላችንም በየቀኑ የምናየው ነው።
በክርስቲያኖች ዘንድ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች የሚያራክሱ የሚመስላቸው ቅዱሳን አይረክሱም ይህን ያዘጋጀው እና ገዢው ወይም ተገልጋዩ ነው የሚረክሰው።
ቱርክ የፀረ–ክርስቶስ ፍዬላማ አገር ነች። ተዋሕዶ ክርስቲያን ሆነህ/ሽ ቱርክ ከሆነ ነገር ሁሉ የማትርቅ/ቂ ፤ ጋኔን የተሞላበትን የቱርክ ፊልምና ድራማ ከማየት የማትቆጠብ/ቢ ከአውሬው ጋር በፈቃዳችሁ ለመደመር የወሰናችሁ ናችሁ ማለት ነው፤ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ!